This content has been professionally translated in other languages.
Este contenido ha sido traducido profesionalmente a otros idiomas.
此內容已被專業翻譯成其他語言。
Nội dung này đã được dịch chuyên nghiệp sang các ngôn ngữ khác.
Qoraalkan waxaa si xirfad leh loogu turjumay luqado kale.
Ang nilalamang ito ay propesyonal na isinalin sa ibang mga wika.
이 콘텐츠는 전문적으로 다른 언어로 번역되었습니다.
ይህ ይዘት በሙያዊ በሌሎች ቋንቋዎች ተተርጉሟል።
ወደ ክፍሉ ይሸጋገሩ፦
- የስልጠና ፕሮግራሞች
- ተዛማጅ የሥራ ክፍሎች
- ለንግድ ተቋማት ድጋፍ የሚሰጡ ድርጅቶች
- በኢንዱስትሪ ላይ የተመሰረቱ ማህበራት (የሙያ ዘርፍ ማህበራት)
- ሌሎች ሀብቶች (መረጃዎች)
- Business Impact Northwest: Business Impact Northwest ንግድዎን በተሳካ ሁኔታ ለመጀመር እና ለማሳደግ የሚያስፈልጎዎትን ስልጠና፣ ትምህርቶች እና ካፒታል ያቀርባል።
- Communities Rise: Communities Rise በዋሽንግተን ግዛት ውስጥ በሚገኙ እና በስርዓታዊ ጭቆና በተጎዱ ድርጅቶች፣ አነስተኛ ንግዶች እና ማህበረሰቦች ጋር በመስራት አቅምን ለመጨመር እና ስልጣንን ለመገንባት ይሰራል። Communities Rise (ኮምዩኒቲስ ራይዝ) በአቻ ለአቻ ትምህርት፣ በሙያዊ ክትትል፣ በሕግ አገልግሎቶች እና በስልጠና አማካኝነት ድጋፍ ያቀርባል።
- የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በሲያትል (Ethiopian Community in Seattle):- የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በሲያትል የተለያዩ አስፈላጊ ፕሮግራሞችን በማቅረብ በሲያትል የሚገኘ የተለያዩ ማህበረሰቦችን ለማገልገል እና ለማብቃት በቆራጥነት ይሰራል። የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ጤንነት ለማጎልበት ለአረጋውያን ድጋፍ እና የጤና አገልግሎት ያቀርባል፤ በትምህርት የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ እና ባህላዊ እሴቶችን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ የትምህርት ቁሳቁሶችን ያመቻቻል፤ ዘላቂ የኑሮ መረጋጋት ለመፍጠር የቤት እርዳታ ያቀርባል፤ እንዲሁም የፈጠራ ስራዎችን ለማበረታታት ለአነስተኛ ንግዶች ድጋፍና የመረጃ ልውውጥ ያደርጋል። ከዚህ በተጨማሪ ተቋሙ የሚያቀርባቸው ማህበራዊ አገልግሎቶች የህብረተሰቡን ሁለገብ ፍላጎቶች የሚያሟሉ ሲሆን፤ ግለሰቦችና ቤተሰቦች የሚያጋጥሟቸውን ተደራራቢ ችግሮች በመወጣት በህይወታቸው ስኬታማ እንዲሆኑ ያግዛሉ።
- Food Innovation Network: የFood Innovation Network ተልዕኮ የአካባቢውን የምግብ ስርዓት ማሻሻል፣ ጤናማ ምግብ የማግኘት እድልን መጨመር፣ ለስኬት መንገዶችን መፍጠር፣ እና የሲያታክ/ታክዊላ (SeaTac/Tukwila) እና የደቡብ ኪንግ ካውንቲ (South King County) የተለያዩ ማህበረሰቦችን የሚያሳትፍ የሀብት እና የሃሳብ መጋራትን መደገፍ ነው። በንግድ ስልጠና እና በአቻ መረብ አማካኝነት፣ ስራ ፈጣሪዎች ፈቃድ በማግኘት እንዲደገፉ ይደረጋል፣ ድጎማ የተደረገባቸው የወጥ ቤት ኪራይ ይሰጣቸዋል፣ እና እንደ የምግብ አቅርቦት እድሎች ላሉ የገበያ መስመሮች ግንኙነቶች ይቀርብላቸዋል።
- Greater Seattle SCORE: አዲስ ንግድ ለመጀመር፣ ነባር ንግድዎን ለማሳደግ እንዲሁም ንግድዎን ለመሸጥ ወይም ጡረታ ለመውጣት ዝግጁ በቢሆኑም፤ ከSCORE ተቋም ባለሙያ አማካሪዎች ነፃ እና ምስጢራዊነቱ የተጠበቀና ሙያዊ የንግድ ምክር አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ። በዘርፉ ባለሙያዎች የሚመሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ አሳታፊ አውደ ጥናቶችን እና ዌቢናሮችን ጨምሮ ሁሉም የአነስተኛ ንግድ ስልጠናዎች ነፃ ናቸው።
