This content has been professionally translated in other languages.
Este contenido ha sido traducido profesionalmente a otros idiomas.
此內容已被專業翻譯成其他語言。
Nội dung này đã được dịch chuyên nghiệp sang các ngôn ngữ khác.
Qoraalkan waxaa si xirfad leh loogu turjumay luqado kale.
Ang nilalamang ito ay propesyonal na isinalin sa ibang mga wika.
이 콘텐츠는 전문적으로 다른 언어로 번역되었습니다.
ይህ ይዘት በሙያዊ በሌሎች ቋንቋዎች ተተርጉሟል።
የአሰሪ መብቶች እና ኃላፊነቶች
- የሰራተኛ ደረጃዎች ጽሕፈት ቤት (OLS) የከተማዋን የሰራተኛ ደንቦች ለዝቅተኛ ደመወዝ፣ ለሚከፈልበት የሕመም እና የደህንነት ፈቃድ፣ ለደመወዝ ስርቆት፣ ለፍትሃዊ እድል ስራ (የወንጀል ታሪክ አጠቃቀምን የሚቆጣጠር) እና ከተማዋ ወደፊት ልታወጣቸው ለምትችላቸው ሌሎች ህጎች ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ አለበት። ተጨማሪ የሰራተኛ ደንቦች እና አዳዲስ ህጎች በድረ-ገጻቸው ላይ ማግኘት ይችላሉ።
- የየሰራተኛ ደረጃዎች ጽሕፈት ቤት (OLS) በሲያትል ህጎች ስር ከሚሸፈኑ ንግዶች እና ግለሰቦች ስለ ሲያትል የሰራተኛ ደረጃዎች ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጡ የተመደቡ ሰራተኞች አሉት። እነዚህ ውይይቶች የግል ናቸው እና ማንነትዎ እና የንግድ ስምዎ ከእኛ አስፈጻሚ ቡድን ጋር አይጋሩም።
- ተጨማሪ ድጋፍ ከፈለጉ፣ እባክዎን laborstandards@seattle.gov ያግኙ።
ንግድዎን ለማሳደግ የሚረዱ የከተማ መሳሪያዎች
- የሂሳብ አያያዝ እና የንግድ ምክክር ፕሮግራም፡- የእኛ የሂሳብ አያያዝ እና የንግድ ምክክር ፕሮግራም በሲያትል ላሉ አነስተኛ ንግዶች ከባለሙያ አማካሪዎች እስከ 10 ሰአታት የሚደርስ ነፃ እርዳታ ይሰጣል። ተቋሙ የፋይናንስ ፍሰትን በማስተዳደር፣ የንግድና የማርኬቲንግ ስትራቴጂዎችን በማዘጋጀት እንዲሁም የብድር አቅምን (ክሬዲትን) በማሳደግ ረገድ አስፈላጊውን ድጋፍ ያቀርባል። ዓላማው የንግድ ተቋማት ይበልጥ ዘላቂ በሆነ መንገድ እንዲሰሩ፣ ገቢያቸውን እንዲጨምሩ እና አጠቃላይ የፋይናንስ አስተዳደር ልምዶቻቸውን እንዲያሻሽሉ መርዳት ነው።
- የንግድ ቦታ የማማከር ፕሮግራም (Commercial Space Consulting Program)፡- የንግድ ቦታ የማማከር ፕሮግራም ብቁ ለሆኑ ንግዶች ከአከራዮች ጋር ለመደራደር፣ የወጥ ቤት ስራዎችን ለማከናወን እና ለንግድዎ የሚሆን የንግድ ቦታ ለማግኘት 10 ነፃ የምክክር ሰአታት ይሰጣል።
- የአነስተኛ ንግድ የህግ ድጋፍ ፕሮግራም፡- የአነስተኛ ንግድ የህግ ድጋፍ ፕሮግራም በሲያትል ከተማ ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ አነስተኛ የንግድ ድርጅቶች ነፃ የግል የሕግ ማማከር አገልግሎት እና ሙያዊ የሕግ ግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠናዎችን ያመቻቻል። የዘርፉ የሕግ ባለሙያዎች የንግድ ድርጅትን ከባለቤትነትና ከዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ጋር ተያይዘው የሚመጡ ውስብስብ ሕጋዊ ጉዳዮችን በማቃለልና በመምራት ረገድ አስፈላጊውን ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋሉ። እንዲሁም በኮርፖሬት እና በአእምሯዊ ንብረት፣ በንግድ ኪራይ ውሎች እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ሊረዱ ይችላሉ።
- የአነስተኛ ንግድ ካፒታል ተደራሽነት ፕሮግራም፡- የእኛ የካፒታል ተደራሽነት ፕሮግራም በተለይም የፋይናንስ አገልግሎት አግኝተው በማያውቁ ማህበረሰቦች ውስጥ ተመጣጣኝ ብድሮችን እና ፋይናንስን ተደራሽነት በማሻሻል አነስተኛ ንግዶችን ይደግፋል። ብቁ ለሆኑ ብድሮች እና ሌሎች የፋይናንስ አማራጮች ላይ የዋና ዕዳ ቅናሽ በማድረግ የገንዘብ ድጋፍ ለመስጠት ከማህበረሰብ አበዳሪዎች ጋር እንሰራለን።
- የተከራይ ማሻሻያ ፕሮግራም፡- የእኛ የተከራይ ማሻሻያ ፕሮግራም ድርጅቶች በያዟቸው ቦታዎች ላይ አስፈላጊውን የማሻሻያና የማደስ ሥራዎችን ማከናወን እንዲችሉ እንደ ፍላጎታቸውና እንደ ዝግጁነታቸው ደረጃ የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ ያመቻቻል። ይህ ፕሮግራም አዳዲስ የመሳሪያ ግዢ ወጪዎችን ለመቀነስ የሚረዳ በመሆኑ የንግድ ተቋማት በዕድገታቸው እና ገቢያቸውን በማሳደግ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል።