የዊንተር የአየር ሁኔታ

ለክረምት ማዕበሎች ዝግጅት የሚረዱዎትን መረጃ/ ጥሬ እቃዎችን የት እንደሚያገኟቸው እና ለሲያትል በደህና መንቀሳቀስ የሲያትል የመጓጓዣ መምሪያ (SDOT) እንዴት ምላሽ እንደሚሰጥ እንዲያውቁ፣ እንኳን ወደ የSDOT የክረምት አየር ምላሽ ድህረ ገጽ በደህና መጡ።

መርጃዎች/ ጥሬ እቃዎች

ያውርዱ

የክረምት የአየር ሁኔታ ካርታዎች

ተጨማሪ መርጃዎች/ ጥሬ እቃዎች

የእግረኛ መንገዶችን ግልጽ አድርገው ያቆዩ

በበረዶ ማዕበል ወቅት ከቤትዎ ወይም ከንግድዎ ፊት ለፊት ያሉትን የእግረኛ መንገዶችን ግልጽ አድርገው ያቆዩ። ሁሉም ሰው፣ በተለይ ለመጓዝ የሚቸግራቸው ሰዎች በሰላም እንዲጓዙ፣ በደህና መመላለስ እንዲችሉ ህጉ እና ትክክለኛ መደረግ ያለበት ስራ ነው።

ሲያትል ከ2,400 ማይል በላይ የእግረኛ መንገድ አላት፣ እና የሰራተኞቻችን ቡድኖች በአንድ ጊዜ ሁሉም ቦታ ላይ መሆን አይችሉም። የእርስዎን ድርሻ እንዲወጡ በእርስዎ ላይ እንተማመናለን፣ ስለዚህ በግል ይዞታ ስር ያልሆኑ ሕንፃዎች አቅራቢያ ያሉ የእግረኛ መንገዶችን በማጽዳት እና የከተማዋን በጣም ወሳኝ መንገዶችን እንደጸዱ እንዲቆዩ ማድረግ ላይ እንድናተኩር።

  • ይዘጋጁ — ከበረዶ ማዕበሉ በፊት ያከማቹ። የበረዶ አካፋ፣ የመንገድ ጨው ከረጢት፣ ሙቅ ልብሶች፣ ተጨማሪ ብርድ ልብሶች፣ የእጅ ባትሪዎች፣ የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ ጥቅሎች፣ እና ቢያንስ ለሶስት ቀናት የሚበቃ የምግብ/ የውሃ/ የመድሀኒት አቅርቦት ይኑርዎት።
  • እንደበረዶ ከመቀዝቀዙ በፊት — የበረዶ ድንጋይ እንዳይፈጠር ለመከላከል የድንጋይ ጨው (ወይም ሌላ ለአካባቢ ተስማሚ የሆነ ምርት) በእግረኛ መንገድዎ፣ በእግረኛ መተላለፊያዎች እና በመወጣጫ ኩርባዎች ላይ ይረጩ።
  • ጎረቤትዎ ደህና መሆናቸውን ይመልከቱ — እርዳታዎን መጠቀም እንደሚፈልጉ ካወቁ ከጎረቤትዎ ጋር ያጣሩ። አብረው ይስሩ እና የከተማ ማዕዘን የእግረኛ መንገድዎ፣ የማዕበል መፍሰሻዎች እና የማዕዘን ኩርባ መወጣጫዎች ከበረዶ/ ከጠጣር በረዶ የፀዱ መሆናቸውን ለማረጋገጥ እቅድ አውጡ።
  • በረዶ ሲወርድ — የእግረኛ መንገዶችን አጽዱ — በረዶ ወደ በረዶ ድንጋይ ከመቀየሩ በፊት በየ12 ሰዓቱ ከቤትዎ ወይም ከንግድዎ ፊት ለፊት ያሉትን የእግረኛ መንገዶችን አጽዱ።

ሰዎችን ከቤቶቻቸው፣ ከንግዶቻቸው እና ከስራ ጣቢያዎቻቸው አጠገብ ካሉ የእግረኛ መንገዶች ላይ በረዶን እና ጠጣር በረዶን ስለ ማጽዳት አስፈላጊነት ለማስተማር አንድ ቪዲዮ ለመፍጠር ከRooted in Rights ጋር ቡድን ሆነናል። ይህ መረጃ ከክረምት ማዕበል በኋላ እያንዳንዱ ሰው ሁሉ እንዲዘዋወር የተሻለ ቀላል እና ደህንነቱ የተጠበቀ ያደርገዋል!

Transportation

Greg Spotts, Director
Address: 700 5th Ave, Suite 3800, Seattle, WA, 98104
Mailing Address: PO Box 34996, Seattle, WA, 98124-4996
Phone: (206) 684-7623
684-Road@seattle.gov

Newsletter Updates

Subscribe

Sign up for the latest updates from Transportation

The Seattle Department of Transportation (SDOT) is on a mission to deliver a transportation system that provides safe and affordable access to places and opportunities for everyone as we work to achieve our vision of Seattle as a thriving, equitable community powered by dependable transportation.