- Resource Amplification Management Program (RAMP-Up): የሲያትል ዩኒቨርሲቲ የአልበርስ የንግድ እና ኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤት Resource Amplification Management Program (RAMP-Up) የንግድ ስራ ክህሎትን፣ የዩኒቨርሲቲውን ሀብቶች እንዲሁም የማህበረሰብ ተሳትፎን ያጣመረ ነው። ይህ መርሃ-ግብር ተማሪዎችን እና የዘርፉን አማካሪዎች በሲያትል ማዕከላዊ አካባቢ (Central Area) ውስጥ ካሉና የተለያዩ ድጋፍ ከሚያስፈልጋቸው አነስተኛ ንግዶች ጋር በማጣመር፣ የከተማዋን ፈጣን እድገትና ለውጦች ተቋቁመው ዘላቂ ስኬት እንዲያመጡ የረጅም ጊዜ ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል። ራምፕ-አፕ (Ramp-up) የየአካባቢውን ተፈጥሯዊ የባህል ስብጥርና ብዝሃነት በማስቀጠል፣ ለአነስተኛ ንግዶች የሙያ ክትትል፣ የስትራቴጂክ እቅድ እንዲሁም የቴክኒክ ድጋፍ አገልግሎቶችን ያቀርባል።
- Small Business Development Center: የWashington Small Business Development Center ስራ ፈጣሪዎች ወይም የአነስተኛ ንግድ ባለቤቶች ንግድ እንዲጀምሩ፣ እንዲያሳድጉ፣ እንዲገዙ ወይም እንዲሸጡ ለመርዳት በመላው ግዛቱ በሚገኙ ማህበረሰቦች ውስጥ የሚሰሩ ከ30 በላይ የባለሙያ የንግድ አማካሪዎች ጥምረት ነው።
- Tabor 100: Tabor 100 ለአፍሪካ አሜሪካውያን እና ለመላው ህብረተሰብ የኢኮኖሚ አቅምን ለማጎልበት፣ የላቀ የትምህርት እድልን ለማረጋገጥ እና ማህበራዊ ፍትህን ለማስፈን የሚሰራ የሥራ ፈጣሪዎች እና የንግድ ዘርፍ ተሟጋቾች ማህበር ነው።
- University of Washington Consulting and Business Development Center: የUW Consulting and Business Development Center በተማሪ አማካሪ ቡድኖች እና በፋኩልቲ በሚመሩ የንግድ ትምህርት ኮርሶች አማካኝነት የንግድ ገቢዎችን እድገት እና የስራ እድል ፈጠራን ያበረታታል። ትኩረቱን የቆዳ ቀለም ባላቸው (POC)፣ በሴቶች፣ በLGBTQ+ ማህበረሰብ አባላት፣ በቀድሞ የሰራዊት አባላት እና አነስተኛ የልማት እድል ባገኙ ማህበረሰቦች በተቋቋሙ ንግዶች ላይ በማድረግ፤ ከሳምንት እስከ ሰባት ወራት የሚቆዩ ሙያዊ የምክርና የአማካሪነት ፕሮግራሞችን ያመቻቻል። በእነዚህ ፕሮግራሞች ወቅት፣ ተማሪዎች እና የሙያ አማካሪዎች ትርፍን በሚያሳድጉ እና አዲስ እድገትን በሚያመጡ ፕሮጀክቶች ላይ ከንግድ ባለቤቶች ጋር በቅርበት ይሰራሉ።
- Urban Impact: Urban Impact የንግድ እቅድ ስልጠና እና ጥቃቅን ብድር የማግኘት እድልን በመጠቀም ሃሳቦችን ወደ ማስጀመሪያ ለማምጣት ያለመ ከፍተኛ ፕሮግራም በማቅረብ ለአካባቢው ስራ ፈጣሪዎች የኔትወርክ፣ የአሰልጣኝነት እና የኢንቨስትመንት እድሎችን ይሰጣል። የአርባን ኢምፓክት (Urban Impact) አገልግሎቶች ለነባር የንግድ ተቋማት ሙያዊ ምክርና ክትትል፣ የቴክኒክ ድጋፍ፣ የመረጃ ትስስር እንዲሁም የፋይናንስና የካፒታል አማራጮች የሚያገኙበትን መንገድ ያመቻቻሉ። ከሲያትል ፓሲፊክ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር፣ ስራ ፈጣሪዎች ለስራ ማስጀመሪያ ካፒታል ሃሳባቸውን የሚያዳብሩበት እና የሚያቀርቡበት የማህበራዊ ስራ ፈጠራ የዝግጅት እድልን ይሰጣሉ።
- Urban League of Metropolitan Seattle Entrepreneurship Community and Cultural Office: የEntrepreneurship Community and Cultural Office የንግድ እና የንግድ ፋይናንስ ሙያዊ ክትትል፣ እንዲሁም ለአነስተኛ ንግድ ባለቤቶች ነፃ ቦታ እና ቴክኖሎጂ ድጋፍ ያቀርባል። ከዚህ በተጨማሪ ተቋሙ የንግድ ትስስር ማጠናከሪያ ምሽቶችን፣ የሙያ ማሻሻያ አውደ ጥናቶችን እንዲሁም ለአነስተኛ ንግድ ባለቤቶች የውይይት መድረኮችን ያዘጋጃሉ።
- ቬንቸርስ (Ventures) : ቬንቸርስ (Ventures) ተቋሙ አነስተኛ የገንዘብ አቅም ግን ከፍተኛ የፈጠራ ብቃት ላላቸው ስራ ፈጣሪዎች የንግድ ስልጠናዎችን፣ የመነሻ ካፒታል አቅርቦትን፣ የሙያ ክትትልን እና የተግባር ልምድ ልውውጥ እድሎችን ያመቻቻል።
- የደንበኞች አገልግሎት ጽሕፈት ቤት:-
- "Find It, Fix It" የሞባይል ተጠቃሚዎች የተመረጡ ችግሮችን ለሲያትል ከተማ ሪፖርት የሚያደርጉበት ሌላ መንገድ የሚያቀርብ የስማርትፎን መተግበሪያ ነው። በFind It, Fix It አማካኝነት፣ ችግርን በስማርትፎንዎ ፎቶ በማንሳት እና ዝርዝር መረጃ በማካተት አስረክብ (submit) የሚለውን በመጫን ሪፖርት ማድረግ በጣም ቀላል ነው፡፡ ቦታውን በትክክል ለመለየት የካርታውን "drag and drop" ባህሪ ወይም የስልኩን የራሱን ቴክኖሎጂ መጠቀም ይቻላል።
- የደንበኞች መረጃ መመሪያ በከተማው ውስጥ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚቀርብ አጠቃላይ መረጃ እና የመገናኛ መረጃ ያቀርባል፤ ይህም ስለተመረጡ ባለሥልጣናት፣ 24-ሰዓት አገልግሎቶች፣ የሕፃናትና የወጣቶች መረጃ፣ የንግድ ሀብቶች፣ የእንስሳት መረጃ፣ የቅጥር መረጃ፣ ፈቃድ ማግኘት፣ የፖሊስ ክፍሎች፣ የንብረት ግብር እና ግምገማዎች፣ እና ሌሎችም ያካትታል።
- የሲያትል አዲስ መጪዎች መመሪያ (Seattle Newcomer’s Guide) የተለያዩ ሀብቶችን ስለማዘዋወር፣ የመሰረታዊ አገልግሎቶች (እንደ መብራትና ውሀ)፣ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን፣ የትምህርትና የሥራ እድል መረጃዎችን፣ በዋሽንግተን ስቴት ለመራጭነት የመመዝገቢያ መንገዶችን፣ የመንጃ ፈቃድ አወጣጥን፣ ህጋዊ የነዋሪነት መብት የሚያስገኙ ቅድመ ሁኔታዎችን እንዲሁም አጠቃላይ የማህበረሰብ መረጃዎችን ያካተተ አጠቃላይ መመሪያ ነው።
- የትምህርት እና የቅድመ-መደበኛ ትምህርት መመሪያ:-
- ወላጆች ወይም ተንከባካቢዎች ለልጆቻቸው የቅድመ-መደበኛ ትምህርት ቤት፣ የህፃናት ማቆያ እና ሌሎችንም አቅም የሚያጎልብቱ እድሎችን ለማግኘት የሚረዱ የመረጃ ምንጮች።
- ከቅድመ-መደበኛ ህፃናት እንክብካቤና ትምህርት ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ የትምህርት ተቋማት የሚሆኑ የተለያዩ የፋይናንስና የድጎማ አማራጮችን ያግኙ።
- የአካባቢዎች መምሪያ፡-
- የአካባቢ ማህበረሰብ አጋዥ ፈንድ፦ (Neighborhood Matching Fund) በማህበረሰብ አባላት ቅድመ-ተነሳሽነት ለሚዘጋጁና ለሚተገበሩ የአካባቢ ልማት፣ የማህበረሰብ ማደራጀት እና የልማት ፕሮጀክቶች ማህበረሰቡ ከሚያደርገው አስተዋፅኦ ጋር የሚመጣጠን አጋዥ የፋይናንስ ድጋፍ ያቀርባል። ጠንካራ የማህበረሰብ ትስስር የሚያጎለብቱ ፕሮጀክቶችን ለመተግበር የሚሹ የአካባቢ ማህበራት፣ ህዝባዊ ድርጅቶች፣ መደበኛ ያልሆኑ የነዋሪዎች ስብስቦች እንዲሁም የንግድ ማህበራት ማመልከቻቸውን እንዲያቀርቡ ይበልጥ ይበረታታሉ። ሁለት ዓይነት የገንዘብ ድጋፎች (ፈንዶች) አሉ፦ የስሞል ስፓርክስ ፈንድ/ Small Sparks Funds (እስከ $5,000) እና የኮሚዩኒቲ ፓርትነርሺፕ ፈንድ/Community Partnership Funds (እስከ $25,000)።
- የፊልም ፕሮግራም:- በሲያትል ውስጥ ለተሳካ ፊልም የሚያስፈልጎዎት ሁሉም መረጃዎች በየፊልም መመሪያ መጽሐፍ ውስጥ ያገኛሉ። ይህም ስለ ኢንሹራንስ ሽፋን፣ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ቦታ ክፍያና ቅድመ-ይዞታን፣ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች (ፓርኮች) አጠቃቀምን፣ የፖሊስ ሃይል አመዳደብን፣ የሰው-አልባ አውሮፕላኖች (ድሮን) አጠቃቀምን እና ሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮችን የሚመለከቱ መረጃዎችን ይዟል።
- የኪነ-ጥበብ እና የባህል ጽሕፈት ቤት:-
- ለኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የሥራ እድሎች፦ በኪነ-ጥበብ ዘርፍ ሥራ ያግኙ ወይም የሥራ ዕድል ይለጥፉ፤ ለጀማሪ፣ ለመካከለኛ ደረጃ እና ልምድ ላላቸው የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች እንዲሁም ለድርጅቶች በአሁኑ ወቅት ክፍት የሆኑ ሥራዎችን ይመልከቱ።
- የወጣቶች የፈጠራ ፕሮግራሞች፦ መሥሪያ ቤቱ የተነቃቃ እና ማራኪ የወጣቶች የፈጠራ ባህልን ለማስፋፋት ለሚተጉ የኪነ-ጥበብ አሰልጣኞች፣ መምህራን እና ተቋማት ላይ ኢንቨስት ያደርጋል። ይህንን የሚያደርጉት በወጣቶች የፈጠራ ፕሮግራሞች፣ ለሙያ ማሻሻያ ስልጠናዎች፣ ለባህል አጋርነቶች፣ ለህዝብ ግንዛቤ ፈጠራ መርሃ-ግብሮች እና ለሌሎች ተዛማጅ እድሎች የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ነው። እንዲሁም ለከተማዋ ወጣቶች የሚሆኑ የኪነ-ጥበብ እና የባህል ትምህርቶችን እና ሁነቶችን (ኢቨንቶችን) ይደግፋሉ።
- የባህላዊ ስፍራዎች ልማት መርሃ-ግብር፦ የባህላዊ ስፍራዎች ልማት መርሃ-ግብር፦ ዋና ዓላማ በሲያትል ከተማ ውስጥ ለባህላዊና ጥበባዊ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን መጠበቅ፣ አዳዲሶችን መገንባትና ሥራ ላይ ማዋል፤ ከአርቲስቶችና የጥበብ ተቋማት ጋር በመተባበር የፈጠራ ስፍራዎቻቸውን መፃኢ እድል በመቅረፅ ረገድ ያላቸውን ሚና ማጠናከር፤ እንዲሁም ከአልሚዎችና ከግንባታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ኪነ-ጥበብና ባህል በአዳዲስ የልማት ፕሮጀክቶች ውስጥ እንዲካተቱ ማድረግ ነው።
- የገንዘብ ድጋፎች (ግራንቶች)፦ በባህላዊ ድርጅቶችና በግል አርቲስቶች ላይ የሚደረጉ የARTS ኢንቨስትመንቶች የሲያትል ማህበረሰብን የበለጠ ንቁ እና ማራኪ ያደርጉታል። የገንዘብ ድጋፍ (ግራንት) ፕሮግራሞች ለድርጅቶች፣ ለግለሰብ አርቲስቶች፣ ለወጣቶች የስነ-ጥበብ ፕሮግራሞች፣ እና ለጎረቤት እና ማህበረሰብ ቡድኖች የፈንድ እድሎችን፣ ተነሳሽነቶችን እና ስልጠናን ያካትታሉ።
- የሲቪል/ ዜጎች መብቶች ጽሕፈት ቤት:-
- ተደራሽነት እና አሳታፊነት:-
- ለአነስተኛ የንግድ ተቋማት የተዘጋጁ ከአድልዎ ነፃ የሥራ አካባቢ መፍጠሪያ ስልጠናዎች
- በኮንትራት አሰጣጥ ላይ የሚደረግ ፍትሃዊነት (የኮንትራት ፍትሃዊ እኩልነት)
- የፍትሃዊ ቅጥር ቴክኒካዊ እገዛ
- ለደንበኞች ፍትሃዊ አገልግሎቶች መስጠት (የህዝብ አገልግሎት ህጎች፣ ADA፣ የሁሉም ጾታ መጸዳጃ ቤት ህግ፣ ወዘተ)
- የሰራተኛ ደረጃዎች ጽሕፈት ቤት (OLS):- የሰራተኛ ደረጃዎች ጽሕፈት ቤት ቀጣሪዎች ከሲያትል የሰራተኛ ሕጎች ጋር እንዲጣጣሙ ለመርዳት ነፃ ቴክኒካዊ እገዛ፣ ስልጠናዎች፣ ትርጉሞች እና ሌሎችም ጨምሮ በርካታ ሀብቶችን ያቀርባል። የህግ ተከባሪነት ድጋፍ ለማግኘት እና/ወይም ስልጠና ለመውሰድ፣ አሰሪዎች በስልክ ቁጥር (206) 256-5297 መደወል፣ በኢሜይል laborstandards@seattle.gov መላክ ወይም በኦንላይን ቅጻቸው በኩል መልእክት መላክ ይችላሉ።
- ስልጠና እና ትምህርት
- ቴክኒካዊ እገዛ
- በአካል ወይም በበይነመረብ (በኦንላይን) የሚሰጡ ስልጠናዎች እና ገለጻዎች
- በቀጥታ ሥርጭትና የተቀረጹ የሥራ ቦታ ደረጃዎችና ህጎች መማሪያ ድረ-ሴሚናሮች (ዌቢናሮች)
- የሕግና ደንብ ተከባሪነትን ለማረጋገጥ የሚረዱ ድጋፎችና የመረጃ ምንጮች
- የሥራ ቦታ ደረጃዎችና ህጎች አጭር መረጃዎች፣ ወቅታዊ የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ሰሌዳ (ፖስተር)፣ ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶች እንዲሁም ሌሎች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች
- አሰሪዎች የሕግና ደንብ ተከባሪነትን ለማረጋገጥ የሚጠቀሙባቸው የሰነድ ማዘጋጃ ቅጾች (አብነቶች)
- የሥራ ቦታ ህጎችና ደረጃዎች ምርመራን በተመለከተ ለአሰሪዎች የተዘጋጀ የአሰራር መመሪያ እና የማረጋገጫ ሰነድ
- አሰሪዎች የሠራተኞችን ሰነድና መዝገብ አያያዝ በተመለከተ ሊከተሏቸው የሚገቡ የሕግ መስፈርቶች መመሪያ
- የሲያትል ከተማን አስተዳደራዊ ወሰኖችና ድንበሮች ለማመልከት የሚያገለግል የመረጃ መረብ ካርታ
- የሚከፈልበት የህክምና እና የደህንነት እረፍት አሰጣጥ ህግጋት ማረጋገጫ ሰነድ
- የሰራተኞች የሥራ ውል ሁኔታ ማረጋገጫ ሰነድ (ተቀጣሪ ሰራተኛ ወይም ነጻ ተቋራጭ)
- የሲያትል ከተማ መብራት (SCL):-
