Play Street ፈቃድ

የፍቃድ ቆጣሪ በጊዜያዊነት መዘጋት

የሰራተኞቻችንን እና የደንበኞቻችንን ጤና እና ደህንነት ለመጠበቅ፣ እና የኮቪድ -19 ተጽእኖን ለመቀነስ በሰኞ ማርች 16፣ 2020 ከህዝብ ጋር ፊት ለፊት የሚያገናኙ የደንበኛ አገልግሎት ቆጣሪዎችን ዘግተናል።ሌላ ማስታውቂያ እስኪሰጥ ድረስ ቆጣሪዎቻችን ተዘግተው ይቆያሉ። ይህ በሲያትል የማዘጋጃ ቤት ህንጻ 23ኛ እና 37ኛ ወለል ላይ ያሉትን የመንገድ ጥቅም እና የትራፊክ እና የመኪና ማቆሚያ ፍቃድ ቆጣሪዎችን ያካትታል። የፍቃድ ማመልከቻዎችን አሁንም እየተመለከትናቸው ነው።

የሲያትል አገልግሎቶች ፖርታልንበመጠቀም የሁሉንም የፍቃድ አይነት ማመልከቻዎችን በኦንላይን ማስገባት ይችላሉ.

ሰራተኞቻችን የማመልከቻ ስልጠና እና ፍቃዶችን ለመስጠት እገዛ ለማድረግ በስልክ ይገኛሉ። ለደዋዮች የትርጉም አገልግሎቶች በነጻ ይሰጣሉ።

ሃሎዊንን በትሪክ (Trick) ወይም በጎዳና ያክብሩ

ትሪክ ወይም ጎዳናዎች እና ዲያ ደ ሙርቶስ በየዓመቱ በበልግ ወቅት ይከሰታሉ። በዚህ አመት ከጥቅምት 28 እስከ ህዳር 5 ድረስ ነው. በዚህ ጊዜ ውስጥ፣ ማህበረሰቡ ሃሎዊንን ወይም ዲያ ደ ሙርቶስን ለማክበር እስከ 10፡00 ፒኤም ድረስ ለTrick or Streets ፍቃድ ማመልከት ይችላል። ከተመቻችሁ፣ ለፍቃድዎ ለማመልከት የሲያትል አገልግሎቶች ፖርታልን ይጠቀሙ። ታዲያ የማመልከቻዎን ግምገማ ቅድሚያ መስጠት እንድንችል በ "የፕሮጀክት ስም" መስክ ውስጥ፣ እባክዎን “ዘዴ ወይም መንገድ፣” ወይም "የሙት ቀን" ብለው ያስገቡ። እስከ ጥቅምት 17 ድረስ ማመልከትዎን ያረጋግጡ።

ከእንግሊዝኛ ሌላ ቋንቋ መጠቀም ከመረጡ ወይም የአገልግሎት ፖርታልን መጠቀም ካልተመቸዎት ለመሳተፍ ይህንን ቀላል የምዝገባ ቅጽ ይጠቀሙ ወይም ለመመዝገብ (206) 684-7623 ይደውሉ። አስተርጓሚዎች በነጻ ሊረዱዎት ይችላሉ።

የጨዋታ መንገዶች ማህበረሰብን ለመገንባት እና ጎረቤቶችዎ ጋር ለመተዋወቅ ደስ የሚልና ቀላል መንገድ ነው። ከብሎክ ፓርቲ በተለየ የጨዋታ መንገዶች ቢበዛ በሳምንት 12 ሰአት ለ3 ቀናት በሳምንት ድረስ በተደጋጋሚ መዘጋጀት ይችላሉ። የጨዋታ መንገዶችን በከተማው ባሉየውስጥ ለውስጥ መንገዶች ውስጥ ማዘጋጀት ይችላሉ - ልክ ከእርስዎ ቤት ውጪ ላይም ማድረግ ይችላሉ። ከሁሉም በላይ ፍቃዱ በነጻ ነው።

እነዚህን ቀላል ደረጃዎች ብቻ ይከተሉ:

ደረጃ 1: መጀመር

የጨዋታ መንገድዎየሚከተለውን እንደሆነ እርግጠኛይሁኑ:

