በ 8/6/2025 ተዘምኗል
የሱቅ ፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ ጥፋትን እና የንብረት ውድመትን ለመከላከል የደህንነት ማሻሻያዎችን ለመክፈል ለማገዝ ለአንድ ንግድ እስከ 6,000 ዶላር የአንድ ጊዜ ተመላሽ ያደርጋል።
ብቁ ለመሆን፣ ንግዶች የወንጀል መከላከልን በአካባቢ ዲዛይን (CPTED) የደህንነት ግምገማን ከተረጋገጠ ባለሙያ፣ ለምሳሌ ከሲያትል ፖሊስ ዲፓርትመንት የወንጀል መከላከል አስተባባሪ ጋር ማጠናቀቅ አለባቸው። የCPTED የደህንነት ግምገማ ከተጠናቀቀ በኋላ ብቻ የተገዙ የደህንነት እርምጃዎች ገንዘቡን ለማስመለስ ብቁ ናቸው።
ማመልከቻዎች እስከ ዲሴምበር 2025 ወይም ገንዘቦች እስኪያልቁ ድረስ ክፍት ናቸው።
ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ወጪዎች እና ሌሎች በወንጀል መከላከል በአካባቢያዊ ዲዛይን የተረዱ ኢንቨስትመንቶች ገንዘብ ተመላሽ ሊያደርጉ ይችላሉ። በCPTED የደህንነት ግምገማ ወቅት ከወንጀል መከላከል አስተባባሪ በተሰጡት ጥቆማዎች መሰረት ኢንቨስትመንቶችን እንዲገዙ እናበረታታዎታለን። ስለ ብቁ ወጪዎች ማንኛውም አይነት ጥያቄ ካልዎት ቢሯችንን ያነጋግሩ።
- ጊዜያዊ መስኮት ወይም በር ማሸጊያ እንጨት መትከል
- የመስኮት ጥገና ወይም መተካት
- የበር ጥገና ወይም መተካት
- የግቢ በር ጥገና ወይም መተካት
- የውጭ መብራት መጠገን ወይም መተካት
- በሮች
- መቆለፊያዎች
- ምልክቶች
- የደህንነት መስኮት ማጠናከሪያ ፕላስቲክ
- የማይሰበር መስታወት
- የተፈቀዱ የመንገድ መትከያዎች። የመንገድ የቤት ዕቃዎች መመሪያዎችን ይመልከቱ።
ንግድዎ በታሪካዊ ወረዳ ውስጥ የሚገኝ ከሆነ፣ ከCPTED ጋር የተያያዘ ኢንቨስትመንት ከመግዛትዎ በፊት የፈቃድ ሰርተፍኬት (Certificate of Approval) ማግኘት ሊኖርብዎ ይችላል። ንግድዎ ታሪካዊ ወረዳ ውስጥ መሆኑን እዚህ ያረጋግጡ፦ ታሪካዊ ወረዳዎች - ሰፈሮች።
ማመልከቻዎች እስከ ታህሳስ 2025 ድረስ ክፍት ናቸው ፣ ወይም ገንዘብ እስከሚያልቅ ድረስ ።
እባክዎ ከማመልከትዎ በፊት ሙሉውን የብቃት መስፈርት፣ አስፈላጊ ሰነዶችን እና ሌሎች መረጃዎችን ይመልከቱ። ከማመልከትዎ በፊት ይህንን ሰነድ ከማመልከቻው ጋር አብረው ማየት ይችላሉ፦ ወደ ንግድ መመለስ ፈንድ ማመልከቻ የጥያቄዎች መመሪያ።
ጽ/ቤታችን ሁሉም ማህበረሰቦች የኢኮኖሚ ዕድሎችን እንዲያገኙ በማረጋገጥ በሲያትል ውስጥ ለሁሉም ሰው ተስማሚ የሆነ ተደራሽ እና ሁሉን አቀፍ ኢኮኖሚ ለመፍጠር ቁርጠኛ ነው።
የሲያትል ከተማ፣ እያንዳንዱን ሰው በፕሮግራሞቹ እና በእንቅስቃሴዎቹ እንዲሳተፍ ያበረታታል። እርዳታ፣ ትርጉም፣ ለአካል ጉዳተኞች የሚደረጉ ማስተካከያዎች ወይም በተለየ ቅርጸት የተዘጋጁ ሰነዶች ከፈለጉ፣ ቢሯችንን በ206-684-8090 ወይም በOED@seattle.gov ያነጋግሩ።