- ለአነስተኛና መካከለኛ የንግድ ተቋማት የኃይል መፍትሔዎች:- የሲያትል ከተማ መብራት ስለ መለያ ቁጥርዎ (አካውንትዎ) ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጡና ለንግድዎ ተስማሚ የሆኑ የኃይል አማራጮችን የሚያቀርቡ ባለሙያዎች አሉት። የሲያትል ከተማ መብራት አገልግሎቶች ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው፣ ንጹህ እና በአካባቢ ላይ ምንም ዓይነት አሉታዊ ተፅዕኖ የሌለው (ኔት-ዜሮ) ኤሌክትሪክ ይጠቀማሉ።
- የግንባታ ነክ ጥያቄዎችና የኤሌክትሪክ ኢንጂነሪንግ አገልግሎቶች፦ የ አዳዲስ የግንባታም ሆነ የመስመር ዝርጋታ ማሻሻያ ሥራዎች ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል ወይም አዲስ አቅርቦት በሚሹበት ጊዜ፣ የሲያትል ከተማ መብራት አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል። የተቋሙ ባለሙያዎች ፕሮጀክትዎን በተያዘለት የጊዜ ገደብና በተመደበው በጀት መሠረት ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገውን ሙሉ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ ናቸው።
- የሲያትል የግንባታ እና ቁጥጥር መምሪያ (SDCI) :- SDCI ሰራተኞች አጠቃላይና ልዩ ልዩ ጥያቄዎችዎን በማስተናገድ፣ በኦንላይን በሚሰጥ የአንድ ለአንድ የምክር አገልግሎት ስለ ፕሮጀክትዎ ዝርዝር ፍላጎቶች ሙያዊ ድጋፍ ያደርጉልዎታል።
- የሲያትል የህዝብ መገልገያ (SPU):-
- የስብ፣ ዘይትና ቅባት አወጋገድና ፍሳሽ መዘጋት ተከታታይ ቡድን፦ በትምህርት ቤቶች፣ በሆቴሎችና በሆስፒታሎች የሚገኙ የንግድ ምግብ ማብሰያ ቤቶች ከምግብ ዝግጅትና ከጽዳት ሂደት ከፍተኛ መጠን ያለው የስብ፣ ዘይት እና ቅባት ቆሻሻ (FOG) ያመነጫሉ። እንደ ካፌዎች፣ ፈጣን ምግብ ቤቶችና ፒዛ ቤቶች ያሉ አነስተኛ የንግድ ተቋማትም ቢሆኑ ከፍተኛ መጠን ያለው የስብ፣ ዘይትና ቅባት ተረፈ-ምርት ያመነጫሉ።
- ለንግድ ተቋማት የተዘጋጁ የስብ፣ ዘይትና ቅባት (FOG) የመረጃ ሰነዶች የሚከተሉትን ያካተቱ ናቸው፦ የFOG ቅድመ-ማጣሪያ መሣሪያዎች የጥገና መዝገብ ቅጾች፣ መልካም የአሰራር መመሪያዎች፣ የFOG አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ዝርዝር፣ የምግብ ቤቶች የቅባት አወጋገድ መመሪያዎች እና ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶች።
- የመልሶ መጠቀምና የኦርጋኒክ ቆሻሻ ማዳበሪያ ዝግጅት መርሃ-ግብር፦ ተቋምዎ የቆሻሻ መጠንን በመቀነስ የማስወገጃ ወጪዎችን እንዲቆጥብ የሚያስችሉ ድጋፎችና የመረጃ ምንጮች ተዘጋጅተዋል። ነፃ ፖስተሮችን፣ ምልክቶችን (ዲካሎችን) እና የውስጥ የቆሻሻ ማሰባሰቢያ ዕቃዎችን ለመጠየቅ ከኤስፒዩ (SPU) አረንጓዴ ንግድ ፕሮግራም (Green Business Program) ጋር ይገናኙ። የአረንጓዴ ንግድ ፕሮግራም ጋር ይገናኙ።
- የልማት አገልግሎቶች ጽሕፈት ቤት:- የልማት አገልግሎቶች ጽሕፈት ቤት በሲያትል የህዝብ አገልግሎት መስሪያ ቤት (SPU) የአገልግሎት ክልል ውስጥ አዲስ የውሃ መስመር ዝርጋታ ለማስገባት ለሚፈልጉ አልሚዎችና የቤት ባለቤቶች አስፈላጊውን ሙያዊ ድጋፍና ማብራሪያ ይሰጣል። በሕዝብ መጠቀሚያ ቦታዎች የሚካሄዱ አዳዲስ ፕሮጀክቶች የወጡትን ሕጋዊ መስፈርቶችና መመሪያዎች ማሟላታቸውን ያረጋግጣሉ። እንዲሁም ከሲያትል የትራንስፖርት መምሪያ (SDOT) ጋር በመተባበር ከውሃ ፍሳሽ፣ ከፍሳሽ ውሃ እና ከውሃ ዋና መስመር ማራዘሚያዎች ጋር የተያያዙ የመንገድ አጠቃቀም ፈቃዶችን በመመርመር ያፀድቃሉ።
- የዝናብ ውሃ ፕሮግራሞች:- የግል የፍሳሽ ስርዓትዎ የዝናብ ውሃ ፍሰትን የሚቀንስ ወይም ውሃው ወደ ከተማው የዝናብ ውሃ ስርዓት፣ ጅረቶች፣ ሐይቆች ወይም ፒዩጄት ሳውንድ (Puget Sound) ከመግባቱ በፊት ለማጽዳት የሚረዳ ከሆነ ዝቅተኛ የፍሳሽ ማስወገጃ ክፍያ ለማግኘት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። የንግድ ተቋምዎ ለፍሳሽ ሞልቶ መፍሰስ ተጋላጭ በሆኑ በተለዩ የፍሳሽ ገንዳ አካባቢዎች ውስጥ የሚገኝ ከሆነ፣ የዝናብ ውሃ መሬት ማሳረጊያ (Rain Garden) ወይም የውሃ ማከማቻ ታንከር (Cistern) እንዲገጠምልዎ የሰለጠነ የሬይንዋይዝ (RainWise) ተቋራጭ ለመቅጠር የሚረዳ ቅናሽ/መልሶ ክፍያ (Rebate) ሊያገኙ ይችላሉ። ንብረትዎ ብቁ መሆኑን ይመልከቱ፣ ኮንትራክተር ያግኙ፣ እና በኦንላይን ላይ ያመልክቱ።
