7 ቁጥር የአውቶቡስ መስመር በሲያትል ውስጥ
አማርኛ • 繁体字 • 한국어 • af-Soomaali • Español • Tagalog • Tiếng việt • English
አሁን ምን እየሆነ ነው ያለው?
በቁሳቁሶች መዘግየት እና በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት የሰራተኛ ቡድኖች በደቡብ ዋልደን መንገድ እና በደቡብ ስቴት መንገድ ለጊዜው ስራ አቁመዋል። ይህንን አካባቢ ለሁሉም ተጓዦች ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ በምንሰራበት ወቅት ለትዕግስትዎ እና ለትብብርዎ እናመሰግናለን።
በዚህ ጊዜ ውስጥ ጊዜያዊ የአውቶቡስ ማቆሚያ መዘጋቶች እና ሌላ ጋ ማዘዋወሮች ሊኖሩ ይችላሉ። እባክዎን ከኪንግ ካውንቲ ሜትሮ ምልክቶችን እና ዝመናዎችን ይከተሉ።
በቅርብ ጊዜ የሚደረጉ የማስተዋወቅ ዝግጅቶች:
በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ በሚከተሉት ዝግጅቶች ወደ ማህበረሰቡ ውስጥ እንወጣለን:
- Safeway Rainier Valley Square (3820 Rainier Ave S) ብቅ ባይ፣ ማክሰኞ፣ ነሐሴ 2 ከ2-5 ከሰዓት በኋላ
- ኦቴሎ ፌስቲቫል፣ ኦቴሎ የመጫወቻ ሜዳ፣ እሑድ፣ ነሐሴ 14 ከቀኑ 12-6 ሰዓት ከምሽቱ
- የቅዳሜ ምሽት ገበያ፣ ኮሎምቢያ ከተማ፣ ቅዳሜ፣ ነሐሴ 20 ከ6-10 ከምሽቱ
- የጨዋታ ትልቅ ቀን፣ ረኒየር የጨዋታ ሜዳ፣ ቅዳሜ፣ ነሐሴ 20 ከቀኑ 12-6 ሰዓት ከምሽቱ
- Rainier Beach Back to School Bash፣ Rainier Beach የማኅበረሰብ ማዕከል ፕላዛ፣ ቅዳሜ፣ ነሐሴ 27 ከቀኑ 12-4 ሰዓት ከምሽቱ
- የኮሎምቢያ ከተማ የገበሬዎች ገበያ (ቀኖቹ በቅርቡ ይረጋገጣሉ)
ስለ ፕሮጀክቱ ጥያቄዎች?
በ 7TransitPlus@seattle.gov ኢሜይል ይላኩልን ወይም በ (206) 771-0481 የድምጽ መልእክት ለኛ ይተውልን።
የፕሮጀክት ዳራ
7 ቁጥር የአውቶቡስ መስመር በሲያትል ውስጥ ትምህርት ቤቶች፣ የማህበረሰብ ማእከላት፣ የግሮሰሪ መደብሮች፣ ቤቶች እና መናፈሻዎችን ጨምሮ ከ11,000 በላይ ተሳፋሪዎችን ወደ ተለያዩ መዳረሻዎች የሚያገለግል ከፍተኛ የተሽከርካሪ መንገዶች አንዱ ነው። እና የ7 ቁጥር መስመር አውቶቡሶች በየ10 ደቂቃው ወይም ቀኑን ሙሉ የተሻለ እንዲመጡ ታቅዶ ሳለ፣ የመንገድ ሁኔታዎች መዘግየትን ሊያስከትሉ ይችላሉ።
ሰዎች አስቀድመው ስለ 7 የሚወዱትን ነገር እንዳለ ለማቆየት እና ከሊንክ የቀላል ባቡር፣ ከሜትሮ የሕዝብ ማመላለሻ ማዕከል እና ከዚያም በላይ መገናኘት ቀላል ለማድረግ እንፈልጋለን። ይህንን ለማድረግ፣ የእግረኛ መንገዶችን፣ ማቋረጦችን፣ ምልክቶችን እና የአሜሪካን አካል ጉዳተኝነት ድንጋጌ (ADA) የሚያሟሉ ኩርባዎችን በመትከል ላይ ማሻሻያዎችን እያደረግን ነው።
የፕሮጀክት አጠቃላይ እይታ
በ2018 እና 2019 ከማህበረሰቡ ካገኘነው ግብአት ላይ በማጎልበት፣ የመጨረሻ ንድፎች በ2021 የተጠናቀቁ ሲሆን እና የዚህ ትራንዚት-ፕላስ መልቲሞዳል ኮሪደር (Transit-Plus Multimodal Corridor) ፕሮጀክት አካል ሆነው የተደረጉ ማሻሻያዎች በረኒየር ጐዳና ደቡብ ላይ በእግር፣ በብስክሌት እና በሚንከባለሉ ሰዎች ላይ ማሻሻያዎችን ይጨምራል። በአካባቢዎ እየመጡ ስላሉት ማሻሻያዎች የበለጠ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ከታች ያሉትን ካርታዎች እና መግለጫዎችን ይመልከቱ።