ወደ አንድ ክፍል ይዝለሉ
የብቁነት መስፈርቶች
ለሱቅ የፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ ብቁ ለመሆን፣ ብቁ ንግዶች የሚከተሉትን ማድረግ አለባቸው፡-
- የ CPTED የደህንነት ግምገማ ማግኘት።
- የCPTED የደህንነት ግምገማ ከተደረገ በኋላ ብቁ የሆነ CPTED መረጃ ያለው የደህንነት ኢንቨስትመንት መግዛት።
- አሁን ላይ የሚሰራ/ቀኑ ያላለፈበት የሲያትል የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው መሆን።
- ሁሉንም የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ ህጎች እና ደንቦችን ማክበር።
- በሲያትል ከተማ ወሰኖች ውስጥ መገኘት።
- በግል ባለቤትነት የተያዘ፣ ፍራንቻይዝ ያልሆነ እና ባለ-ሰንሰለት ያልሆነ ንግድ።
- ለትርፍ የተቋቋመ ንግድ ወይም ለትርፍ ያልተቋቋመ ተቋም፣ 501(c)(3)፣ 501(c)(6)፣ ወይም 501(c)(19) መሆን።
- ከሶስት (3) የማይበልጡ ቦታዎች ይኑርዎት።
- በአሁኑ ጊዜ ለንግድ ክፍት እና በመንቀሳቀስ ላይ ያለ።
ተጨማሪ መመዘኛዎች፦
- እያንዳንዱ የንግድ ቦታ፣ ባለቤት ወይም መለያ (እንደ EIN፣ SSN፣ UBI ቁጥር፣ የንግድ ፈቃድ ቁጥር፣ ቤት እና/ወይም የንግድ አድራሻ) አንድ ማመልከቻ ብቻ ነው ማስገባት የሚችለው።
- ንግዱ ማመልከቻው ከገባበት ቀን በፊት ቢያንስ ለ12 ወራት ሲሠራ የቆየ መሆን አለበት።
- ንግዱ በአንድ ህዝቡን የሚያገለግል አካላዊ ቦታ እና/ወይም በተንቀሳቃሽ የጭነት መኪናዎች ላይ ሆኖ የሚሰራ መሆን አለበት።
- ከተሰጣቸው፣ ንግዶች W-9 መሙላት አለባቸው።
የንግድ መጠንን የሚመለከቱ መስፈርቶች፦
- ንግዱ ከ50 የማይበልጡ የሙሉ ጊዜ አቻ ሰራተኞች ሊኖሩት ይገባል።
- ለሲያትል ከተማ የፋይናንስ እና አስተዳደራዊ አገልግሎቶች መምሪያ በ2024በንግድ እና ሥራ (Business and Occupation) ግብሮች ላይ ሪፖርት በተደረገው መሠረት የንግዱ ዓመታዊ የተጣራ ገቢ ከ$1,000 ዶላር በላይ የሚሠራ እና ከ$7,000,000 ዶላር የማይበልጥ መሆን አለበት።
ለሱቅ የፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ ለማመልከት ብቁ ያልሆኑ ንግዶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-
- ከኪንግ ካውንቲ ጋር ባልተካለለ አካባቢ ውስጥ የሚገኝ የንግድ ተቋም።
- ፍራንቻይዝ ወይም ሰንሰለት ንግዶች።
- በሲያትል ማዘጋጃ ቤት ህግ አንቀጽ 6.270 ስር የሚተዳደሩ "የአዋቂዎች መዝናኛ" ንግዶች።
- ንግዱ የአጭር ወይም የረጅም ጊዜ የኪራይ ወይም የኢንቨስትመንት ንብረት ነው (የግል ሪል እስቴት እና ገለልተኛ ሪልተሮችን (independent realtors)፣ የአጭር ጊዜ ኪራዮች ኤርቢኤንቢን (Airbnb)፣ ቨርቦን (Vrbo)፣ ወዘተ ያካትታሉ)።
- ንግዱ የታክሲ ስራ፣ በጋራ መሣፈር (ራይድሼር)፣ ወይም የምግብ ማድረስ አገልግሎት (ለምሳሌ እንደ ኡበር፣ ሊፍት፣ የሎ ካቢ፣ ዶር ዳሽ፣ ኡበር ኢትስ፣ ወዘተ) የሆነ።
ለማመልከቻ አስፈላጊ ሰነዶች
የሱቅ ፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ ማመልከቻዎች በኢንተርኔት ላይ እንደገቡ ተቀባይነት ያገኛሉ፣ ይታያሉ እና ይስተናገዳሉ።
ከማመልከትዎ በፊት ይህንን ሰነድ ከማመልከቻው ጋር አብረው ማየት ይችላሉ፦ ወደ ንግድ መመለስ ፈንድ ማመልከቻ የጥያቄዎች መመሪያ።
ብቁ አመልካቾች ማመልከቻቸውን ለማስገባት የሚከተለው መረጃ ያስፈልጓቸዋል፦
- የተዋሃደ የንግድ መታወቂያ (Unified Business Identifier) ቁጥር (ዘጠኝ አሃዞች)።
- ለዋሽንግተን ስቴት የንግድ ፍቃድ ሲያመለክቱ የተዋሃደ የንግድ መለያ ቁጥር ያገኛሉ። የተዋሃደ የንግድ መለያ ቁጥርዎን (Unified Business Identifier) በዋሽንግተን ስቴት የገቢዎች ክፍል (Washington State Department of Revenue) በኩል በኢንተርኔት ላይ መፈለግ ይችላሉ።
- የከተማ ንግድ ፈቃድ ቁጥር (ከአራት እስከ ስድስት አሃዞች)።
- በሲያትል ውስጥ የንግድ ሥራ እየሰሩ ከሆነ፣ የሲያትል ንግድ ፈቃድ የግብር ምስክር ወረቀት ሊኖርዎት ይገባል፣ ይህ የከተማ ንግድ ፈቃድ ቁጥር (City Business License Number) በመባልም ይታወቃል። ይህንን የምስክር ወረቀት በየዓመቱ ከታህሳስ31 በፊት ማደስ አለብዎት።
- ይህ የከተማ ንግድ ፈቃድ ቁጥር ከዋሽንግተን ስቴት የንግድ ፍቃድ የተለየ ነው። ቁጥርዎን በከተማ ንግድ ፍቃድ የንግድ ፍለጋ መሳሪያ ላይ ማግኘት ካልቻሉ የዋሽንግተን ስቴት ፍቃድ ብቻ ሊሆን ይችላል ያልዎት።
- ለከተማ ንግድ ፈቃድ ማመልከት እና በኢንተርኔት ላይ በ filelocal-wa.gov ወይም በፖስታ ማደስ ይችላሉ።
- የተሞላ CPTED የደህንነት ግምገማ ።
- የCPTED የደህንነት ግምገማ ቀጠሮ ለመያዝ፣ የአካባቢዎን የወንጀል መከላከያ አስተባባሪ በኢንተርኔት ላይ ያግኙ እና ኢሜል ይላኩለት/ላት። የንግድዎን ስም፣ የንግድ አድራሻዎን ያካትቱ እና ለወደ ንግድ መመለስ ፕሮግራም (Back to Business Program) የCPTED ደህንነት ግምገማ እየጠየቁ መሆኑን ልብ ይበሉ።
- ብቁ የሆኑ የኢንቨስትመንቶች ዝርዝር እዚህ ይገኛል።