- የውሃ ቁጠባ ፕሮግራም:- ውሃ መቆጠብ ለንግድ እና ለአካባቢው ጠቃሚ ነው። የንግድ ተቋምዎ የውሃ ብክነት የሚያስከትሉ መሣሪያዎችን በማዘመን እና የዕለት ተዕለት አሰራሮችን በማሻሻል የውሃ አጠቃቀምን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ፣ እንዲሁም ወርሃዊ የአገልግሎት ወጪውን ከ20 እስከ 30 በመቶ በታች ማውረድ ይችላል። ውሃን በአግባቡ መጠቀም ወርሃዊ ወጪን ለመቀነስ የሚረዳ ብቻ ሳይሆን፣ ንጹህ የውሃ ሀብት መጠን የተወሰነ በመሆኑ ለአካባቢ ጥበቃም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል።
- የውሃ ቁጠባ አጋርነት (Saving Water Partnership)፦ በሲያትል እና በኪንግ ካውንቲ (King County) ውስጥ የውሃ ቁጠባ ፕሮግራሞችን ለማቅረብ በአንድነት በሚሰሩ የሀገር ውስጥ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ስብስብ በኩል ከዋጋ ተመላሽ ቅናሾችና (ሪቤቶች) እና ድጋፎችን ያግኙ።
- የኤንቫይሮስታርስ (EnviroStars) አረንጓዴ ንግድ ፕሮግራም:- የEnviroStars ፕሮግራም አካባቢንና የህብረተሰብን ጤና ለማስጠበቅ ለሚሰሩ የዋሽንግተን ግዛት የንግድ ተቋማት የተዘጋጀ ሁሉን አቀፍ የአገልግሎትና የመረጃ ማዕከል ነው። ይህ መርሃ-ግብር ከ16 የመንግስት መሥሪያ ቤቶች የተውጣጡ ለአካባቢ ተስማሚ የንግድ ፕሮግራሞችን አስተባብሮ የያዘ ሲሆን፣ የኃይልና የውሃ አጠቃቀም ቁጠባን፣ የብክለት መከላከልን፣ እንዲሁም የቆሻሻ፣ የመርዛማ ኬሚካሎችና የበረዶ መቅለጥ/የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትሉ ጋዞች (Greenhouse Gases) ልቀትን የመቀነስ ጥረቶችን በበላይነት ይደግፋል። ይህ መርሃ-ግብር በሲያትል ህዝብ አገልግሎት መስሪያ ቤት፣ በሲያትል ሲቲ ላይት የኤሌክትሪክ አገልግሎት እና በሲያትል የኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በጋራ የሚደገፍና የሚከናወን ነው።
- የስብ፣ ዘይትና ቅባት አወጋገድና ፍሳሽ መዘጋት ተከታታይ ቡድን፦ በትምህርት ቤቶች፣ በሆቴሎችና በሆስፒታሎች የሚገኙ የንግድ ምግብ ማብሰያ ቤቶች ከምግብ ዝግጅትና ከጽዳት ሂደት ከፍተኛ መጠን ያለው የስብ፣ ዘይት እና ቅባት ቆሻሻ (FOG) ያመነጫሉ። እንደ ካፌዎች፣ ፈጣን ምግብ ቤቶችና ፒዛ ቤቶች ያሉ አነስተኛ የንግድ ተቋማትም ቢሆኑ ከፍተኛ መጠን ያለው የስብ፣ ዘይትና ቅባት ተረፈ-ምርት ያመነጫሉ።
- የልዩ ዝግጅቶች (ኩነቶች) ጽሕፈት ቤት:- የልዩ ዝግጅቶች (ኩነቶች) ድረ-ገጽ የትኞቹ ዝግጅቶች በልዩ ኩነትነት እንደሚመደቡ እና የልዩ ዝግጅት (ኩነት) ፈቃድ ማውጣት የሚገባበትን ሁኔታ በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ያቀርባል። በተጨማሪም ድረ-ገጹ የልዩ ዝግጅት (ኩነት) ፈቃድ አሰጣጥ ሂደትን፣ የማመልከቻ መመሪያዎችን፣ እንዲሁም ለአስፈላጊ ዝግጅቶች የሚያስፈልጉ ሌሎች ተዛማጅ ፈቃዶችን የሚመለከቱ ዝርዝር መረጃዎችን ያካተተ ነው።
- ስልጠና እና ትምህርት
- ተደራሽነት እና አሳታፊነት:-
- የሲያትል የንግድ አካባቢዎች (ቢዝነስ ዲስትሪክቶች):- የሲያትል የንግድ አካባቢዎች (ቢዝነስ ዲስትሪክቶች)የከተማዋን ልዩ ልዩ ባህላዊና ማህበራዊ ብዝሃነት በጥልቀት ለመረዳትና ለመቃኘት በርካታ አማራጮችን ያመቻቻሉ። እያንዳንዱ ሰፈር/አካባቢ ልዩ እና በባህል እንዲሁም በተለያዩ የንግድ ዘርፎች የበለፀገ ነው። በከተማው ውስጥ ያሉትን የተለያዩ የአነስተኛ ንግድ አካባቢዎች ማወቅ፣ ንግድ ለማካሄድ በሚወስኑበት ቦታ ላይ የሚገኘውን አካባቢ፣ ህዝብ እና ባህል በደንብ ለመረዳት እድል ይሰጣል።