  • ለሁሉም ህዝብ ነጻ እና ክፍት እንደሆነ
  • ከአንድ ቅያስ ርዝመት ያልበለጠ እና መስቀለኛ መንገድን የማያካትት
  • የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ላይ። የመንገዶን አይነትእዚህ ጋር ማግኘት ይችላሉ
    • በመንገዱ መሃል ላይ መስመር ከሌለ—በነጠብጣብ ወይም ቀጥ ያለ—በአብዛኛውየሰፈር መንገድ ሊሆን ይችላል.
    • ከላይ የተያያዘው ካርታ የሰፈር መንገዶችን በግራጫ እናዋና መንገዶችን ደግሞ በሌላ መንገድ ያሳያሉ
  • አውቶብሶች የሚሄዱበት ወይም የድንገተኛ መኪኖች መንገድ ላይ መሆን የለበትም
  • ማዘጋጀት/ማጽዳትን ጨምሮ እንዲካሄድ የታቀደው ከ9:00 AM – እና እስኪመሽ ድረስ (ወይም እስከ 9:00 ድረስ የሚመሸው ከዚህ አልፎ ከሆነ)።

የፕሮግራሙን ዝግጅት በሚያቅዱበት ጊዜ:

  • የድንገተኛ ተደራሽነት ካስፈለገ መንገድ ላይ ያሉት የጨዋታ እቃዎቹ ቶሎ ለማንቀሳቀስ ቀላል መሆን አለባቸው።
  • ሻጮች፣ የምግብ መኪኖች፣ ጊዜያዊ መድረኮች፣የሚነጥሩ ቤቶች፣ ወይም ሌሎች መዋቅሮች በዚህ ፍቃድ ስር የተፈቀዱ አይደሉም።

ደረጃ 2: ጎረቤቶችዎን ያሳትፉ

ማህበራዊ ርቀትና ሌሎች የኮቪድ-19 የደህንነት መመሪያዎችን በአእምሮ ውስጥ በመያዝ ለፍቃድ ከማመልከትዎ በፊት ከጎረቤትዎ ጋር እንዲነጋገሩ እናበረታታለን። በቅድሚያ ከጎረቤትዎ ጋር መተባበር በተመሳሳይ ቀን የታቀደ ወደ መንገድዎ ተጨማሪ መኪኖች የሚያመጡ ጎብኚዎች ወይም የግንባታ ፕሮጀክት ሊኖራቸው ስለሚችል ከሌላ ጎረቤት ጋር የማይጋጭ ቀን ለመምረጥ ሊረዳዎ ይችላል።

ፕሮግራምዎን ስኬታማ ለማድረግ ሊረዱ የሚችሉ በጎ ፍቃደኛ ሰዎችን መለየትም ይችላሉ። ጎረቤቶችዎን ለማሳወቅ ሙሉ በሩን የሚሸፍን ተንጠልጣዮችን እና በራሪ ወረቀቶችን መጠቀም ይችላሉ።

ጎረቤትዎችዎን በኢሜይል ወይም በኦንላይን ለማግኘት ካቀዱ መጠቀም የሚችሉት ኢሜይል ወይም ልጥፍ ናሙና እዚህ ጋር አለ:

የኢሜይል ወይም ልጥፍ ናሙና

ሰላም!

ለ Seattle Department of Transportation ለተወሰነ ከቤት ውጪ ጨዋታ እናመዝናኛ መንገዳችንን ለመዝጋት የጨዋታ መንገድ ፍቃድ እንዲሰጠን እያመለከትን ነው! የተሳታፊዎች ማህበራዊ ርቀት እና ደህንነት እንዲጠበቅ የህብረተሰብ ጤና እናየስቴት መመሪያዎችን ለመከተል አቅደናል። የመንገዱ መዘጋት አልፎ የሚሄድ የትራፊክ እንቅስቃሴን ብቻ ይገድባል። ሁሉም አካባቢያዊ እንቅስቃሴዎች፣ ጎረቤቶች፣ ጎብኚዎች፣ አቅራቢዎች እና የድንገተኛ መኪኖችን ጨምሮ፣ መንገዱን አሁንም መጠቀም ይችላሉ። ከ(ቀን) ጀምሮ እና በ(ቀን) የሚያልቅ ከ(የሚጀመርበት ሰአት) እስከ (የሚያልቅበት ሰአት) (ቀን/የሳምንት ቀናትን) ለመጠየቅ እያሰብን ነው።

ማመልከቻችንን ከማስገባታችን በፊት ስለዚህ ሃሳብ ምን እንደሚያስቡና መመልስ የምንችላቸው ጥያቄዎች ካልዎት ለማወቅ እንወዳለን። እባክዎ ስለዚህ ነገር ማንኛውም ጥያቄዎች ወይም ስጋቶች ካልዎት በ(ቀን) ያሳውቁን። በ (ኢሜይል አድራሻ እና/ወይም ስልክ ቁጥር እኛን ማግኘት ይችላሉ።

እናመሰግናለን!

