Amharic - አማርኛ

Tenant Animation - Renting in Seattle
Landlord Animation - Renting in Seattle

የሚገኘው መረጃ ምንድ ነው?

ድህረ ገጹ የሁለቱም ማለትም ተከራዮች እና አከራዮች በኪራይ ሂደት ውስጥ መግባት እና መውጣት  አስመልክቶ ያላቸውን መብቶች እና ኃላፍነቶችን በተመለከተ መረጃ ይሰጣል። ስለ ከተማው ሕጎች፣ አነስተኛ ቤቱ ማሟላት ስላለበት ደረጃዎች እና እርስዎ ወይም እርስዎ የሚያውቁት ሰው በቤት ማግኘት ላይ አድልዎ ሲደረግ ካዩ ምን ማድረግ እንዳለብዎት ይገልጻል።  ከአንድ ሰው ጋር ለመነጋገር ከፈለጉ፣ እርዳታ ከፈለጉ፣ ወይም ስለ ቤት ቅሬታ ማቅረብ ከፈለጉ ለእኛም ሊደውሉ ይችላሉ። 

የትርጉም አገልግሎት ሁልጊዜ ይሰጣል።

ECONOMIC DISPLACEMENT RELOCATION ASSISTANCE ማስታወቂያ:-
ለፋይናንስ እርዳታ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ
የ Economic Displacement Relocation Assistance (EDRA፣ የምጣኔ ሃብታዊ መፈናቀል ዝውውር እርዳታ) ፕሮግራም 10% ወይም ተጨማሪ የቤት ኪራይ ጭማሪ ያገኙ ለገቢ ብቁ ተከራዮች ለማዘዋወር የገንዘብ እርዳታ ለማግኘት እንዲያመለክቱ እድል ይሰጣል። እባክዎ የመልቀቅ እቅድ ካልዎት ብቻ ያመልክቱ።
ጥቅማ ጥቅሙ ምንድነው እና ማነው የሚያቀርበው?
በሲያትል ከተማ አከራዮች የቤት ወጪዎን ቢያንስ 10% ሲጨምሩ ስለዚህ ፕሮግራም ለተከራዮች እንዲያሳውቁ ያስፈልጋል። የ Seattle Department of Construction and Inspections (SDCI፣ የሲያትል የግንባታ እና ፍተሻ ክፍል) ከባለንብረቱ ገንዘብ ይሰበስባል እና ገንዘቡን ብቁ ለሆኑ ቤተሰቦች ያከፋፍላል። ከተፈቀደ፣ ተከራዮች ከወርሃዊ የቤት ወጪ እስከ 3 እጥፍ የሚደርስ ነጠላ ክፍያ ከከተማው ይደርሳቸዋል።

የተተረጎሙ ማቴሪያሎች፡

ይህ ድኅረገጽ ስለ ኪራይ ሕጎች፣ የተከራይ ከላላዎች፣ ፍትሐዊ የሆነ የቤት ሕጎች፣ መሰረታዊ አገልግሎቶች፣ እና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን በተመለከተ አጋዥ መረጃዎችን የሚሰጡ ሰነዶችን ይተረጉማል።

ስያትል (Seattle) በሁሉን አቃፊነት እና በእኩልነት ታምናለች።  ስደተኞች እና በመጠለያ ጣቢያ የሚኖሩ መምጣት ይችላሉ።

የከተማ ሠራተኞች ስለ ዜግነት ሁኔታ የማይጠይቅ ሲሆን የስደተኝነት ሁኔታን ሳይመለከት ሁሉንም ነዋሪዎች ያገለግላል።

ዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ ቤት የሚገኝበትን፣ ወደ ቤት ለመግባት እገዛን፣ ሕጋዊ ድጋፍን፣ እና ሌሎች የማኅበረሰብ አስፈላጊ ነገሮችን በተመለከተ እርዳታ ከፈለጉ በ2-1-1 ወይም 1 (877) 211-9274 ላይ ይደውሉ ወይም ወደ win211.org. ድኅረገጽ ይሂዱ።

የአከራይ መረጃ

ቤት ተከራይቶ መግባት

አከራይ መሆን

ቤት መልቀቅ

  

Renting in Seattle

Address: 700 5th Ave, Suite 2000, Seattle, WA, 98124
Mailing Address: P.O. Box 34019, Seattle, WA, 98124-4019
Phone: (206) 684-5700
Contact Us

The Seattle Department of Construction & Inspections (SDCI) includes permitting, construction inspections, code compliance and tenant protections, and rental housing registration and inspections.