- ብቁ ለሆኑ CPTED ኢንቨስትመንቶች የክፍያ ማስረጃ።
- ብቁ ለሆኑ CPTED በመረጃ የተደገፈ ኢንቨስትመንቶች ግዢ የደረሰኞች ቅጂዎችን ያቅርቡ። ብቁ የሆኑ የኢንቨስትመንቶች ዝርዝር እዚህ ይገኛል።
- ግምቶች እና/ወይም የዋጋ ጥቅሶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- የሱቅ ፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ የሚንቀሳቀሰው በማካካሻ ሞዴል ነው፣ ይህ ማለት አመልካቾች አስቀድመው ብቁ መሳሪያዎችን ገዝተዋል ወይም ለብቁ ተከላዎች ከፍለዋል።
- ስለ ብቁ ወጪዎች ማንኛውም ዓይነት ጥያቄ ካልዎት እባክዎን ቢሯችንን ያነጋግሩ።
የማመልከቻ እገዛ
የሱቅ የፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ ማመልከቻ በእንግሊዝኛ በኢንተርኔት ላይ መቅረብ አለበት።
የጽሑፍ ትርጉም ወይም የቃል ትርጉም ድጋፍ
ጥያቄዎችን ለመመለስ እና ማመልከቻዎን እንዲያጠናቅቁ ለመርዳት ሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ሰራተኞች አሉን።
የጽሑፍ ትርጉም ወይም የቃል አስተርጓሚ አገልግሎቶችን ለመጠየቅ፣ እባክዎን በ(206) 684-8090 ይደውሉ። እባክዎ የእርስዎን ስም፣ ስልክ ቁጥር፣ ተመራጭ ቋንቋ እና የተፈለገውን የድጋፍ ዓይነት የያዘ የድምጽ መልዕክት ይተዉ።
በማመልከቻው ላይ ተጨማሪ እገዛ
ጽ/ቤታችን ሁሉም ማህበረሰቦች የኢኮኖሚ ዕድሎችን እንዲያገኙ በማረጋገጥ በሲያትል ውስጥ ለሁሉም ሰው ተስማሚ የሆነ ተደራሽ እና ሁሉን አቀፍ ኢኮኖሚ ለመፍጠር ቁርጠኛ ነው። እርዳታ፣ ትርጉም፣ ለአካል ጉዳተኞች የሚደረጉ ማስተካከያዎች ወይም በተለየ ቅርጸት የተዘጋጁ ሰነዶች ከፈለጉ፣ ቢሮአችንን በ206-684-8090 ወይም በOED@seattle.gov ያነጋግሩ።
በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች
1. በሱቅ የፊት ለፊት ጥገና ፈንድ እና ሱቅ የፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
የሱቅ የፊት ለፊት ጥገና ፈንድ በብልሽት ወይም በሌላ ንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት በማካካስ ይረዳል። ስለ የሱቅ የፊት ለፊት ጥገና ፈንድ የበለጠ ይወቁ።
የሱቅ የፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ የመከላከያ የደህንነት እርምጃዎችን ለማስመለስ ይረዳል።
2። የሱቅ የፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ የሚውለው ለመከላከያ የደህንነት እርምጃዎች ግዢዎች ብቻ ነው?
