በዝቃጭ ማሸጊያ (SLURRY SEAL) እንደገና አስፋልት በነባሩ ላይ ማንጠፍ ፕሮጀክት

This content has been professionally translated in other languages.

Este contenido ha sido traducido profesionalmente a otros idiomas.

此內容已被專業翻譯成其他語言。

Nội dung này đã được dịch chuyên nghiệp sang các ngôn ngữ khác.

Qoraalkan waxaa si xirfad leh loogu turjumay luqado kale.

Ang nilalamang ito ay propesyonal na isinalin sa ibang mga wika.

ይህ ይዘት በሙያዊ በሌሎች ቋንቋዎች ተተርጉሟል።

የተዘመነ: ግንቦት፣ 2025

አሁን ምን እየሆነ ነው?

በቅርብ ጊዜ አንዳንድ የሰፈር መንገዶችን ረዘም ላለ ጊዜ እንዲቆዩ፣ የዝቃጭ ማሸጊያ (slurry seal) በተባለ፣ ስስ የአስፋልት ንጣፍ እናለብሳለን።

ስራ በምንሰራበት ወቅት፣ መንገዶች ይዘጋሉ፣ ሁሉም የመኪና ማቆሚያዎች ይወገዳሉ፣ እና የንግድ ድርጅቶች መዳረሻ ለጊዜው ተጽዕኖ ሊደርስበት ይችላል።

የእኛ የዝቃጭ ማሸጊያ (የአስፋልት እና ጠጠር እንደገና ማንጠፍ) በሐምሌ እና ነሐሴ በሰሜን ምስራቅ እና በደቡብ ሲያትል መንገዶች ላይ ያተኩራል። እኛ የት የት እንደምንሰራ ከዚህ በታች ያሉ ካርታዎችን ማየት ይችላሉ።

እኛ የምንሠራባቸውን ቀናት መለወጥ ሊያስፈልገን ይችል ይሆናል።

Slurry seal being applied

የዝቃጭ ማሸጊያ (አስፋልት እና ጠጠር ማልበሱ) ሂደት እስከ ስምንት ሰዓት ያህል ይወስዳል። በዚህ ወቅት፣ የዝቃጭ ማሸጊያው እየደረቀ እያለ መንገዱ ላይ መንዳት አይችሉም።

ሥራ ከመጀመራችን በፊት ተሽከርካሪ ማቆም አይቻልም የሚል ምልክቶችን በመንገድ ላይ እናስቀምጣለን።

Map showing where we will be working near Lake City Way N and 115th St

ጠቅ ያድርጉ ይህን አገናኝ ሙሉ ካርታውን ለማውረድ።

Map of where we will be working in Seward Park

ጠቅ ያድርጉ ይህን አገናኝ ሙሉ ካርታውን ለማውረድ።

ምን ይጠበቃል:

እኛ በእርስዎ አካባቢ ሥራ በምንጀምርበት ቀን:

  • እስከ ስምንት ሰአታት ድረስ በአዲሱ የመንገድ ወለል ላይ መንዳት፣ ወይም ተሽከርካሪ ማቆም፣ ወይም በእግር መሄድ አይችሉም። እኛ ሥራ ስንጀምር፣ የእርስዎ መኪና መንገድ ላይ ቆሞ ከተገኜ መኪናዎ ይጐተታል። ቡድኖቻችን ከጠዋቱ 7 ሰዓት (AM) በፊት ለመስራት ሲዘጋጁ እና እርስ በርስ ሲነጋገሩ ታስተውላላችሁ።
  • እንዲሁም ደግሞ ትላልቅ የጭነት መኪናዎች እና ማሽኖች ሲመጡ፣ ሲሄዱ፣ እና ጥቅም ላይ ሲውሉ ታስተውላላችሁ። እንዲሁም ጫጫታ፣ አቧራ፣ እና ምናልባትም ንዝረቶች ይኖራሉ።
  • በእርስዎ አከባቢ ዙሪያ ተለዋጭ መንገድ ለመጠቀም ማቀድ አለብዎት።

ስለ ሥራው እርስዎ ማወቅ ያለብዎት ነገር ይኸውና:

  • ምንም የእግረኛ መንገዶች በሌለው መንገድ ላይ የምትኖር ከሆነ፣ የዝቃጭ ማሸጊያ እስከ መንገዱ ጠርዝ ብቻ ነው የሚሄደው።
  • መንገዱ እንደገና ለትራፊክ እስኪከፈት ድረስ እግረኞች እና የቤት እንስሶች ከዝቃጭ ማሸጊያ (ከተነጠፈው አስፋልት እና ጠጠር) መራቅ አለባቸው። ደርቆ ያላበቃው ማሸጊያ ቁሳቁስ (አስፋልት እና ጠጠር) ከልብስ፣ ከጫማ ወይም መዳፎች ላይ ለማስወገድ አስቸጋሪ ነው።
  • በመንገዱ ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር የሚችል የግል ግንባታ እየሰሩ ከሆነ፣ እባክዎ ከኛ ፕሮጀክት በፊት ያንን ያጠናቅቁ።
  • የእርስዎ መንገድ ቆሻሻ ወይም በድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውሉትን የማንሻ ቀን እንዲሰራ ታቅዶ ከሆነ፣ እኛ ቀደም ብሎ እንዲነሳ እናስተባብራለን።

ጥያቄዎች?

