ርዕስ VI:- የዜጎች መብቶች ህግ

English 正體字 (Traditional Chinese) Español (Spanish)
Af-Soomaali (Somali) አማርኛ (Amharic) 한국어 (Korean)
Tagalog (Tagalog) Tiếng Việt (Vietnamese)

የሲያትል ከተማ የሲቪል መብቶች ህግ ርዕስ VIን ትከተላለች። ይህ ህግ እርስዎን በዘር፣ በቀለም፣ ወይም በብሄራዊ ማንነት ላይ የተመሠረተ በከተማ ፕሮግራሞች ውስጥ፣ በአገልግሎቶች ወይም የፌደራል የድጋፍ ገንዘብ በሚያስገኙ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ከሚያደርስ መድልዎ ይጠብቅዎታል። 

የኛ ቁርጠኝነት

እኛ ሁሉም ሰው በፍትሃዊ አሰራር እና በእኩልነት እንዲስተናገድ ለማድረግ ቆርጠን ተነስተናል። የሲያትል ከተማ በአካል ጉዳተኝነት፣ ጾታ፣ ዕድሜ፣ ጾታዊ ዝንባሌ፣ የፆታ ማንነት፣ የኢሚግሬሽን ሁኔታ፣ የእርግዝና ውጤቶች፣ ሃይማኖት ወይም እምነት፣ ትውልድ ቆጠራ፣ መደብ፣ የጦር ሜዳ አገልግሎት፣ ወይም ወታደራዊ አቋም፣ በአደባባይ ጡት ማጥባትን፣ በሕዝብ ቦታዎች የአገልግሎት እንስሳ መጠቀም ላይ በመመስረት በማንኛቸውም የከተማ ፕሮግራም፣ አገልግሎት፣ መገልገያዎች፣ እና ኮንትራቶች አድልዎ ማድረግን ይከለክላል። 

እርስዎን መድልዎ ካጋጠመ

መድልዎ ደርሶብኛል ብለው ካሰቡ ከእኛ ጋር ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ። እንዴት እንደሚያስገቡ እነሆ:-

ስለ የአካል ጉዳተኝነት መድልዎ ቅሬታዎች ወይም ስለ አሜሪካን የአካል ጉዳተኝነት (ADA) መስተንግዶዎች ለመጠየቅ የ ADA አስተባባሪዎችን ያነጋግሩ:-  

እኛ ለመርዳት እዚህ አለን። ስለ ከተማዋ ፀረ አድልዎ ህጎች እና የርዕስ VI አንቀጽ ማክበርን በተመለከተ ለበለጠ መረጃ የሲያትል የሲቪል መብቶች ጽሕፈት ቤትን ያነጋግሩ። እኛ የትርጉም እና የማስተርጐም አገልግሎቶችን በነጻ እናቀርባለን። 

ርዕስ VI የቅሬታ ሂደት

የሲያትል ከተማ በእርስዎ ዘር፣ ቀለም፣ በብሔራዊ ማንነትዎ ምክንያት አድልዎ የተፈጸመብዎ ሆኖ ከተሰማዎት የሚከተሉትን እርምጃዎች በመከተል ለሲያትል የሲቪል መብቶች ጽሕፈት ቤት (SOCR) ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ:-  

እርምጃ 1:- እኛን ያግኙ

እዚህ በመስመር ላይ ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ፣ ወይም በ (206) 684-4500፣ TTY:- 7-1-1 ይደውሉልን። ያስታውሱ፣ ቅሬታዎች ክስተቱ በተፈጠረ በ180 ቀናት ውስጥ መቅረብ አለባቸው።

እርምጃ 2፡- እንነጋገር

ስለ ሁኔታዎ ለመነጋገር ጊዜ ቀጠሮ እናዘጋጃለን እና ለርዕስ VI ቅሬታ ማቅረብ በቂ መረጃ እንዳለ እናያለን።  

እርምጃ 3፡- ቅሬታውን ማቅረብ

በቂ መረጃ ያለ ከሆነ፣ እርስዎ እንዲፈርሙበት መደበኛ ቅሬታውን እንዲጽፉ እናግዝዎታለን። ከዚያም የሚመለከተውን የሲያትል ከተማ መምሪያ ስለ ቅሬታው እናሳውቃለን።