የገንዘብ ድጋፍ ከመከላከያ የደህንነት እርምጃዎች ጋር ለተያያዙ ግዢዎች ብቻ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችለው የCPTED የደህንነት ግምገማ ከተጠናቀቀ በኋላ ነው። ሊገዙ የሚችሉ ግዢዎች ጊዜያዊ መስኮት ወይም የበር ማሸጊያ እንጨት፣ የመስኮት ጥገና ወይም መተካት፣ የበር ጥገና ወይም መተካት፣ የግቢ በር ጥገና ወይም መተካት፣ በሮች፣ መቆለፊያዎች፣ ምልክቶች፣ የደህንነት የደህንነት መስኮት ማጠናከሪያ ፕላስቲክ እና የማይሰበር መስታወትን ያካትታሉ። የሱቅ ፊት ለፊት ደህንነት የገንዘብ ድጋፍ ሕገወጥ የግድግዳ ጽሑፎችን ማስወገድን፣ የደህንነት ካሜራዎችን መግዛትን፣ ለደህንነት ጥበቃ ሰራተኞች ክፍያን ወይም የተሰረቁ እቃዎች መጥፋትን አይሸፍንም።
የሱቅ ፊት ለፊትዎን ለመጠገን የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ማመልከት የሚፈልጉ ከሆነ፣ እባክዎ በማመልከቻ ውስጥ ያሉትን ጥያቄዎች ይከተሉ። ስለ የሱቅ የፊት ለፊት ጥገና ፈንድ ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይገኛል።
ሕገወጥ የግድግዳ ጽሑፍ በሕዝብ ቦታ ላይ ወይም በግል ንበረት ላይ ካዩ በሚከተለው ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ፦
- አግኝ/አስተካክል (Find It/Fix It) መተግበሪያን፣ የኢንተርኔት ላይ የሪፖርት ቅጹን በመጠቀም ወይም ወደ ከተማው የግራፊቲ ሪፖርት መስመር ጋር በ(206) 684-7587 በመደወል።
- በግል ንብረት ላይ ለሚጻፉ ሕገወጥ ጽሑፎች፣ የንብረቱ ባለቤቶች ጽሑፎችን የማስወገድ ኃላፊነት አለባቸው። ነገር ግን፣ ባለቤቱ ሕገወጥ ጽሁፉን ለማስወገድ ከከተማው እርዳታ ከፈለገ፣ ሕገወጥ ጽሁፎችን በነጻ ለማስወገድ የፈቃድ እና የመልቀቂያ ቅጹን መሙላት ይችላሉ።
ስለ ሕገወጥ ጽሑፍ መወገድ እና መቀነስ ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን የሕገወጥ ጽሑፍ መከላከያ እና ማስወገድ መጽሔቱን
ይመልከቱ። የሱቅ የፊት ለፊት የደህንነት የገንዘብ ስጦታዎች 6,000 ዶላር ናቸው። በልዩ ሁኔታዎች ላይ ለምሳሌ ብዙ ኢንቨስትመንቶች መደረግ ሲኖርባቸው፣ ስጦታው ከገደቡ በላይ የመሄድ ዕድል ሊኖር ይችላል?
የደህንነት እርምጃዎች ዋጋ ከ6,000 ዶላር በላይ ሊሆን እንደሚችል እንገነዘባለን። ሆኖም ከተማዋ በተቻለ መጠን ብዙ ንግዶችን መርዳት እንድትችል እርዳታዎች በ6,000 ዶላር ብቻ የተገደቡ ይሆናሉ።
4. ምን ዓይነት ንግዶች ናቸው ለዚህ የገንዘብ ድጋፍ ብቁ የሆኑት?
አትራፊ ንግዶች ወይም ለትርፍ ያልተቋቋሙ ተቋሞች 501(c)(3)፣ 501(c)(6)፣ ወይም 501(c)(19)፣ በአካል መሬት ላይ ያሉ ሕዝብን የሚያገለግሉ ሱቆች እና የምግብ መኪናዎች ለሱቅ የፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ ብቁ ናቸው። ሁሉም አመልካቾች ወቅታዊ የሲያትል ንግድ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል።
5. በአካባቢ ዲዛይን የወንጀል መከላከል (Crime Prevention Through Environmental Design) ምንድነው?
በአካባቢ ዲዛይን ወንጀልን መከላከል ወንጀልን የመከላከል ቦታን መሰረት ያደረገ እና ዘርፈ-ብዙ ዲሲፕሊናዊ አካሄድ ሲሆን፣ የተገነባውን አካባቢ ዲዛይን እና አስተዳደር በመጠቀም ወንጀልን ለመከላከል ወንጀልን ሊያስከትሉ የሚችሉ የአደጋ ስሜቶችን በማሳደግ በሰዎች ባህሪ ላይ ተጽእኖ ማሳደር ነው። 'ሴፕ-ቴድ' እየተባለ የሚጠራው CPTED ተጎጂዎችን ይቀንሳል፣ የደህንነትን ግንዛቤ ያሳድጋል እና ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታዎችን በመፍጠር እና በመንከባከብ የማህበረሰብን ጠቃሚ ሚና እውቅና ይሰጣል።
CPTED የቦታዎችን አካላዊ እና ማህበራዊ አካባቢ ለመገምገም እና የእንቅስቃሴ ቅጦችን እና እርስ በርስ የሚጋጩ አጠቃቀሞችን ለመለየት እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ለመገምገም ማዕቀፍ ያቀርባል፣ ባህላዊ እና ታሪካዊ ተፅእኖዎችን እና የጠባቂዎች ዓይነቶችን እና ደረጃዎችን ይለያል።
ለበለጠ መረጃ የሲያትል ፖሊስ ዲፓርትመንት ድረ-ገጽን በCPTED እና በዚህ በራሪ ወረቀት ላይ ይመልከቱ።
6. የካናቢስ ንግዶች ለማመልከት ብቁ ናቸው?