የቆሻሻ እና እንደገና ጥቅም ላይ የሚውሉ ማንሻ ጥያቄዎች፣ ወይም የእርስዎ ቆሻሻ ተነስቶ ካልሆነ እና መነሳት ከነበረበት፣ ጥያቄዎቹ ወደ ሚከተለው ሊመሩ ይችላሉ: DOT_SlurrySeal@seattle.gov ወይም (206) 775-8742 .

ስለ የዝቃጭ ማሸጊያ (አስፋልት እና ጠጠር ማልበሱ) ሂደት ይወቁ

A የዝቃጭ ማሸጊያ መንገዱን ለመጠበቅ እና ረዘም ላለ ጊዜ እንዲቆይ በመንገድ ላይ የሚዘረጋ ስስ የአስፓልት እና ጠጠር ድብልቅ ነው። ትናንሽ ስንጥቆችን ይሞላል እና የላይ ዝርጊያውን ያሳምራል፣ ለምሳሌ ግድግዳ ላይ ስንጥቅ ለማሸግ እና ለመከላከል አዲስ የቀለም ሽፋን እንደ ማድረግ ነው። በኋላ ላይ የበለጠ ትልቅ ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል አሁንም በጥሩ ሁኔታ ላይ ባሉ መንገዶች ላይ ጥቅም ላይ ይውላል።

በዚህ ላይ እንደሚታየው አጭር ቪዲዮ፣ የዝቃጭ ማሸጊያ መሳሪያው በመንገዱ ላይ ሲንቀሳቀስ፣ ድብልቁ ወደ ማከፋፈያ ሳጥን ውስጥ ይመገባል። የማሸጊያ ቁሱ በትራፊክ መስመሮች ሙሉ ወርድ ላይ ተዘርግቶ ከዚያም ይስተካከላል። እንዲሁም መሳሪያው የመንገዱን ጠርዞች ስስ በማድረግ ለሽግግር አመቺ ያደርጋቸዋል። ይህ ሁሉ የሚሆነው በአንድ እርምጃ ነው።

የታሸገው ልባስ ከደረቀ በኋላ (ጠንካራ ይሆናል)፣ መንገዱ እንደገና ሊከፈት እና በመደበኛነት መጠቀም ይቻላል። ነገር ግን፣ ስራው በታቀደለት መርሐ-ግብር ቀን ሙሉ የመኪና ማቆሚያ ገደቦች እና የመንገድ መዘጋቶች ሊኖሩ ይችላሉ።

መንገዳችን ጥሩ ይመስላል። ለምን እንደገና ንጣፉ ማድረግ አስፈለገ?

ተለዋዋጭ የመንገድ ንጣፍ (በተለምዶ አስፋልት) ከውሃ (ዝናብ) እና ከፀሀይ ጉዳት ለመከላከል እንደገና መታሸግ ያስፈልጋቸዋል። ሳይጠገኑ ከተተው፣ ንጣፉ ተሰባሪ እና ሊሰነጠቅ ይችላል። እንደገና መታሸጉ ውድ የሆኑ የጥገና ወጪዎችን ያስቀራል። መንገዶችን እንዳሉ እንዲቆዩ ለመጠበቅ መደበኛ የመከላከል ጥገና በጣም ወጪ ቆጣቢው መንገድ ነው።

መንገዱን ማዘጋጀት: ጉድጓዶችን፣ ስንጥቆችን፣ ወዘተ መጠገን።

ከዝቃጭ ማሸጊያ (አስፋልት እና ጠጠር ማልበሱ) ሂደቱ በፊት መዋቅራዊ ጉዳቱ መጠገን አስፈላጊ ነው። ወዲያው ከዝቃጭ ማሸጊያ ስራ አስቀድሞ የሲያትል መጓጓዣ መምሪያ (SDOT) ሰራተኞች ቡድን ከተመረጡት መንገዶች የተበላሹ/ የተጐዱ ቦታዎችን መጣፍ ይጀምራሉ። በተጨማሪም፣ የዝቃጭ ማሸጊያ መሳሪያዎች ወደሚሰሩ መንገዶች መድረስ እንዲችሉ፣ ዝቅ ብለው የተንጠለጠሉ ቅርንጫፎች እና ከመጠን በላይ እድገት ያላቸውን ማሳጠር ሊያስፈልግ ይችላል። የዝቃጭ ማሸጊያ (አስፋልት እና ጠጠር) በሚደርግበት ቀን፣ የሰራተኞቹ ቡድን የዝቃጭ ማሸጊያውን (አስፋልት እና ጠጠር) ከማልበሳቸው በፊት መንገዱን ጠራርገው ያዘጋጃሉ።

የትርጉም ሥራ መድረስ

እኛ በእርስዎ አካባቢ እየሠራን ስላለው የአስፋልት ንጣፍ ስራ በቋንቋዎ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ፣ እባክዎን በ (206) 775-8742 ይደውሉልን። ሲደውሉ፣ የመረጡትን ቋንቋ በእንግሊዝኛ ይንገሩን። የጽሑፍ ትርጉም እና የአስተርጓሚ አገልግሎቶች በነጻ ይገኛሉ።

የፕሮጀክት ቤተ መጻሕፍት

Transportation

Adiam Emery, Interim Director
Address: 700 5th Ave, Suite 3800, Seattle, WA, 98104
Mailing Address: PO Box 34996, Seattle, WA, 98124-4996
Phone: (206) 684-7623
684-Road@seattle.gov

Newsletter Updates

Subscribe

Sign up for the latest updates from Transportation

The Seattle Department of Transportation (SDOT) is on a mission to deliver a transportation system that provides safe and affordable access to places and opportunities for everyone as we work to achieve our vision of Seattle as a thriving, equitable community powered by dependable transportation.