የረኒየር ጐዳና ደቡብ የአውቶብስ-ብቻ መስመሮች አሁን እየታቀደ እና በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ እየተገነባ ያለ ብቻውን የቆመ ፕሮጀክት ነው። የቦታዎች እና የጊዜ ሰሌዳዎች አጭር መግለጫ በዚህ ካርታ ላይ ይገኛል።
የፕሮጀክት ካርታ
ዋና ማሻሻያ የተደረገባቸው ቦታዎች
ረኒየር ጎዳና ደቡብ እና ደቡብ አላስካ መንገድ
በዚህ መስቀለኛ መንገድ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ:
- በረኒየር ጎዳና ደቡብ እና ደቡብ ዲርቦርን እና ደቡብ ቻርለስ መስቀለኛ መንገዶች ላይ አዲስ የአሜሪካን አካል ዱዳተኝነት ድንጋጌ (ADA) የኩርባ መወጣጫዎችን መጨመር
- በረኒየር ጎዳና ደቡብ እና ደቡብ ዲርቦርን እና ደቡብ ቻርለስ መንገዶች ላይ የእግረኛ መንገዶችን መጠገን
- የእግረኛ መንገድ ተደራሽነትን ለማሻሻል በረኒየር ጐዳና ደቡብ በምስራቅ እና በምዕራብ በኩል ከሠፈር መውጫ የመኪና መንገዶችን መጠገን
ረኒየር ጐዳና ደቡብ እና I-90
በዚህ የረኒየር ጐዳና ደቡብ እና I-90 መውጫ መወጣጫ መገናኛ ላይ፣ መሻገሪያዎችን የበለጠ ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ ጉልህ ማሻሻያዎችን እናደርጋለን፣ እነዚህንም ጨምሮ:
- አዲስ የአሜሪካን አካል ጉዳተኝነት ድንጋጌ (ADA) ኩርባ መወጣጫዎችን ማከል
- በመስቀለኛ መንገድ እና በረኒየር ጐዳና ደቡብ በምዕራቡ በኩል የእግረኛ መንገዶችን መጠገን
- በረኒየር ጐዳና ደቡብ እና I-90 መውጫ መወጣጫ መስቀለኛ በስተሰሜን በኩል አዲስ የእግረኛ መሻገሪያ መሥራት
ረኒየር ጎዳና ደቡብ እና ደቡብ ስቴት መንገድ
አሁን ባለበት ሁኔታ፣ በረኒየር ጎዳና ደቡብ ምስራቃዊ በኩል በሚገኘው በመንገዱ ለመሻገር እና ለረጅም ዝርጊያ በጎዳና ላይ እንዲቆዩ ሰዎች በእግር መሄድን፣ በመንከባለል፣ እና በብስክሌት መጋለብን ይጠይቃል። ወደዚህ መስቀለኛ መንገድ ማሻሻያዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ:
- መሻገሪያዎችን አጭር እና ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ አቀማመጡ የተስተካከለ ኩርባ ክብ ራስ መገንባት
- የመስቀለኛው መንገድ ላይ በሰሜን በኩል አዲስ የአሜሪካን አካል ጉዳተኝነት ድንጋጌ (ADA) የኩርባ መወጣጫዎችን ማከል
- በመስቀለኛው መንገድ ላይ በሰሜን በኩል በመንገዱ ውስጥ አዲስ ኮንክሪት
ረኒየር ጐዳና ደቡብ እና ደቡብ ዋልደን መንገድ
በዚህ መስቀለኛ መንገድ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች የብስክሌት መሻገሪያዎችን የበለጠ ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ የብስክሌት የታህታይ መዋቅር ግንባታን ይጨምራል። እነዚህ ማሻሻያዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ:
- በመስቀለኛው መንገድ በሰሜን እና በደቡብ በኩል የብስክሌት መወጣጫዎችን መገንባት
- በመስቀለኛው መንገድ ውስጥ ሁሉ አረንጓዴ የብስክሌት መሻገሪያ ምልክቶችን መቀባት
