ለዝናብ ወቅት መዘጋጀት

ከባድ ዝናብ የጎርፍ መጥለቅለቅን ሊያስከትል ይችላል፣ እና በአንዳንድ የሲያትል አካባቢዎች፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓቱን ሊያጨናንቅ እንዲሁም የፍሳሽ ማስወገጃዎች ሞልተው እንዲፈሱ ሊያደርግ ይችላል።

የሲያትል የህዝብ መገልገያዎች (SPU) የሰራተኛ ቡድኖች የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓታችንን ቁልፍ ክፍሎች በመፈተሽ ለማጽዳት፣ አያያዛቸውን በመጠበቅ እና አስፈላጊውን ጥገና በማከናወን ለሲያትል የእርጥብ አየር ጠባይ ወቅት ይዘጋጃሉ።

በዝናብ አውሎ ንፋሶች ወቅት፣ ይዘጋጁ፣ ደህንነትዎን ይጠብቁ እና መረጃ ያግኙ።

ከዝናብ በፊት

የዝናብ አውሎ ንፋስ መውረጃዎን በጥንቃቄ ከቅጠሎች እና ከቆሻሻ በማጽዳት የጎርፍ መጥለቅለቅን ይከላከሉ።

በሰፈርዎ ውስጥ የዝናብ ኣውሎ ነፋስ መውረጃዎች ከመደፈናቸው በፊት በግቢዎ ውስጥ ያሉ ቅጠሎችን ይጥረጉ/ ይሰብስቡ።

ቅጠሎችን በግቢ የብስባሽ መሰብሰቢያ ውስጥ ያኑሩ፣ ነገር ግን ቆሻሻውን በቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ ያስቀምጡ።

ብዙ ቅጠሎች ካሉዎት፣ የቤተሰብ ደንበኞች በህዳር ወር ውስጥ በያንዳንዱ መሰብሰቢያ ቀን እስከ 10 ከረጢት ተጨማሪ የግቢ ስብሳቢዎችን በነፃ ማውጣት ይችላሉ።

ሲዘንብ

የጎርፍ መጥለቅለቅ ወይም የፍሳሽ ማስወገጃ ችግሮች ካዩ ከሰኞ እስከ አርብ 24 ሰዓት በየቀኑ (206) 386-1800 (የትርጉም አገልግሎት አለ) ይደውሉ።

በከባድ የዝናብ አውሎ ንፋስ ወቅት atyourservice.seattle.govን በመጎብኘት እና SPUን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ።