እንዴት ማዘጋጀት እና መርዳት እንደሚቻል

መረጃ ይዘው ይቆዩ፣ ቤትዎ እና የጉዞ ዕቅዶችዎን ላልተተጠበቀው ሁኔታ ያዘጋጁዋቸው። የእግረኛ መንገዶችዎን ከበረዶ ግግር እና ክምር ነጻ ያድርጓቸው። እርዳታ የሚፈልጉትን ያግዙ።  

ከበረዶ በፊት

ላልተጠበቀው ሁኔታ ቤትዎን ያዘጋጁ።

  • ለዝግጅት እንዲረዳዎ የበጋ የበረዶ ማዕበል መፈተሻ ያውርዱ። የአየር ሁኔታ ትንበያውን ይከታተሉ እና ከባድ የሆነ የአየር ሁኔታ ሊያጋጥም ከሆነ ዕቅድ ያዝጋጁ። 
  • ከበረዶ ማዕበሉ በፊት የሚፈልጓቸውን ነገሮች ያከማቹ። የቤተሰብ የድንገተኛ ግዜ ዕቅድ፣ ስልክ እና ተንቀሳቃሽ ቻርጀር፣ በባትሪ የሚሰራ ሬድዮ፣ የበረዶ መጥረጊያ ኣካፋ፣ የጎዳና ጨው የሞላ ከረጢት፣ ሙቀት ሰጪ የሆኑ ልብሶች፣ ተጨማሪ ብርድ ልብሶች፣ የእጅ መብራቶች፣ የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ ኪት እና ቢያንስ ለሶስት ቀናት የሚሆን የምግብ/ውሃ/መድሃኒት አቅርቦት ይኑርዎ።

ይዘጋጁ

ከበረዶ ማዕበሉ በፊት የሚፈልጓቸውን ነገሮች ያከማቹ። የበረዶ አካፋ፣ የመንገድ ጨው ከረጢት፣ ሙቅ ልብሶች፣ ተጨማሪ ብርድ ልብሶች፣ የእጅ ባትሪዎች፣ የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ ጥቅሎች፣ እና ቢያንስ ለሶስት ቀናት የሚበቃ የምግብ/ የውሃ/ የመድሀኒት አቅርቦት ይኑርዎት።

ቅዝቃዜ ከመምጣቱ በፊት

የበረዶ ግግር እንዳይፈጠር ለመከላከል የድንጋይ ጨው (ወይም ሌላ ለአካባቢ ተስማሚ የሆነ ምርት) በእግረኛ መንገድዎ፣ በእግረኛ መተላለፊያዎች እና በመወጣጫ ኩርባዎች ላይ ይረጩ።

በረዶ ሲዘንብ- የእግረኛ መንገዶቹን ያጽዱ

ከመኖሪያ ቤትዎ ወይም ከንግድ ተቋምዎ ፊትለፊት የሚገኙትን የእግረኛ መንገዶች በየ 12 ሰዓቱ የበረዶ ብናኙ ወደ ግግር ከመቀየሩ በፊት ያጽዷቸው።

ጎረቤትዎን ይመልከቱ

ጎረቤትዎ እርዳታዎን እንደሚፈልግ የሚያውቁ ከሆነ የቻሉትን ያህል ያግዙት አብረው ይስሩ እና የከተማ ማዕዘን የእግረኛ መንገድዎ፣ የማዕበል መፍሰሻዎች እና የማዕዘን ኩርባ መወጣጫዎች ከበረዶ/ ከጠጣር በረዶ የፀዱ መሆናቸውን ለማረጋገጥ እቅድ አውጡ።

የበረዶ መጥረግ የደህንነት አጫጭር መረጃዎች

ጉዳትን ያስወግዱ! የሚከተሉትን የመረጃ ምንጮች ተጠቅመው የበረዶ ብናኝ እና የበረዶ ግግርን ደህንነትዎን በጠበቀ አኳሃን ያስወግዱ፡

ማስጠንቀቂያ፡ ከተማይቱ በእግረኛ መንገዶች ላይ ያለውን የበረዶ ክምር በመጥረግ ላይ ለሚያጋጥሙ የንብረት ጉዳትም ይሁን አካላዊ ጉዳቶች ሃላፊነት ኣትወስድም።

ለመኖሪያ አከባቢያችን የበረዶ መጥረግ ስራ በጎ ፈቃደኛ ይሁኑ

በዚህ የበጋ ወቅት እርዳታዎን የሚፈልጉ ጎረቤቶችዎን ለማገዝ በጎ ፈቃደኛ መሆን ይፈልጋሉ? የሲያትል ከተማ የማህበረሰቡን የበረዶ መጥረግ ጥረቶችን ለመደገፍ የሙከራ ፕሮግራም በማስጀመር ላይ ነች። የዚህ ዓላማ አረጋውያን እና የመንቀሳቀስ ተግዳሮቶች ያሉባቸውን ሰዎች በቤቶቻቸው አጠገብ የሚገኘውን በረዶ በማጽዳት ከቤታቸው ወጥተው ወደ ፈለጉበት ቦታ እንዲሄዱ ማስቻል ነው።

በዚህ ክረምት ዉርጭ እና በረዶ ሲመጡ የተቸገረን ጎረቤት ለመርዳት ፍቃደኛ ከሆኑ፣ እባክዎን በ 684-Road@seattle.gov ኢሜይል ያድርጉ ወይም በ (206) 684-7623 በመደወል በደንበኛ እንክብካቤ ቡድናችን ይመዝገቡ።

የበረዶ መጥረግ እርዳታን ይጠይቁ

በቤታቸው ዙርያ ከሚገኙ የእግረኛ መንገዶች ላይ በረዶን ለመጥረግ እርዳታን የሚሹ ሰዎች ከ Neighbors Helping Neighbors የበረዶ መጥረግ ፕሮግራም እገዛን ሊጠይቁ ይችላሉ!

በዚህ ክረምት ዉርጭ እና በረዶ በሚከሰትበት ጊዜ የበጎ ፈቃደኞች የበረዶ መጥረግ እርዳታ ለማግኘት መመዝገብ ከፈለጉ፣ እባክዎን ወደ 684-Road@seattle.gov ኢሜይል በማድረግ ወይም በ (206) 684-7623 በመደወል በደንበኛ እንክብካቤ ቡድናችን ይመዝገቡ። የክረምቱ የአየር ሁኔታ ከመምጣቱ በፊት በአካባቢዎ ከሚገኝ በጎ ፈቃደኞች ጋር እርስዎን ለማገናኘት የተቻለንን እናደርጋለን።

Transportation

Greg Spotts, Director
Address: 700 5th Ave, Suite 3800, Seattle, WA, 98104
Mailing Address: PO Box 34996, Seattle, WA, 98124-4996
Phone: (206) 684-7623
684-Road@seattle.gov

Newsletter Updates

Subscribe

Sign up for the latest updates from Transportation

The Seattle Department of Transportation (SDOT) is on a mission to deliver a transportation system that provides safe and affordable access to places and opportunities for everyone as we work to achieve our vision of Seattle as a thriving, equitable community powered by dependable transportation.