ደህንነታቸው የተጠበቁ ወደ ትምህርት ቤት የጉዞ መሥመሮች የዘር ፍትዓዊነት ትንታኔ

አጠቃላይ ሐሳብ

Happy kid on bike with adult helping

የስያትል የዘርና የማህበራዊ ፍትህ ንቅናቄ (RSJI) በከተማ አስተዳደር ውስጥ ያለውን ተቋማዊ ዘረኝነትና በዘር ላይ የተመሰረቱ አድሎ ለማስቆም የሚደረገው ከተማ-አቀፍ ጥረት ነው፡፡ የዘር ፍትዓዊነት ቱልኪት (RET) የዘር ፍትዓዊነት ተጽንኦዎችን ለመቅረፍ በምደረገው እንቅስቃሴ ፖሊሲዎችን፣ ንቅናቄዎችን፣ ፕሮግራሞችን እና የባጀት ጉዳዮችን ለመምራት መደበኛ ሂደትንና ጥያቄዎችን ያስቀምጣል፡፡

ደህንነታቸው የተጠበቀ ወዴ ትምህርት ቤት የጉዞ መሥመሮች (SRTS) ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ሲጓዙ እና በብስክለት መጋለብ ቀላልና ደህንነቱ የተጠበቀ የሚያደርግ አከባቢያዊ፣ ሀገራዊ እና ብሔራዊ እንቅስቃሴ ነው፡፡ የስያትል ተራንስፖርት መምሪያ ይህንን ግብ ለማሳካት የስልቶቹን ቅንጅት ይጠቀማል፡

 • ትምህርት: እያንዳንዱ ሰወ እንዴት ደህንነቱን ጠብቆ መጓዝ እንደሚችል ማወቁን ማረጋገጥ
 • ማበረታታት: በትምህርት ቤት ማኅበረሰብ ውስጥ በእግር መሄድን እና ብስክሌት መጋለብን ማበረታታት
 • ምሕንድስና: እንደ የእግረኛ መንገዶች፣ ለደህንነት አስተማማኝ የሆኑ ማቋረጫ መንገዶች፣ እና ብስክሌት ለመጋለብ የተሻሻሉ መንገዶችን የመሳሰሉ የግንባታ ፕሮጄክቶች
 • ሕግ ማስከበር: የትራፊክ ደህንነት ሕጎችን ለማስከበር ከሲያትል የፖሊስ መምሪያ ጋር በአጋርነት መሥራት
 • ምዘና: በእኛ የተጋሩ የደህንነት ግቦች ላይ ያለውን ግስጋሴ ዱካ ክትትል ማድረግ
 • ማብቃት: ለምርጥ ትምህርት ቤቶች ግብዓቶችን ማቅረብ

የዘር ርትዓዊነት ራዕይ

የእኛ ራዕይ የሲያትል ትምህርት ቤት ልጆች ወደ ትምህርት ቤት በእግር የመሄድ እና ብስክሌት የመጋለብ ተሞክሮዋቸውን እንዲጀምሩ ማስቻል ሲሆን እነዚህንም ያካትታል፦

 • መዝናናት
 • የደህንነት ስሜት መሰማት
 • ከእነርሱ ማኅበረሰቦች ጋር ያሉ ግንኙነቶችን ማጠናከር
 • ለቁርስ እና ለትምህርት ወደ ትምህርት ቤት በሰዓቱ መድረስ
 • የተሻሻለ አካላዊ እና የአእምሮ ጤና

በተቋም ደረጃ የሚመራ ዘረኝነትን ለማስቆም እና ይበልጥ ፍትዓዊ የሆነች ከተማን ለመገንባት ሲያትል የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ፣ በእነዚህ ቡድኖች ውስጥ በሚገኙ ተማሪዎች ላይ ትኩረት አድርገናል፦ ጥቁር ማኅበረሰቦች፣ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ማኅበረሰቦች፣ የስደተኛ እና ጥገኝነት ጠያቂ ማኅበረሰቦች፣ የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች፣ መኖሪያ አልባነትን የቀመሱ ወይም የመጠለያ ዋስትና ማጣት ችግር ያጋጠማቸው ሰዎች፣ የተመሳሳይ ጾታ ወሲባዊ ግንኙነት ፈጻሚ ሰዎች [LGBTQ] ማኅበረሰብ እና ልጃገረዶች።