እንዲሁም ማሻሻያዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ:
- አዲስ የመንገድ መወጣጫዎችን መገንባት
- ረኒየር ጐዳና ደቡብ እና ደቡብ ዋልደን መንገድ ላይ የእግረኛ መንገድ ክፍሎችን መጠገን
- በመንገድ ውስጥ የእግረኛ ንጣፍ መጠገን
- የአሽከርካሪዎችን እና የእግረኛ ግጭቶችን ለመቀነስ የትራፊክ ምልክትን ለተጠበቁ የግራ መታጠፊያዎች ማሻሻል
- መሪ የእግረኛ የሚገፉ አዝራሮችን ክፍተት ጊዜ መጨመር
- የእግረኛ መንገድ ተደራሽነትን ለማሻሻል ከሠፈር መውጫ የመኪና መንገድ መጠገን
ረኒየር ጎዳና ደቡብ እና ደቡብ ብራንደን መንገድ
በደቡብ ስቴት መንገድ ላይ ከታቀዱት ተመሳሳይ ማሻሻያዎች ጋር፣ ለሚራመዱ እግረኞች፣ ለሚንከባለሉ እና ለቢስክሌት ጋላቢዎች መሻገሪያዎችን አጭር ለማድረግ ማሻሻያዎችን እንገነባለን። በዚህ መስቀለኛ መንገድ ላይ የሚከተሉት ማሻሻያዎች ያካትታሉ:
- ከአሜሪካን አካል ጉዳተኝነት ዲንጋጌ (ADA) የኩርባ መወጣጫዎች ጋር መሻገሪያን አጭር እና አስተማማኝ ለማድረግ የኩርባ አምፖሎችን መገንባት
- ከሲቲ ቴሪያኪ ቀጥሎ በደቡብ ብራንደን ጎዳና በደቡብ በኩል የእግረኛ መንገድን መጠገን
- ነባሩን የእግረኛ መንገድ ማደስ እና የብረት ቁራሹን ቀለም መቀባት ማቆም
- ከመስቀለኛው መንገድ በምዕራብ በኩል በመንገዱ ውስጥ አዲስ ኮንክሪት
ረኒየር ጐዳና ደቡብ እና ደቡብ ፊንድሌይ መንገድ
በዚህ መስቀለኛ መንገድ ላይ በደቡብ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ የመስቀለኛ መንገዱ አቅጣጫዎች በመካከለኛው ውስጥ የሚያቋርጡትን ሰዎች ለመጠበቅ የኩርባ ቋሚዎችን መቀባት እና መትከልን ጨምሮ ማሻሻያዎችን አድርገናል። ይህ ፕሮጀክት አሁን ያለውን ነባር ቀለም እና ልጥፎችን ማደስን ያካትታል። ተጨማሪ ማሻሻያዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ:
- በመስቀለኛው መንገድ በአራቱም ማዕዘናት ላይ አዲስ የኩርባ መወጣጫዎችን መገንባት
- ከደቡብ ፊንድሌይ መንገድ በስተደቡብ በኩል እና በረኒየር ጐዳና ደቡብ ሰሜናዊ ምዕራብ በኩል የእግረኛ መንገድን መጠገን
- ነባሩን ቀለም ማደስ/የኩርባ አምፖሎች እና መካከለኛ ቋሚን መለጠፍ/ማቆም
በሬኒየር አቅጣጨ ሌሎች ፕሮጀክቶች
የፕሮጀክት ቡድናችን ፕሮጀክቶችን ከመከታተል ጋር በቅርበት ተቀናጅቷል:
የፕሮጀክት ታሪክ
የ2015 ለሙቭ ሲያትል (Move Seattle) ቀረጥ የገንዘብ ድጋፍ የ7 መስመርን ወደ RapidRide መስመር ለማሻሻል አካቷል። ይህ ለውጥ የ2016 ትራንዚት ማስተር ፕላን ዝመና እና የ2017 የሜትሮ የረጅም ርቀት አገናኝ እቅድ ውስጥ ተካቷል።
7 ቁጥር የአውቶቡስ መስመርን ወደ RapidRide R መስመር ማሻሻል በሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) እና በኪንግ ካውንቲ ሜትሮ መካከል አጋርነትን ይጠይቃል። ሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) ለመንገድ፣ ለእግረኛ መንገዶች እና ለሚራመዱ፣ ለቢስክሌት፣ ለመንከባለል እና ለመንዳት መሠረተ ልማት ማሻሻያዎችን የማድረግ ኃላፊነት አለበት። እነዚህን ማሻሻያዎች እያደረግን ያለነው የአውቶቡስ አስተማማኝነት እና የሕዝብ ማመላለሻ ለሚጠቀሙ ሰዎች ተደራሽነት ለማሻሻል ነው።
