የንግድ የተከራይ ማሻሻያ ፈንድ

በኮቪድ-19 ለተጎዱ አነስተኛ ንግዶች የንግድ ቦታ ማሻሻያዎችን የበለጠ ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ለማድረግ የሲያትል የኢኮኖሚ ልማት ጽሕፈት ቤት የ$1.9 ሚሊዮን ዶላር መዋዕለ ንዋይ እያደረገ ነው። የንግድ የተከራይ ማሻሻያ ፈንድ ለተከራይ ማሻሻያ ፕሮጀክቶች ጠቀሜታ ወይም በአዲስ ቦታ ላይ ለመገንባት እስከ $100,000 ዶላር የሚደርስ ይቅር ሊባል የሚችል ብድር ነው።

ማመልከቻዎች ሴፕቴምበር 8 ቀን 2022 ከምሽቱ 5 ሰዓት ላይ ያበቃሉ። እባክዎን ከማመልከትዎ በፊት ከታች ያለውን መረጃ ይከልሱ።

ማመልከቻው በእንግሊዝኛ መቅረብ አለበት። ማመልከቻዎን እንዲያጠናቅቁ ለመርዳት የሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ሰራተኞች ይገኛሉ እና ከዚህ በታች ያሉትን የማመልከቻ ጥያቄዎች አስቀድመው ማየት ይችላሉ። የትርጉም ወይም የአስተጓሚ አገልግሎቶችን ለመጠየቅ፣ እባክዎን (206) 684-8090 ይደውሉ።

ምን ዓይነት ፕሮጀክቶች ናቸው ብቁ የሚሆኑ?

ይህ የገንዘብ ድጋፍ የሚከተሉትን ጨምሮ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች ሊያገለግል ይችላል:

  • እንደ የደጅ ማስቀመጫ አሁን ላላቸው ቦታ የእድሳት ዋጋ የሚሆን።
  • የመውሰጃ መስኮቶችን ማሰራት።
  • የአየር ማጣሪያ ስርዓቶችን ማሻሻል።
  • አሁኑ ያለውን ቦታ ማስፋፋት።
  • አዲስ ቦታን መገንባት።
  • ሁሉንም እንደ ቁሳቁስ፣ የአርክቴክት ክፍያዎች፣ የፍቃድ ክፍያዎች እና መሳሪያዎች የግንባታ ወጪዎች።

የብቃት መስፈርቶች

ለዚህ የገንዘብ ድጋፍ ብቁ ለመሆን የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለቦት:

  • በሲያትል ከተማ ገደቦች ውስጥ የሚገኝ ልዩ ፈቃድ የሚሸጥ ወይም አንድ የሰንሰለት ተቋም ሳይሆን ራሱን የቻለ ለትርፍ የተቋቋመ ንግድ የሆነ።
  • ንግዱ በኮቪድ-19 ምክንያት ቀጥተኛ የኢኮኖሚ መተጓጐል ችግር ልምድ ያጋጠመው።
  • አሁን የሚሠራ ተገቢ የሲያትል የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው።
  • የከተማ ንግድ እና ሥራ (B&O) ግብሮችን ፋይል ያደረጉ። ካለበት ግብሮችን ሙሉ በሙሉ የከፈለ ወይም ተመርጠው በሁለት ወራት ውስጥ የሚያሟላ።
  • ከ2019 በፊት የንግድ ሥራ መሥራት የጀመረ። ፕሮጀክቱ የጀማሪ ከሆነ፣ አመልካቹ የቀደመ የንግድ ሥራ ልምድ ወይም የኢንዱስትሪ ልምድ ሊኖረው ይገባል።
  • ለፕሮጀክትዎ አንድ የድጋፍ ደብዳቤ ያስገቡ።

ቦታ:

  • የተከራይ ማሻሻያ ፕሮጀክት በሲያትል ከተማ ገደብ ውስጥ እንዲገኝ ያቅዱ።
  • በአሁኑ ጊዜ ሁለት ወይም ከዚያ ያነሱ ቦታዎችን የሚያካሄድ።  