ግንባታን፣ ጥገናን፣ የጐዳናዎች እንዳሉ እንዲቆዩ ማድረግን፣ የእግረኛ መንገዶችን፣ አውራ ጐዳናዎችን፣ ወይም ድልድዮች እና ከመሬት በታች መተላለፊያዎችን የሚመለከቱ ጉዳዮች በፌዴራል የአውራ ጐዳናዎች አስተዳደር ይገመገማሉ።

እርምጃ 4፡- ቅድመ መፍትሄ

እርስዎ እና የሲያትል ከተማ መምሪያ ቅሬታውን በመወያየት በቅድሚያ ለመፍታት/ ተቀዳሚ መፍትሄ መሻት ላይ የመሳተፍ እድል ይኖራችኋል። ተቀዳሚ መፍትሄ መሻት በሁሉም ወገኖች የፈቃደኝነት ተሳትፎ ያስፈልገዋል።

እርምጃ 5፡- ምርመራ  

ተቀዳሚ መፍትሄ መሻት እርምጃ የሚሠራ ካልሆነ፣ አንድ መርማሪ ቅሬታው በቀረበ በ100 ቀናት ውስጥ መረጃ ይሰበስባል፣ ቃለ መጠይቆች ያደርጋል፣ እና እውነታዎቹን ይገመግማቸዋል።

እርምጃ 6፡- ውሳኔ  

የርዕስ VI ጥሰትን ለማሳየት ሲያትል የሲቪል መብቶች ጽሕፈት ቤት (SOCR) በቂ ማስረጃ ካለ ይወስናል።

ግንባታን፣ ጥገናን፣ የጐዳናዎች እንዳሉ እንዲቆዩ ማድረግን፣ የእግረኛ መንገዶችን፣ አውራ ጐዳናዎችን፣ ወይም ድልድዮች እና ከመሬት በታች መተላለፊያዎችን የሚመለከቱ ምርመራዎች በፌዴራል የአውራ ጐዳናዎች አስተዳደር ይገመገማሉ። እንዲሁም የርዕስ VI ቅሬታን በቀጥታ ለአሜሪካ መጓጓዣ መምሪያ፣ ለሲቪል መብቶች የፌደራል የሕዝብ ማመላለሻ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት የማቅረብ እድል አማራጭ ደግሞ ይኖርዎታል፡

እኛ እምንሰራው 

የሲያትል ከተማ የሚከተሉትን አገልግሎቶች ይሰጣል:- 

ፍትሃዊ እኩልነት ተደራሽነት በሁሉም ፕሮግራሞቻችን፣ አገልግሎቶቻችን፣ እና ኮንትራቶቻችን ውስጥ አድልዎ መከላከል። 

የአካል ጉዳተኝነት መዳረሻ አካል ጉዳተኝነት ያላቸው ፕሮግራሞቻችንን፣ አገልግሎቶቻችንን እና እንቅስቃሴዎቻችንን ማግኘት/ መድረስ እና ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ያረጋግጡ። 

የቋንቋ መዳረሻ እርስዎ በመረጡት ቋንቋ መረጃ እና አገልግሎቶችን ማቅረብ። 

የተፈጥሮ አካባቢ ፍትህ በተፈጥሮ አካባቢያዊ ኢፍትሃዊነት እጅግ በጣም ለተጎዱ ማህበረሰቦች ጤናን፣ የተፈጥሮ አካባቢን፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውጤቶችን ማሻሻል።

ኮንትራት የመስጠት ፍትሃዊ እኩልነት ከሴቶች እና በቁጥር ዝቅ ያሉ ክፍሎች-ባለቤትነት ያላቸው ንግዶች (WMBE) ጋር ኮንትራት እና ግዢን ማሳደግ። 

የመጓጓዣ እኩልነት በዘር ፍትሃዊ እኩል እና ማህበራዊ ፍትሃዊ የሆነ የመጓጓዣ ስርዓት ለማዳበር ከማህበረሰቦች ጋር መተባበር።

Civil Rights

Newsletter Updates

Subscribe

Sign up for the latest updates from Civil Rights

The Seattle Office for Civil Rights (SOCR) works to advance civil rights and end barriers to equity. We enforce laws against illegal discrimination in employment, housing, public places, and contracting within Seattle.