ደረጃ 3: ለነጻ ፍቃድዎ ያመልክቱ

ከመጀመሪያው ፕሮግራምዎ በትንሹ 14 ቀናት ቀደም ብለው ማመልከቻዎን ለማስገባት ይሞክሩ።ለማመልከት ዝግጁ ሲሆኑ በ 206-684-7623 ይደውሉልን። ሰራተኞቻችን ለፍቃድ እንዲያመለክቱ በነጻ ይረዱዎታል። ለደዋዮች ትርጉም በነጻ አለ!

ደረጃ 4: መንገዱን ለመዝጋት ይዘጋጁ

ለተዘጋው መንገድዎ መሰናክሎች እና ምልክቶችን ያስቀምጡ። በተገቢው ቦታዎች ላይ መሰናክሎችና ምልክቶችን እንዲያስቀምጡ ለመርዳት ቴምፕሌቶችን አዘጋጅተናል።

ስለ መሰናክሎች መሰረታዊ ነገር

  • በዘጉት መንገድ መጨረሻዎች ላይ ከ6’ በላይ ያልተለያዩ መሰናክሎችን ያዘጋጁ እና በቀጭን ረዥም ወረቀት ወይም በገመድ ያገናኙዋቸው።
  • ሰዎች መንገዱን ለማቋረጥ እንዲቀላቸው ለማድረግ መሰናክሎቹን ከእግረኛ መሄጃ ጀርባ ያስቀምጡዋቸው።
  • ከዋና መንገድ ቀጥሎ ከሆነ ያሉት አይነት 3 መሰናክሎችንን መጠቀም አለብዎት(ፈጣን የኢንተርኔት ፍለጋ አይነት 3መሰናክሎችን) የሚያከራዩ የተወሰኑ ቦታዎችን ያሳይዎታል።
  • ከውስት ለውስጥ መንገድ ቀጥሎ ከሆነ ያሉት አይነት 2 መሰናክሎችን ወይም የግል ቆሻሻ መጣያዎች ወይም 3 ጫማ ርዝመት እና 2 ጫማ ስፋት ያላቸው የቤት እቃዎችን የመሳሰሉ የቢት ውስጥ እቃዎችን መተቀም ይችላሉ።
  • የአይነት 2 እና የአይነት 3 በቴምፕሌታችን(ቶቻችን) ላይ ከላይ የሚገኙ መሰናክሎችንምሳሌዎችን ይመልከቱ

ምልክቶችንም እንዲሁ!

  • ”የተዘጋ መንገድ” የሚል ምልክትን በመንገዱ መሃል ላይይትከሉ።
  • የሚፈለገው “የተዘጋ መንገድ” የሚለው ምልክት 36″ x 24″ ይለካል። እራስዎ ወይም በፕሪንት ሱቅ ፕሪንት ማድረግ የሚችሉት የምልክቱ PDF ቨርዢን እዚህ አለ። በፕሪንት ሱቅ ፕሪንት የማያደርጉት ከሆነና በዚህ መስፈርት ፕሪንት የሚያደርግ ፕሪንተር ከሌልዎት ይህን PDFአሁንም ፕሪንት ማድረግ ይችላሉ፤ ነገር ግን ምልክቱን ማገጣጠም አለብዎት። እዚህ ጋርለመገጣጠም ምልክቱን እንዴት ፕሪንት እንደሚያደርጉት የሚያሳዩ መመሪያዎችን ማግኘት ይችላሉ።
  • የ  King County Public Health ምልክቶችን በተዘጋው መንገድ ሁለቱም መግቢያዎች ላይ ይለጥፉ።
  • መንገዱ ለምን እንደተዘጋ ለሌሎች የሚያሳውቁ መረጃ የሚሰጡ ምልክቶችንፕሪንት ያድርጉ።
  • ምልክቶቹ በትንሹ አንድ ጫማ ከመንገድ ደረጃው ከፍ ብለው ለሹፌሮች በቀላሉ እንዲታዩ ተደርገው ከመሰናክሉ ጋር መለጠፍ አለባቸው።

ለመንገድዎ ትክክለኛ መሰናክሎችን ወይም ምልክቶችን ለማግኘት እርዳታ ከፈለጉ እገዛ መስጠት እንችላለን። ተጨማሪ ለማወቅ እባክዎ በ 206-684-7623 ይደውሉልን። የትርጉም አገልግሎቶች በነጻ ይገኛሉ!