መጠን:

  • 50 ወይም ከዚያ በታች የሙሉ ጊዜ ተመጣጣኝ (FTE) ሰራተኞች ያሉት። 
  • የ$2 ሚሊዮን ወይም ከዚያ በታች ዶላር ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢ ያለው።
  • አንድ ብቸኛ ባለቤት፣ ሲ-ኮርፖሬሽን፣ የትብብር ኅብረት፣ ተጠያቂነቱ የተወሰነ ኩባንያ፣ ሽርክና ወይም የተገደበ ሽርክና የሆነ።

በተጨማሪም፣ የተሰጣቸው ፕሮጀክቶች ብቁ ሆነው ለመቀጠል የሚከተሉትን ማቅረብ መቻል አለባቸው:

  • ከተመረጠ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የፍላጎት ማሳያ ደብዳቤ (LOI) ወይም ከአከራይ የተፈረመ የኪራይ ስምምነት ውል ያስገቡ።
  • ከታሕሳስ 2023 በፊት ግንባታ የጀመረ።

የዚህ የገንዘብ ድጋፍ ውሎቹ ምንድ ናቸው?

  • ብቁ የሆኑ ንግዶች እስከ $100,000 ዶላር ሊቀበሉ ይችላሉ።
  • የገንዘብ ድጋፍ ከ 0% ወለድ ጋር ሊሰረይ እንደሚችል ብድር ይሰጣል። ግንባታውን ካጠናቀቁ ከአንድ ዓመት በኋላ ንግድዎ ለአንድ ዓመት ያህል ሥራዎችን ከቀጠለ ብድሩ ይቅር ሊባል የሚችል ይሆናል።
  • የከተማው የገንዘብ ድጋፍ የፕሮጀክቱን ሙሉ ወጪዎች ለመሸፈን የታሰበ አይደለም። ለበጀቱ እርስዎ እና አከራይዎ የገንዘብ አስተዋጽዎ እንዲያደርጉ ይጠበቅባችኋል።
  • ወደ መጨረሻው የድጋፍ ገንዘብ ስጦታ ምዕራፍ ለመቀጠል፣ የሽልማት ማስታወቂያ ከተሰጠበት በስድስት ወራት ውስጥ የፍላጎት ማሳያ ደብዳቤ (LOI) ወይም ከባለንብረቱ የተፈረመ የኪራይ ውል ማስገባት እና ገንዘቡን ከታሕሳስ 15 ቀን 2023 በፊት ማውጣት ይኖርብዎታል።

አስፈላጊ ሰነዶች

ማመልከቻዎን ለማስገባት የሚከተሉት ሰነዶች ያስፈልግዎታል:

  • የተዋሃደ የንግድ መለያ (UBI) ቁጥር (ዘጠኝ አሃዞች)።
  • የከተማ ንግድ ፈቃድ ቁጥር (ስድስት አሃዞች)።
  • የንግድ እና ሙያ (B&O) ግብሮች።
  • ኮቪድ ንግድዎን እንዴት እንደነካው ማብራሪያ።
  • የፕሮጀክት ወጪዎችን እና የድጋፍ ገንዘብ ምንጮችን የሚገልጽ በጀት።
  • ከአከባቢዎ የጐረቤት ድርጅት የድጋፍ ደብዳቤ (የንግድ ወረዳ ድርጅቶች ዝርዝር)፣ ሌላ አነስተኛ የንግድ ድርጅት ባለቤት፣ ወይም ለትርፍ ያልተቋቋመ። (የድጋፍ ደብዳቤ አብነት በእንግሊዝኛ እዚህ ይገኛል: Letter of Support Template)።

ለድጋፍ ገንዘብ ከተመረጠ፣ የሚከተሉትን ማስገባት ያስፈልግዎታል:

  • ከ2019፣ 2020 እና 2021 የቅርብ ጊዜ የሂሳብ መግለጫዎች።
  • የፍላጎት ማሳያ ደብዳቤ ወይም ከተመረጠ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ የተፈረመ የኪራይ ውል።