- የንግድ ማሻሻያ አካባቢዎች መርሃ-ግብር (Business Improvement Areas)፦ የንግድ ማሻሻያ አካባቢዎች መርሃ-ግብር የንግድ ማዕከላትን (አካባቢዎችን) መልሶ ለማንቀሳቀስ፣ ለማደስ እና በአግባቡ ለማስተዳደር የሚያስችሉ የፋይናንስ ምንጭ ማመቻቻ ስርዓቶች ናቸው። የአካባቢው ባለድርሻ አካላት የንግድ አካባቢያቸውን ጥገና፣ ማሻሻያ እና ማስተዋወቅ በበላይነት ይቆጣጠራሉ፤ እንዲሁም በገንዘብ ይደግፋሉ። የንግድ ማሻሻያ አካባቢዎች (BIA) ፕሮጀክቶች ሃሳብ አመንጪነት፣ ንድፍ አዘጋጅነት እና አስተዳደር በሙሉ የሚከናወነው የገንዘብ መዋጮውን በሚያበረክቱት የአካባቢው ባለድርሻ አካላት ነው:: በቀጠናው የሚገኙ ሁሉም አካላት ተገቢውን የገንዘብ መዋጮ/ድርሻ የመክፈል ግዴታ አለባቸው። እያንዳንዱ የንግድ ማሻሻያ ቀጠና (BIA) በክፍያ ከፋዮች በሚሰየም የመማክርት ቦርድ በበላይነት ይመራል። የከተማው አስተዳደር የንግድ ማሻሻያ ቀጠናውን (BIA) በመወከል የተጣሉትን ክፍያዎች የሚሰበስብ ሲሆን፣ ለሥራው የወጡ ወርሃዊ ወጪዎችንም በበጀት ምትክ መልክ ተመላሽ ያደርጋል።
- በአሁኑ ጊዜ በሲያትል ከተማ ውስጥ አስራ አንድ የተቋቋሙ የንግድ ማሻሻያ ቀጠናዎች (BIAs) አሉ፡- 15th Ave in Capitol Hill፣ Ballard፣ Broadway፣ Chinatown-International District፣ Columbia City፣ Downtown Metropolitan Improvement District፣ Pioneer Square፣ Seattle Tourism Improvement Area፣ SODO፣ University District፣ እና West Seattle Junction።
- ቪዚት ሲያትል (Visit Seattle)፦ ቪዚት ሲያትል (Visit Seattle) የሲያትል እና የኪንግ ካውንቲ ይፋዊ የቱሪዝም ማስተዋወቂያ ድርጅት ሆኖ የሚያገለግል፣ የአካባቢውን የሥራ እድሎች እና የኢኮኖሚ እድገት የሚያፋጥን ለትርፍ ያልተቋቋመ የግል ድርጅት ነው። ቪዚት ሲያትል (Visit Seattle) በአባልነት ላይ የተመሰረተ ድርጅት ሲሆን፣ ከ750 በላይ የሚሆኑ የአካባቢው የንግድ ድርጅቶችን፣ ምርቶቻቸውንና አገልግሎቶቻቸውን ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ከሚያመነጨው የቱሪዝም ገበያ ጋር ያገናኛል። Visit Seattle ቪዚት ሲያትል ዓመቱን ሙሉ የሙያ ማበልጸጊያ መድረኮችን፣ የማስተዋወቂያ መርሃ-ግብሮችን እና የተለያዩ የንግድ ትስስር ማጠናከሪያ አማራጮችን ያመቻቻል።
በኢንዱስትሪ ላይ የተመሰረቱ ማህበራት (የሙያ ዘርፍ ማህበራት)
- Good Business Network of Washington:- Good Business Network of Washington በነዋሪዎች፣ በአካባቢው የንግድ ድርጅቶች፣ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ማህበራት እና በከተማ አስተዳደር ተቋማት መካከል የተመሰረተ ስትራቴጂካዊ ጥምረት ነው። የSeattle Good Business Network ማህበረሰቡ በአካባቢው ምርትና አገልግሎት ላይ እንዲሳተፍ፣ እንዲያመርትና ኢንቨስት እንዲያደርግ በማስቻል ግኑኝነትን ይፈጥራል፤ ይህም እያንዳንዱ ዜጋ በአካባቢው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ውስጥ ጉልህ ድርሻ እንዲኖረው ያመቻቻል። ተቋሙ ሲያትል ሜድ (Seattle Made) እና ጉድ ፉድ ኢኮኖሚ (Good Food Economy) የተሰኙትን ጨምሮ የአካባቢው ምርቶችና አገልግሎቶችን ለማበልጸግ የሚያስችሉ በርካታ መርሃ-ግብሮችን ያከናውናል።
- ላይፍ ሳይንስ ዋሽንግተን (Life Science Washington)፦ ላይፍ ሳይንስ ዋሽንግተን (Life Science Washington)፦ በአባልነት ላይ የተመሰረተ ድርጅት ሲሆን፣ በተሳትፎ፣ በትብብር፣ በማስተዋወቅ እና በሞጋችነት (አድቮኬሲ) አማካኝነት አባላቱን እና አጋሮቹን በዋሽንግተን ግዛት ውስጥ የሚከናወኑ የህይወት ሳይንስ ፈጠራዎች፣ የሥራ እድል ፈጠራ እና የዘርፉ እድገት አካል እንዲሆኑ ያገናኛል፣ ድጋፍም ይሰጣል።
- የአምራች ኢንዱስትሪ ምክር ቤት (Manufacturing Industrial Council)፦ የአምራች ኢንዱስትሪ ምክር ቤት (Manufacturing Industrial Council)፦ በሁሉም የኢንዱስትሪ ዘርፎች ውስጥ ያሉ ትላልቅ እና አነስተኛ የንግድ ተቋማትን ያካተተ በአባልነት ላይ የተመሰረተ ድርጅት ነው። የአምራች ኢንዱስትሪ ምክር ቤት (MIC) ለኢንዱስትሪ መሬቶች ጥበቃ እንዲሁም እዚያ ለሚንቀሳቀሱ የባህር ላይ እና የማኑፋክቸሪንግ ንግዶች፣ በማደግ ላይ ባለው የኢንዱስትሪ ኢኮኖሚ ስም ተፅዕኖ ፈጣሪ ድምፅ ይሆናል።
