Greenways በአማርኛ
ሲያትል የ neighborhood greenways አውታረመረብ (ኔትዎርክ) በመፍጠር ላይ ነች። Neighborhood greenways ለእርስዎ፣ ለቤተሰብዎ፣ እና ለጎረቤቶችዎ ይበልጥ ደህንነታቸው አስተማማኝ የሆኑ፣ ይበልጥ ጸጥታ የተሞሉ የመኖሪያ ጎዳናዎች ናቸው። በጎዳናዎች ላይ ከዝቅተኛ የተሽከርካሪ ፍሰት እና ፍጥነት ጋር greenway የሚከተለውን ማድረግ ይችላል፥
- ደህንነትን ጥበቃን ይበልጥ ማሻሻል
- ሰዎች ሥራ የሚበዛባቸውን ጎዳናዎች እንዲያቋርጡ ማገዝ
- ተሽከርካሪዎች ዋና ጎዳናዎችን በመሸሽ የሰፈር ውስጥ መንገዶችን ለመጠቀም እንዳይበረታቱ ማድረግ
- የሰፈሮቻችንን የመኖሪያ ቦታነት ባህሪ ጠብቆ ማቆየት
- የተሽከርካሪዎችን ፍጥነቶችን በአነስተኛ ፍጥነት ላይ መገደብ
- ሰዎች እንደ መናፈሻ ቦታዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ሱቆች እና ምግብ ቤቶች የመሳሰሉ መሄድ የሚፈልጉባቸው ቦታዎች እንዲሄዱ ማድረግ
Neighborhood greenways የብስክሌት መሄጃ መስመሮችን የማያካትቱ ሲሆን በጎዳና ላይ መኪና ማቆሚያ ላይ የሚያስከትሉት ተጽዕኖ ካለ ዝቅተኛ ነው። አብዛኛዎቹ በዘጠኝ ዓመቱ የድምጽ ሰጪ የጸደቀ Bridging the Gap ገቢ መሰበሰቢያ በተባለው የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግላቸው ናቸው። SDOT ለእነሱ በርካታ ጥያቄዎችን ተቀብሏል። በእርግጥ፣ በርካታ ነዋሪዎች ወደ ሰፈራቸው ለመምጣት እንዲያግዛቸው Seattle Neighborhood Greenways ን መምረጥ በመጀመራቸው በጣም ደስተኛ ናቸው።
የአሁኑ ፕሮጀክቶች
- Central Area
- Wedgwood
- Rainier Valley North South
- Central Ridge
- North Seattle Greenway & School Safety Project
- West Seattle Neighborhood Greenway
- Chinatown/International District, Little Saigon & Judkins Park
- Lake WA Loop
በቅርብ ጊዜ የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች
ብስክሌተኞች |
ደህንነታቸው የተጠበቀ ይበልጥ ምቹ የሆኑ መንገዶች |
ነዋሪዎች |
ይበልጥ ጸጥታ የተሞሉ እና ብዙ ማኅበረሰብ |
አሽከርካሪዎች |
ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ይበልጥ ጸጥታ ያላቸው፣ ይበልጥ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት የሚያስችል መንገድ |
እግረኞች |
ደህንነታቸው የተጠበቀ መንገድ ማቋረጫዎች እና መስተጓጎል የሌለባቸው የእግረኛ መንገዶች |
ዝርዝር ማብራሪያ
Neighborhood greenways በጥሩ መሰረት ላይ የተጀመሩ ሲሆኑ በመጨረሻ ትልቅ ለውጥ የሚያመጡ ትናንሽ ማሻሻያዎችን በየጊዜው ያደርጋሉ። እያንዳንዱ ሰፈር በራሱ ልዩ ነው፣ ሆኖም ግን፣ በሁሉም ቦታ የምናያቸው ጥቂት የጋራ መገለጫ የሆኑ greenway ጸባያት አሉ።
- የተሽከርካሪን ፍጥነት ወደ በሰዓት 20 ማይል መለወጥ
- በየብሎኩ ወደ አንድ የፍጥነት ማስቀነሻ ጉብታ (ሃምፕ) ያክል መጨመር
- ሰዎች መሄድ የሚፈልጉበትን ቦታ ማግኘት እንዲችሉ ለማገዝ ምልክቶችን እና የእግረኛ መንገድ ምልክቶችን ማከል
- በጣም ሥራ በሚበዛባቸው መስቀለኛ እና ተላላፊ መንገዶች ላይ የመንገድ ጠርዝ ቅጥያዎችን፣ ፈጣን ብልጭ ድርግም ባይ ማስጠንቀቂያ መብራቶችን፣ የእግረኛ ማቋረጫ መንገዶችን፣ አካፋዮችን ወይም የትራፊክ ምልክቶችን ማከል
- greenway አቋርጠው በሚያልፉ መንገዶች ላይ የአቁም ምልክቶችን ማከል
- የተስተካከሉ የእግረኛ መንገዶች እና የመኪና መንገዶች እንዲሁም የመንገድ ጠርዝ መሸጋገሪያ አነስተኛ መሬት ላይ ተለጣፊ ድልድዮችን ማከል
እንዴት Neighborhood Greenways መጠቀም እንደሚቻል መመሪያዎች
እግረኞች
- ሁሉንም የትራፊክ ምልክቶችን እና ሲጊናሎችን ይታዘዙ።
- በ greenwayላይለመቆየትምልክቶችንይከተሉ።
ብስክሌተኞች
- ሁሉንም የትራፊክ ምልክቶችን እና መብራቶችን ይታዘዙ።
- የመንገድ ቅድሚያ ላላቸው እግረኞች እና ባለ መኪኖች ቅድሚያ ይስጡ።
- በመስቀለኛ እና ተላላፊ መንገዶች ላይ በጥንቃቄ ይጓዙ።
- በ greenway.ላይ ለመቆየት የብስክሌት የመንገድ ጠርዝ ምልክቶችን ይከተሉ።
ባለ መኪኖች
- እግረኞችን እና ብስክሌተኞችን በጥንቃቄ ይመልከቱ።
- ሁሉንም የትራፊክ ምልክቶችን እና መብራቶችን ይታዘዙ።
- ከመኪና ማቆሚያ ሲወጡና ወደ ዋናው መንገድ ሲገቡ ሁልጊዜ ከኋላ፣ በቀኝ እና በግራ በኩል መኪናዎን ከማንቀሳቅስዎ በፊት ይመልከቱ።
- በመተላለፊያ ወይም መስቀለኛ መንገድ ከመንቀሳቀስዎ ወይም መኪናዎን ከማዞርዎ በፊት ፍጥነት ይቀንሱ።
- በብስክሌት የመንገድ ጠርዝ ምልክቶች ላይ መንዳት ችግር የለውም።
- ብስክሌት የሚነዳውን ሰው በደህንነቱ አስተማማኝ ፍጥነት ቅድሚያ ሰጥተው ይከተሉት እና በሁለታችሁ መካከል ቢያንስ ደህንነቱ አስተማማኝ የሆነ የሶስት ጫማ መተላለፊያ ርቀት እንዳለ እርግጠኛ ከሆኑ ብቻ ይቅደሙት።
- የመኪናዎን በር ሲከፍቱ ጥንቃቄ ያድርጉ። በመጀመሪያ በእግራቸው እየሄዱ ያሉ ወይም ብስክሌት በመንዳት ላይ ያሉ ሰዎች መኖር አለመኖራቸውን ያረጋግጡ።