የዘር ፍትዓዊነት ትንታኔ የሥራ ሂደት

የሲያትል ጥቁር ተማሪዎችን በተቻለ ምርጥ መንገድ ማገልገል እንድንችል የደህንነታቸው የተጠበቁ የጉዞ መሥመሮችን እንዴት ማሻሻል እንደምንችል የበለጠ መረዳት እንድንችል ከማኅበረሰቦች ጋር አብረን ተጋግዘን ለመሥራት ጥልቅ ፍላጎት እና ተነሳሽነት አለን። ዘራቸው ከግምት ሳይገባ ሁሉም ተማሪዎች ለጤና፣ ደስታ፣ እና አካዳሚያዊ ስኬት መብት ስላላቸው የሲያትል ወደ ትምህርት ቤት ደህንነታቸው የተጠበቁ ጉዞዎችን ማድረግ ፕሮግራም በተማሪዎች መካከል ይበልጥ ቀጣይነት ያለው በእግር እና በብስክሌት መንቀሳቀስን ለማበረታታት በርትዓዊነት ላይ የተመረኮዘ አቀራረብን በመከተል ላይ ነው።

በ 2015, ደህንነታቸው የተጠበቁ ወደ ትምህርት ቤት የጉዞ መሥመሮች ፕሮግራም የምጀምረው Safe Streets, Healthy Schools and Communities: A Safe Routes to School 5-Year Action Plan for Seattle. ይህ ዕቅድ ደህንነታቸው የተጠበቁ ወደ ትምህርት ቤት የጉዞ መሥመሮች ፕሮግራም ፍትአዊ አገልግሎቶች ማቅረቡን ለማረጋገጥ RETን ለ2017 ፕሮግራማችን ወደ ማመልከት ይመራናል፡፡

ደህንነታቸው የተጠበቁ ወደ ትምህርት ቤት የጉዞ መሥመሮች (SRTS) RET ሂደት የሚሆነው፡

 • ለSRTS ፕሮግራም የዘር ፍትዓዊነት ውጤቶችን ያስቀምጣል
  • በSRTS ፕሮግራም ተጽእኖ የተደረገባቸውን ባለድርሻ አካላት ያሳትፋል
  • ያለውን ዳታ ይተንትኑ
  • እነዚህን የዘር ኢፍትአዊነትን የሚፈጥሩ መነሻ ምክንያቶችን ይለያል
 • የ SRTS ፕሮግራም ከዘር ፍትዓዊነት ውጤቶች ጋር ያለውን ቁርኝት ይገመግማል
  • የበለጠ የዘር ፍትዓዊነትን ለመፍጠር ስልቶችን ያበጃል
  • መፍትኤ ያላገኙ ጉዳዮችን ዶክመንት ያደርጋል
 • የግምገማ መለክያዎችን እና ሪፖርት ማቅረቢያ መንገዶችን ይለያል
 • የRET ሰነድን ከሊደርሽፕ መምሪያ፣ የለውጥ ቡድን እና ህብረተሰቡ አባላቱ መጋራት

በሚቀጥለው ዓመት፣ የኛ የዘር ርትዓዊነት ትንታኔ የሚከናወነው፦

 • ፉል 2017
  • ባለፉት ጊዜያት ማኅበረሰቦች እንዴት አገልግሎት ይሰጣቸው እንደነበረ መረጃን ሰብስቦ ትንታኔ መስጠት
 • ክረምት 2018
  • በውይይቶች እና ዳሰሳ ጥናቶች ተጠቅሞ በእኛ ፕሮግራም ተጽዕኖ ያረፈባቸውን ሰዎች ማሳተፍ
 • ስፕሪንግ 2018
  • የእኛን የዘር ርትዓዊነት ራዕይ ግብ ለመምታት አዳዲስ ስትራቴጂዎችን እና አጋርነቶችን ማዘጋጀት
  • ወደ የእኛ ራዕይ በምናደርገው ግስጋሴ ያለውን ውጤት ለመለካት መለኪያ መስፈርቶችን ለይቶ ማወቅ
 • በጋ 2018
  • ለማኅበረሰቦች መልሶ ሪፖርት ማድረግ

በተማሪዎቻችው ዘር፣ ነገድ እና የቋንቋ ስብጥር ምክንያት ከሚከተሉት ትምህርት ቤቶች ጋር በአጋርነት እየሠራን ነው፦

Wing Luke Elementary
West Seattle Elementary
Dearborn Park Elementary
Concord Elementary
Dunlap Elementary
Bailey Gatzert Elementary
Aki Kurose Middle School
Rainier Beach High School

እርስዎ የሚሉትን መስማት እንፈልጋለን!

በፖስታ ቤት በኩል፣ በመሥመር ላይ (ኦንላይን) እና በሲያትል ዙሪያ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና ማኅበረሰብ ድርጅቶች ውስጥ የኛን ዳሰሳ ጥናቶች ይጠባበቁ።

kids crossing safely in a crosswalk