ከቤት ማስወጣት ድጋፍ (Eviction Assistance)

English
አማርኛ
繁體中文
한국어
Soomaali
Español
Tiếng Việt

የሲያትል በኮቪድ-19 የማስወጣት እገዳ የካቲት 28 ቀን 2022 ያበቃል።

አሁን እርዳታ ያግኙ

ከቤት ማስወጣት ክልከላዎች፣ ኃላፊነቶች፣ እና ለተከራዮች የተለመዱ መልሶች

ከቤት ማስወጣት ክልከላዎች፣ ኃላፊነቶች፣ እና ለአከራዮች የተለመዱ መልሶች

 

ይህ ለተከራዮች፣ ለአከራዮች እና ለንብረት ሥራ እስኪያጆች ምን ማለት ነው?

በእገዳው ሥር፣ ከቤት ማፈናቀሉ ለጤና እና ለደህንነት የማይቀር ለሚባል ስጋት ባለባቸው ሁኔታዎች ብቻ ተወስነው ነበር። አንዴ እገዳው ካለቀ፣ ተከራዮች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ጥቂት ከቤት የማፈናቀል ክልከላዎች መቀጠል ይኖራቸዋል። አከራዮች የተወሰኑ ከቤት ማፈናቀሎችን መቀጠል ይችላሉ ነገር ግን ስለ ሂደቱ መሠረታዊ ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል። አንዲሁም አከራዮች የተፈቀዱትን እና ያልተፈቀዱትን ማወቅ አለባቸው። የሲያትል ከተማ መንግስት እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ተከራዮች እና አከራዮች መብቶቻቸውን፣ ኃላፊነታቸውን እና ያሉትን ግብእቶች እንዲረዱ መርዳት ይችላሉ።

 

እርዳታ ያግኙ

አብዛኛዎቹ እነዚህ ግብእቶች የሚገኙት በእንግሊዝኛ ብቻ ነው። ነገር ግን፣ ደውለው አና አስተርጓሚ ሊጠይቁ ይችላሉ።

የቤቶች ፍትህ ፕሮጀክት (Housing Justice Project)

በኪንግ ካውንቲ ውስጥ ከቤት ማስወጣት ለሚጠብቃቸው ተከራዮች ነፃ የሕግ ድጋፍ

ለእገዛ 2-1-1 ይደውሉ

በኪራይ እርዳታ፣ በመጠለያ፣ በህጋዊ የድጋፍ ምሪቶች፣ በመኖሪያ ቤት እርዳታ እና በተጨማሪ ሌሎችም ሊረዱ ከሚችሉ አገልግሎቶች ጋር ይገናኙ።

የኪንግ ካውንቲ ከቤት ማስወጣት መከላከል ፕሮግራም

በኮቪድ-19 ችግሮች ምክንያት ለቤት ኪራይ እና ለፍጆታ ክፍያዎች እርዳታ ያግኙ።

 

ከቤት ማስወጣት ክልከላዎች፣ ኃላፊነቶች፣ እና ለተከራዮች እና ለአከራዮች የተለመዱ መልሶች

ለተከራዮች

ተጨማሪ ጥበቃዎች
(ከእነዚህ ግብዓቶች አብዛኛዎቹ የሚገኙት በእንግሊዝኛ ብቻ ነው።)

እገዳው ካለቀ በኋላ ሲያትል ብቁ ለሆኑ ተከራዮች ተጨማሪ ከቤት የማስወጣት ጥበቃ ይሰጣል። አንዳንድ ምሳሌዎች:

  • ከኮቪድ ጋር የተያያዘ መክፈል አለመቻል: ከመጋቢት 3 ቀን 2020 አና እገዳው ካለቀ በኋላ 6 ወራት ድረስ መካከል ያለእግባብ/ በጥፋተኝነት የተከማቸ የቤት ኪራይ ተከራዮችን ከቤት ማስወጣት ይገድባል።
  • የትምህርት ዓመት ወቅት ከቤት የማስወጣት ክልከላዎች: በሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች የቀን አቆጣጠር መሠረት ከመስከረም እስከ ሰኔ ድረስ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ተማሪዎች ላሏቸው ቤተሰቦች (በሕፃናት እንክብካቤ ውስጥ ያሉ ልጆችን ጨምሮ)፣ አስተማሪዎችን እና የትምህርት ቤት ሰራተኞችን ከቤት ማስወጣትን ይገድባል።
  • የሕግ እማካሪ የማግኘት መብት: በሲያትል ያሉ ጠበቃ መግዛት/ መያዝ የማይችሉ ከቤት ማስወጣትን የተጋፈጡ ተከራዮች በ ቤቶች ፍትህ ፕሮጀክት (Housing Justice Project (HJP) በኩል ነፃ የሕግ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።
  • ከቤት የመልቀቂያ ማስጠንቀቂያ ካገኙ፣ በሲያትል መከራየት የእርዳታ መስመር በ (206) 684-5700 ይደውሉ። የተሰጠዎ ማስጠንቀቂያ የከተማውን ህግ የሚያከብር መሆኑን አንገመግማለን እና ወደ ግብአቶች እንመራዎታለን። ሲደውሉ፣ ነጻ የትርጉም አገልግሎት መጠየቅ ይችላሉ።

ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች

  1. የሲያትል ከቤት የማፈናቀል እገዳ አበቃ?
    ከቤት የማፈናቀሉ እገዳ በየካቲት 28 ቀን 2022 ያበቃል።
  2. እገዳው የካቲት 28 ሲያልቅ ምን ይሆናል?
    የሲያትል አከራዮች በህጋዊ መንገድ ከቤት የማስለቀቂያ ማሳወቂያዎችን ለተከራዮቻቸው መላክ/ መስጠት እና ከቤት ማስለቀቅን (ብዙውን ጊዜ "ህጋዊ ያልሆኑ ታሳሪዎች" ይባላሉ) በፍርድ ቤት እንዲቀጥሉ ይፈቀድላቸዋል። ተከራዮች ጠበቃ መግዛት/ መያዝ ካልቻሉ አሁንም ብዙ ከቤት ማስለቀቂያ ጥበቃዎች እና የህግ አማካሪ የማግኘት መብት አላቸው።
  3. ባለንብረቱ "በ14-ቀን ክፍያ ወይም ከቤት የመልቀቅ" ማስጠንቀቂያ ወይም ሌላ ዓይነት ማስታወቂያ ቢያቀርብልኝ ምን ማድረግ አለብኝ?
    በመጀመሪያ፣ የሲያትል ከተማን በሲያትል የቤት መከራየት የእርዳታ መስመር (206) 684-5700 ይደውሉ እና ከአከራይዎ ማስጠንቀቂያ እንዳለዎት ያሳውቁ። እባክዎ ለአንድ የተወሰነ ቋንቋ አስተርጓሚ ካስፈለግዎ ለኦፕሬተሩ ይንገሩ። አስፈላጊ መረጃዎችን ሁሉ ያካተተ መሆኑን ለማረጋገጥ ማስጠንቀቂቂያውን እንገመግመዋለን። ትክክል ካልሆነ፣ አከራዩን እንዲሰርዘው እንጠይቃለን። ትክክል ከሆነ፣ ለህግ ምክር ወደ የቤቶች ፍትህ ፕሮጀክት (Housing Justice Project (HJP) እንልክልዎታለን።
  4. የቤት ኪራይ መክፈል ካልቻልኩኝ ምንም ዓይነት የክፍያ ዕቅዶች ይኖራሉን?
    አከራዮች ከሚያቀርቡት ማንኛውም በ14-ቀን ውስጥ ክፍያ ወይም ከቤት ልቀቅ ማስጠንቀቂያ ጋር መክፈል የሚቻል የክፍያ እቅድ እንዲያቀርቡልዎ ይጠበቅባቸዋል። የቤት ኪራይ ለመክፈል ዘግይተው ከሆነ፣ የኢኮኖሚያዊ ችግርዎ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተጽዕኖ ምክንያት መሆኑን ማረጋገጥ ከቻሉ ከቤት ለማስወጣት መከላከያ አለዎት። የቤቶች ፍትህ ፕሮጀክት (HJP) በመብቶችዎ ላይ ምክር ሊሰጥዎት እና በሂደቱ ሊመራዎት ይችላል።
  5. ሌሎች ከቤት ማስወጣት ጥበቃዎች/ መከላከያዎች አሉ?
    አዎን፣ አንድ ባለንብረት የኪራይ ውልዎን ለማቆም ወይም የኪራይ ውልዎን ማደስ ላለመቀበል ከ16 ልዩ ምክንያቶች አንዱ እንዲኖርበት የሚጠይቅ፣ በሲያትል ውስጥ ያሉ የኪራይ ስምምነቶች ሁሉም የሚተዳደሩት በ ፍትሀዊ መነሻ ያለው ከቤት ማስወጣት ድንጋጌ ነው። አከራይዎችዎ ለእርስዎ የሚሰጥዎት ማስጠንቀቂያውን የመደግፍ ልዩ መንስኤ/ዎችን እና እውነታዎችን መግለጽ አለበት። በተጨማሪም፣ ሲያትል በክረምት ወቅት (ከታሕሣስ 1 እስከ መጋቢት 1) ገቢያቸው ለሚያበቃቸው ተከራዮች ተፈፃሚ የሚሆን ከቤት የማስወጣት መከላከያ አለው። ይህ ከቤት የማስወጣት መከላከያ በሲያትል የትምህርቱ ዘመን (ከመስከረም እስከ ሰኔ) ልጆች ትምህርት ቤት ውስጥ ላሏቸው ቤተሰቦችም (ከመዋዕለ ሕፃናት እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ይጨምራል) እንዲሁም ለትምህርት ቤቶች ሰራተኞች እና ተቀጣሪዎችም አለ።
  6. ለቤት እየተባረርኩ ከሆነ፣ ነገር ግን ጠበቃ መግዛት/ መያዝ ካልቻልኩ ምን ማድረግ አለብኝ?
    ሲያትል ለጠበቃ/ ለሕግ ምክር የሚሆን መብት አለው፣ ይህ ማለት ማንኛውም ተከራይ "መጥሪያዎች እና የቅሬታ መንሾ" የተሰኙ የፍርድ ቤት ሰነድ ቀርቦለት (እንዲሁም "የማስወጣት ክስ" በመባልም ይታወቃል) እና ጠበቃ መግዛት/ መያዝ የማይችል ከሆነ ነፃ የህግ አማካሪ የማግኘት መብት አለው። እያንዳንዱ ተከራይ ከቤት የማስወጣት መከላከያ ጠበቃ ማግኘቱ እንዲረጋገጥ ከተማው ከ ከቤቶች ፍትህ ፕሮጀክት (HJP) ጋር በጋራ ይተባበራል።