እንደ አለመታደል ሆኖ፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተጽዕኖዎች ገቢን በመቀነሳቸው ሜትሮ የRapidRide R Lineን ባለበት እንዲያቆም አስፈልጓል። ይህንን ፕሮጀክት በተቻለ ፍጥነት ለማስቀጠል መንገዶችን እየፈለጉ ነው። ለበለጠ መረጃ የ RapidRide R Line ድህረ-ገጽን ይጎብኙ።
የማህበረሰብ ማዳረስ
መጀመሪያ 2020: የሜትሮ ከፍቶ የማሳየት
ከኪንግ ካውንቲ የሜትሮ ራፒድራይድ አር መስመር ከፍቶ የማሳየት ጋር በማስተባበር ውስጥ ተሳትፏል
ሐምሌ 2019: በአካል የሚደረጉ ጥናቶች
በደቡብ ማሳቹሴትስ መንገድ እና ደቡብ ቤይቪው መንገድ መካከል ስለ የበለጠ ማድረስ እና የደንበኛ ተደራሽነትን ለማወቅ በረኒየር ላይ ሊሆኑ የሚችሉ የአውቶቡስ መስመሮች አቅምን ለማሳወቅ ረኒየር ጐዳና ደቡብ አጠገብ ባሉ ንግዶች የዳሰሳ ጥናቶችን አድርጓል።
ሰኔ 2019: የሲያትል ቁጥጥር ኮሚቴ የቀረጥ አንቀሳቅስ
ለባለድርሻ አካላት አጭር መግለጫ
ግንቦት 2019: የባለድርሻ አካላት አጭር መግለጫ
የሲያትል የሕዝብ ማመላለሻ አማካሪ ቦርድ
ከመጋቢት - ሚያዚያ 2018: በአካል የተደረጉ የዳሰሳ ጥናቶች
- ቻይናታዎን-ዓለም አቀፍ ወረዳ (District) የማህበረሰብ ማዕከል
- ኪንግ ዶናትስ
- የረኒየር የማህበረሰብ ማዕከል
- ቪየት ዋህ ኤስያን ሱፐርማርኬት
- የኤስያን የምክር እና የማጣቀሻ አገልግሎት
- የረኒየር ገበሬዎች ገበያ
- የኤስያን የምክር እና የማጣቀሻ አገልግሎት
- ቡሽ አፓርታማዎች
- ኢስተር ሆቴል
- ኒሆን ተረስ
- ላንግ ኮንግ ቲን ዬ ማህበር
- ሁሉም የቤተሰብ ማህበር
- ቤተ-መጻሕፍት፣ ሚኒ-ማርቶች እና የአፓርታማ ሕንፃዎችን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች ብቅ-ባዮች
መጋቢት-ሚያዝያ 2018: የባለድርሻ አካላት መግለጫዎች
- የሲያትል የብስክሌት አማካሪ ቦርድ
- የሲያትል የእግረኞች አማካሪ ቦርድ
- የሲያትል የጭነት አማካሪ ቦርድ
- የኪንግ ካውንቲ የሕዝብ ማመላለሻ አማካሪ ኮሚቴ
- የመጓጓዣ ምርጫዎች ጥምረት እና የፑጀት ሳውንድ ሳጅ
ከመጋቢት 19 - ሚያዚያ 14 ቀን 2018: የመስመር ላይ በር ከፍቶ ማሳያ
በዝርዝር የፅንሰ-ሃሳብ አማራጮች ላይ ግብዓት ለመሰብሰብ የመስመር ላይ በር ከፍቶ ማሳያ እና የዳሰሳ ጥናት፤ ማሳወቂያዎች ወደ 40,000 አድራሻዎች የተላኩ መላላኪያዎች፣ ሊስትሰርቭ ኢሜይሎች፣ ሚዲያዎች፣ እና ለማህበረሰብ ቡድኖች የተደረጉ ኢሜይሎች እና የስልክ ጥሪዎችን፤ ወደ ስፓኒሽ፣ ቻይንኛ፣ ቬይትናምኛ፣ ታጋሎግ፣ ሶማሊኛ፣ አማርኛ፣ ክመር፣ ኦሞሮ እና ትግርኛ የተተረጐሙ የመስመር ላይ እና የወረቀት የዳሰሳ ጥናቶችን ያካትታል።
2017: የቀደምት እቅድ ማዳረስ
የመጀመሪያውን የRapidRide ዕቅዶችን እና የአጋርነት ጊዜ መስመርን ከሌሎች የሲያትል ደቡብ ምዕራብ ፕሮጄክቶች ጋር በመተባበር አጋርቷል (የመላላኪያ፣ ከፍቶ የማሳየት፣ የማህበረሰብ ውይይቶች እና ማህበራዊ ሚዲያን ጨምሮ)
የገንዘብ ድጋፍ
ይህ ፕሮጀክት በ2015 በመራጮች የጸደቀው የ9-አመት ሲያትልን አንቀሳቀስ ቀረጥ በተዋጣው የገንዘብ ድጋፍ ነው። የፕሮጀክቱን ክፍሎች በፍጥነት እና በብቃት ለማድረስ በሬኒየር ጎዳና ደቡብ በኩል ከሌሎች ፕሮጀክቶች ጋር በመተባበር እየሰራን ነው።