- የዋሽንግተን ቢራ አምራቾች ማህበር (Washington Brewers Guild)፦ የዋሽንግተን ቢራ አምራቾች ማህበር (Washington Brewers Guild) ለትርፍ ያልተቋቋመ ተቋም ሲሆን፣ የክራፍት ቢራ አምራቾችን መብትና ጥቅም ለማስከበርና ለማስተዋወቅ፣ እንዲሁም በዋሽንግተን ግዛተ የዘርፉን ማህበረሰብ ለማጠናከር ይሰራል:: የእጅ ሥራ ቢራ ኢንዱስትሪ እንዲበልጽግ የሚያስችሉ እና ለዋሽንግተን ቢራ ወዳዶች ጥራትና ምርጫ እንዲኖር የሚያረጋግጡ ሕጎችንና ፖሊሲዎችን ለመከታተል ከግዛቱ ሁሉ ቢራ አፍራሾችን ያቀናጃሉ።
- የዋሽንግተን ዓለም አቀፍ ጤና ጥምረት (Washington Global Health Alliance)፦ የዋሽንግተን ዓለም አቀፍ ጤና ጥምረት (Washington Global Health Alliance)፦ የዋሽንግተን ዓለም አቀፍ ጤና ጥምረት የዋሽንግተንን ዓለም አቀፍ የጤና ማህበረሰብ የሚያገናኝ እና መረጃ የሚያቀርብ በአባልነት ላይ የተመሰረተ ድርጅት ነው። ተቋሙ በዋሽንግተን ግዛት ውስጥ ከዓለም አቀፍ ጤና ጋር የተያያዙ ዜናዎች፣ ኩነቶች እና የሥራ ዕድሎች ዋነኛ የመረጃ ምንጭ ሆኖ ያገለግላል።
- የዋሽንግተን ሆስፒታሊቲ ማህበር (Washington Hospitality Association)፦ የዋሽንግተን ሆስፒታሊቲ ማህበር (Washington Hospitality Association) የዋሽንግተን ሆስፒታሊቲ ማህበር ከ6,000 በላይ የሆቴል፣ የምግብ ቤት (ሬስቶራንት) እና የእንግዳ ተቀባይነት/ሆስፒታሊቲ ኢንዱስትሪ አባላትን የሚወክል የግዛቱ መሪ የሆስፒታሊቲ ንግድ ማህበር ነው። የሲያትል ሬስቶራንት አሊያንስ (Seattle Restaurant Alliance)በሲያትል የምግብ ቤት (ሬስቶራንት) ኢንዱስትሪ ላይ ትኩረት የሚያደርግ የአካባቢያቸው ቅርንጫፍ ነው። ለሲያትል ምግብ ቤት ባለቤቶች ወርሃዊ ስብሰባዎች ይካሄዳሉ።
- የዋሽንግተን የችርቻሮ ንግድ ማህበር፡- የዋሽንግተን የችርቻሮ ንግድ ማህበር በህግ አውጭ እና በቁጥጥር ጉዳዮች ላይ የችርቻሮ ነጋዴዎችን ልዩ ጥቅሞች ለመደገፍ ብቻ የተቋቋመ የክልሉ ዋና ማህበር ነው። WRA በመላው ግዛቱ ከትላልቅ ብሄራዊ ሰንሰለቶች እስከ ትንሹ ገለልተኛ ቸርቻሪዎች የሚደርሱ ከ3,500 በላይ የሱቅ ቦታዎችን ይወክላል፣ እና በመላው ግዛቱ እና በሀገሪቱ ካሉ ተመሳሳይ አስተሳሰብ ካላቸው ማህበራት እና የንግድ ምክር ቤቶች ጋር በርካታ ሽርክናዎችን ይይዛል።
- የዋሽንግተን ግዛት የምግብ መኪና ማህበር (Washington State Food Truck Association)፡- የዋሽንግተን ግዛት የምግብ መኪና ማህበር (Washington State Food Truck Association) የተንቀሳቃሽ ምግብ አቅራቢ አባላቶቻቸውን ስኬታማ እንዲሆኑ ለመርዳት የሚሟገት የአባል አገልግሎት ድርጅት ነው። ማህበሩ የምግብ መኪና ንግድ ለመጀመር እና በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ እንደ ማዕከላዊ የሀብት ማዕከል ሆኖ ያገለግላል። ይህ ለሽያጭ የሚሆኑ ግብዓቶችን፣ የዝግጅት እና የምግብ አቅርቦት ማጣቀሻ ምንጭን፣ እንዲሁም የአካባቢ እና የክልል ደረጃ የቁጥጥር ማሻሻያዎችን እና ንቁ የሎቢ እና የጥብቅና ስራዎችን ያካትታል።
- የዋሽንግተን የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪ ማህበር፡- የዋሽንግተን የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪ ማህበር ትላልቅ እና ትናንሽ የሆኑ 1,100 የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ተፅእኖ ፈጣሪ ጥምረት ነው። አሰሪዎች ጠንካራ የሰው ኃይል ስርዓቶችን እንዲገነቡ፣ ንግዶች እንዲያድጉ እና እንዲስፋፉ ለመርዳት፣ ለመደገፍ፣ እና የስርዓት ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና ለኢንቨስትመንት ካፒታል፣ ስልጠና እና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ለስራ እኩል ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የአባል ኩባንያዎችን አቅም ያጠናክራሉ።