 

ለአከራዮች

ተጨማሪ ድጋፍ
(ከእነዚህ ግብዓቶች አብዛኛዎቹ የሚገኙት በእንግሊዝኛ ብቻ ነው።)

ሲያትል ለአከራዮች በማፈናቀሉ ሂደት የረዥም ጊዜ መስፈርቶች አሏት፣ እና ወቅታዊ ህጎችን ለመረዳት እንደ ጠበቃ ካሉ ባለሞያ ወይም የአከራይ ድርጅት ከመሳሰሉ ጋር እንዲማከሩ በጥብቅ ይመከራል።

 ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች

  1. ከቤት የማፈናቀሉ እገዳ ሁሉንም ከቤት ማስወጣትን ይከለክላል?
    የኮቪድ-19 ከቤት ማስወጣት እገዳ ተከራይ ለጤና እና ለደህንነት የማይቀር ስጋት ካልፈጠረ በስተቀር ሁሉንም ማፈናቀል ይከለክላል። ይህ የውል ማቋረጫ ማሳወቂያዎችን መስጠት ወይም ከየካቲት 28 ቀን 2022 በኋላ ከቤት ለማስወጣት ማስፈራራትን ይጨምራል።
  2. ለጤና እና ለደህንነት የማይቀር ስጋት ተብሎ የሚወሰደው ምንድን ነው?
    ተከራዩ በባለንብረቱ፣ ወይም በህንፃው ውስጥ ባሉ ሌሎች ተከራዮች ጤና እና ደህንነት ላይ ከባድ አደጋ እንደሚያመጣ ምክንያታዊ እርግጠኝነት ሲኖር የማይቀር ስጋት አለ። አንድ ነገር የማይቀር ስጋት መሆን አለመሆኑ በመጨረሻ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ነው። ለወንጀል ድርጊት በ3-ቀን የማቆም ማስታወቂያ ካወጡ፣ ደጋፊ መረጃዎችን የያዘ ቅጂ በጊዜው ለመገምገም እና ለመመዝገብ ወደ ሲያትል የግምባታ እና ምርመራዎች መምሪያ (SDCI) መላክ አለቦት።
  3. እገዳው ሲያልቅ ምን ማድረግ እችላለሁ?
    ማስጠንቀቂያዎችን በሕጉ ለተከራዮችዎ መስጠት እና ከቤት ማስወጣቱን መቀጠል ይችላሉ። የርስዎን ከቤት ማስወጣት በሲያትል ፍትሀዊ መነሻ ያለው ከቤት ማስወጣት ድንጋጌ ስር መፈቀዱን ያረጋግጡ፣ እና የተጠየቁ መረጃዎች ሁሉ እና የማስጠንቀቂያዎ ላይ ቋንቋ መካተት አለበት አለዚያ ሊሰረዝ ይችላል። በማስለቀቅ ሂደት ውስጥ ብቁ የሆኑ ተከራዮች ከቤት ማስወጣት መከላከያዎች ተብለው የሚጠሩ ተጨማሪ ከለላዎችን ሊያነሱ ስለሚችሉት ማወቅ አለቦት። ማንኛውንም ከቤት የማስወጣት እርምጃ ከመቀጠልዎ በፊት ከጠበቃ ጋር እንዲያማክሩ እንመክርዎታለን።
  4. ባለመክፈል ምክንያት አሁን ማስወጣት እችላለሁ?
    ለተከራይዎ በ14-ቀን ውስጥ መክፈል ወይም የመልቀቅ ማስጠንቀቂያ መስጠት ይችላሉ። ነገር ግን፣ ተከራይዎ ክፍያ ያልተፈጸመው የገንዘብ ችግራቸውን ወረርሽኙ ባስከተላቸው ተፅዕኖዎች ምክንያት ብለው ካረጋገጡ ከቤት ማስወጣት መከላከያ በፍርድ ቤት ሊያነሱ ይችላሉ። ላለፈው ውዝፍ ኪራይ የክፍያ እቅድ አቅርቦትን ከማስጠንቀቂያው ጋር ማካተትዎን ያስታውሱ። እንዴት እንደሚቀጥሉ የህግ አማካሪን ያማክሩ።
  5. የኮቪድ-19 እገዳው ሲያበቃ በቅርቡ የተላለፉት የክረምት ከቤት የማፈናቀል እና የትምህርት አመት ከቤት የማስወጣት ክልከላዎች ለአከራዮች ምን ማለት ነው?
    ከቤት ማስወጣት ክልከላው በተለየ የትምህርት አመት እና የክረምቱ ከቤት የማስወጣት መመሪያዎች ባለቤቱ የመልቀቂያ ማስታወቂያ ከማውጣት ወይም ህገወጥ እስረኛ (ከቤት የማፈናቀል ክስ) ከማቅረብ አይከለክልም። ብቁ የሆኑ ተከራዮች በጣም ቀዝቃዛ በሆነው የአየር ሁኔታ ወራት እና በሲያትል የትምህርት አመት ወቅት ከቤት የማስወጣት መከላከያን ማንሳት ይችላሉ።
  6. እነዚህን ከቤት የማስለቀቂያ መከላከያዎችን ማንሳት ብቁ የሆነው ማነው?
    • በወረርሽኙ ወቅት የቤት ኪራይ ያልከፈሉ ተከራዮች።
    • በክረምት ወራት (ከታህሳስ 1 እስከ መጋቢት 1) ለመልቀቅ የተጋለጡ ገቢያቸው የሚያሟላላቸው ተከራዮች።
    • ልጆች ያሏቸው ቤተሰቦች (ከመዋዕለ ሕፃናት እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት)፣ በሲያትል የትምህርት ዘመን ወቅት (ከጥር - ሰኔ) የትምህርት ቤት ሰራተኞች እና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች።
  7. እነዚህን ሁሉ የከተማ ኪራይ ደንቦችን እንዲረዳ ለእርዳታ የት መሄድ እችላለሁ?
    ለቴክኒክ ድጋፍ የሲያትል ከተማ በሲያትል ለመከራየት የእርዳታ መስመርን በ (206) 684-5700 ይደውሉ። እባክዎ ለአንድ የተወሰነ ቋንቋ አስተርጓሚ ካስፈለግዎ ለኦፕሬተሩ ይንገሩ። ማንኛቸውንም ጥያቄ ለመመለስ እና በመስፈርቶቹ ዉስጥ ለመመሪያ ዕርዳታ የኛ ሕጉ የመከበሩ ተንታኞች ይገኛሉ። ተጨማሪ የአከራይ ግብዓቶች እዚህ ይገኛሉ፣ (ገጽ በእንግሊዝኛ ብቻ ይገኛል)።

 

ይህ ያልሆነው ቃል: በዚህ ድህረ-ገጽ ላይ የቀረበው መረጃ የህግ ምክር አይደለም እና ለመወከልም የታሰበ አይደለም። በዚህ ድህረ-ገጽ ላይ የሚገኙት ሁሉም መረጃዎች፣ ይዘቶች እና ቁሶች ለአጠቃላይ መረጃ ዓላማዎች ብቻ ናቸው።

Renting in Seattle

Address: 700 5th Ave, Suite 2000, Seattle, WA, 98124
Mailing Address: P.O. Box 34019, Seattle, WA, 98124-4019
Phone: (206) 684-5700
Contact Us

The Seattle Department of Construction & Inspections (SDCI) includes permitting, construction inspections, code compliance and tenant protections, and rental housing registration and inspections.