ደረጃ 5: መንገድዎን ደህንነቱን ጠብቀው ይዝጉ እና ይዝናኑ!

ስለ ልጆችዎ እና ጓደኞችዎ ደህንነት የሚጨነቁ ከሆነ መዝናናት ከባድ ነው፤ ስለዚህ ከመጀመርዎ በፊት መንገዱን መዝጋትዎን እርግጠኛ ይሁኑ! መሰናክሎችዎን እና ምልክቶችዎን ያዘጋጁ። መሰናክሎቹን የሚቆጣጠረው አዋቂ(ዎች) ማን እንደሆኑ ይስማሙ። ለአካባቢያዊ የትራፊክ እንቅስቃሴ መሰናክሎቹን በፍጥነት ለማንቀሳቀስ በትንሹ አንድ አዋቂ ሁለቱም መሰናክሎች እና እዛው ቦታ ላይ መታየት አለበት። ያስታውሱ -- ወደ ተዘጋው መንገድ አካባቢያዊ ተጠቃሚዎች፣ አቅራቢዎች እና ድንገተኛ መኪኖች መግባት ተፈቅዶላቸዋል። የፕሮግራሙ ስኬታማነት እና የጎረቤቶችዎ ደህንነት የሚወሰነው ለፍላጎቶቻቸው አዘጋጆቹ ባላቸው ንቃት እና ምላሽ ነው።

20-ጫማየእሳት መስመር ሁልጊዜ መጠበቅ አለበት፤ ስለዚህ መንገዱ ላይ በቀላሉ የሚንቀሳቀሱ እቃዎች ብቻ ናቸው መሆን ያለባቸው።

በቀላሉ የማይንቀሳቀሱ ማንኛውም ትልቅ እቃዎች በመንገዱ ውስጥ ወይም በእግረኛ መሄጃ ላይ አይፈቀዱም። በዚህ ፍቃድ ስር የሚነጥሩ ቤቶች የማይፈቀዱት ለዚህ ነው።

እሺ፣ ለመዝናናት ጊዜው አሁን ነው!

ደረጃ 6: ያጽዱ እና መሰናክሎቹን ያንሱ

የጨዋታ መንገድበሚያልቅበት ጊዜ እባክዎ መንገዱ ከጨዋታ እቃና ከማንኛውም ተግባራት ቆሻሻ ባዶ መሆኑን ያረጋግጡ። ማጽዳት ከተሳተፉት ሁሉም ልጆች ጋር የሚጋሩት ትልቅ ተግባር ነው! መሰናክሎቹን ማንሳትዎን እና ለሚያልፉ የትራፊክ እንቅስቃሴዎች ክፍት ማድረግዎን እርግጠኛ ይሁኑ።

ምን በጥሩ ሁኔታ እንደተካሄደ፣ የሚሻሻሉ ሃሳቦችን፣ ወይም የፕሮግራምዎ ፎቶዎችን ማጋራት ከፈለጉ ከእርስዎ ለመስማት እንወዳለን። በ publicspace@seattle.gov ኢሜይል ለማድረግ ወይም በ @SeattleDOT ትዊተር ላይ እኛን ለማያያዝ ነጻነት ይሰማዎት!

Transportation

Greg Spotts, Director
Address: 700 5th Ave, Suite 3800, Seattle, WA, 98104
Mailing Address: PO Box 34996, Seattle, WA, 98124-4996
Phone: (206) 684-7623
684-Road@seattle.gov

Newsletter Updates

Subscribe

Sign up for the latest updates from Transportation

The Seattle Department of Transportation (SDOT) is on a mission to deliver a transportation system that provides safe and affordable access to places and opportunities for everyone as we work to achieve our vision of Seattle as a thriving, equitable community powered by dependable transportation.