አዎ፣ የካናቢስ ሱቆች፣ አብቃይ እና ማከፋፈያዎች ሌሎች የብቁነት መስፈርቶችን እስካሟሉ ድረስ ማመልከት ይችላሉ።
7. የገንዘብ ተቀባዮች እንዴት ነው የሚመረጡት?
ማመልከቻዎችን እንደገቡ እየገመገምን እናስተናግዳለን። ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ ያጋጠማቸው አነስተኛ ንግዶችን ለመርዳት ለሚከተሉት ቡድኖች ቅድሚያ እንሰጣለን፦
በጥቁር፣ በአገሬው ተወላጆች እና በባለ ቀለም ሰዎች ባለቤትነት የተያዙ አነስተኛ ንግዶች።
በሴት ባለቤትነት የተያዙ አነስተኛ ንግዶች።
በጣም በሕዝብ ቆጠራ የተጨናነቀ፣ ቢያንስ 30% ድህነት ወይም ከ60% መካከለኛ ገቢ ያልበለጠ ቦታ ውስጥ የሚገኙ አነስተኛ ንግዶች። ማሳሰቢያ፡- እነዚህ አካባቢዎች የአነስተኛ ንግድ አስተዳደርን የ" ዝቅተኛ ገቢ ማህበረሰቦችን" ፍች ያሟላሉ።
ማሳሰቢያ፦ ሰራተኞቻችን አመልካቾችን በ206 ኤሪያ ኮድ ስልክ ወይም በ@seattle.gov በሚያልቅ ኢሜል ያነጋግራሉ። የሰራተኞቹን ማንነት በ (206) 684-8090 በመደወል ማጣራት ይችላሉ።
8. ተሸላሚዎች ገንዘቡን መልሰው መክፈል አለባቸው?
አይ፣ ይህ ስጦታ ነው። የንግድ ድርጅቶች ገንዘቡን መመለስ አይጠበቅባቸውም።
9. ድጎማዎቹ እንደ ታክስ ገቢ ይቆጠራሉ?
አይ፣ ድጎማዎቹ ታክስ የሚከፈልባቸው ገቢዎች አይደሉም።
10. የትርፍ ሰዓት ሰራተኞች እንደ ተቀጣሪዎች ይቆጠራሉ?
አዎ፣ በደመወዝ ላይ ያለ ማንኛውም ሰው እንደ ሰራተኛ ይቆጠራል።
11. የሱቅ ፊት ለፊት ደህንነት ፈንድ የገንዘብ ምንጭ ምንድን ነው?
የሱቅ ፊት ደህንነት ፈንድ የሚሸፈነው በደመወዝ ወጭ ታክስ (Payroll Expense Tax) ነው።
12. አመልካቾች አንድ ነገር ከመግዛታቸው በፊት ገንዘቡን ማግኘት ይችላሉ?
አይ። ወደ ንግድ ሥራ መመለስ ፕሮግራም የሚሠራው በማካካሻ ሞዴል ነው፣ ይህም ማለት አመልካቾች አስቀድመው መሣሪያዎችን ገዝተዋል ወይም ለጥገና ክፍያ ከፍለዋል ማለት ነው።
13. አመልካቾች ገንዘቡን እንዴት ነው የሚያገኙት?
ብቁ አመልካቾች ቼክ በፖስታ ይላክላቸዋል። አስፈላጊ ከሆነ ቼኮችን በአካል የመቀበል አማራጭ ይኖርዎታል።