የማመልከቻ ሂደት

ማመልከቻዎን እስከ ሴፕቴምበር 8 ቀን 2022 ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት ድረስ በመስመር ላይ ማስገባት አለቦት።

  • የዘገዩ ማመልከቻዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
  • የኢኮኖሚ ልማት ጽሕፈት ቤት እና አንድ የማህበረሰብ አማካሪ ቡድን በመስከረም ወር 2022 ወቅት ማመልከቻዎችን ይገመግማሉ።
  • በጥቅምት 2022 ውስጥ አመልካቾች ሁሉ ሁኔታቸው ይነገራቸዋል።

ማመልከቻው በእንግሊዘኛ መቅረብ አለበት፣ ነገር ግን የሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ሰራተኞች ለጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እና ማመልከቻዎን በመሙላት ሊረዱዎት ይችላሉ።

በመስመር ላይ ከማመልከትዎ በፊት ይህንን ሰነድ ከማመልከቻው ጥያቄዎች ጋር መገምገም ይችላሉ: የንግድ የተከራይ ማሻሻያ ፈንድ ማመልከቻ

 

እዚህ ያመልክቱ!

እርዳታ ይፈልጋሉ ወይም ጥያቄዎች አሉዎት?

እባክዎን ለእርዳታ (206) 684-8090 ይደውሉ እና የሚከተለውን መረጃ በድምጽ መልእክትዎ ውስጥ ያስተውሉ: ስም፣ የስልክ ቁጥር፣ ተመራጭ ቋንቋ እና የሚያስፈልግዎት የድጋፍ አይነት።

ምናባዊ የመረጃ ክፍለ ጊዜዎች

እነዚህ ምናባዊ የመረጃ ክፍለ ጊዜዎች ፕሮግራሙን ያብራራሉ እና ጥያቄዎችን ይመልሳሉ። እባክዎን ለሁለት ቋንቋ የማስተርጐም ድጋፍ ሁለት ሳምንቶችን አስቀድመው ይመዝገቡ።

መጪ ፕሮግራሞች ወይም እርዳታ

ከኢኮኖሚ ልማት ጽህፈት ቤት ስለ ዝመናዎች እና ሌሎች ፕሮግራሞችን ለማግኘት፣ እባክዎ ለጋዜጣችን አባልነት ይመዝገቡ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይከተሉን: @SeattleEconomy በ Twitter፣ Instagram፣ እና Facebook። 

የሲያትል የኢኮኖሚ ልማት ጽሕፈት ቤት ለሁሉም የሲያትል የተለያዩ ማህበረሰቦች የኢኮኖሚ ዕድሎችን በማስፋፋት መላውን ከተማ ለማዳረስ የሚጠቅም ፍትሃዊ እኩልነት እና አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባት ቁርጠኛ ነው።

የሲያትል ከተማ ሁሉንም ሰው በፕሮግራሞቹ እና በእንቅስቃሴዎቹ እንዲሳተፍ ያበረታታል። ለተጨማሪ ጥያቄዎች፣ ለትርጉም ወይም ለማስተርጐም፣ ለቴክኒክ ድጋፍ፣ ለአካል ጉዳተኝነት ማስተናገጃዎች፣ ተለዋጭ ይዞታዎች ላላቸው ቁሳቁሶች ወይም የተደራሽነት መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎ የሲያትል የኢኮኖሚ ልማት ጽሕፈት ቤትን በ (206) 684-8090 ወይም oed@seattle.gov ያግኙ።

Economic Development

Markham McIntyre, Director
Address: 700 5th Ave, Suite 5752, Seattle, WA, 98104
Mailing Address: PO Box 94708, Seattle, WA, 98124-4708
Phone: (206) 684-8090
Phone Alt: (206) 684-0379
Fax: (206) 684-0379
oed@seattle.gov

Newsletter Updates

Subscribe

Sign up for the latest updates from Economic Development

The mission of the Office of Economic Development (OED) is to help create healthy businesses, thriving neighborhoods, and community organizations to contribute to a robust economy that will benefit all Seattle residents and future generations.