ንግድን መዝጋት

Illustration of red food cart with two people smiling and one holding pastry.

This content has been professionally translated in other languages.

Este contenido ha sido traducido profesionalmente a otros idiomas.

此內容已被專業翻譯成其他語言。

Nội dung này đã được dịch chuyên nghiệp sang các ngôn ngữ khác.

Qoraalkan waxaa si xirfad leh loogu turjumay luqado kale.

Ang nilalamang ito ay propesyonal na isinalin sa ibang mga wika.

이 콘텐츠는 전문적으로 다른 언어로 번역되었습니다.

ይህ ይዘት በሙያዊ በሌሎች ቋንቋዎች ተተርጉሟል።

ወደ ክፍሉ ይሸጋገሩ፦

  1. የንግድ መውጫ ስልቶች
  2. ንግድን ለመዝጋት የሚያስፈልጉ የቼክሊስት ዝርዝሮች
  3. ንግድዎን ለመልቀቅ የሚያግዙ የህዝብ ሀብቶች
  4. ማሳወቅ ያለባቸው የቁጥጥር ኤጀንሲዎች፡- የሲያትል ከተማ
  5. ማሳወቅ ያለባቸው የቁጥጥር ኤጀንሲዎች፡- ካውንቲ፣ ስቴት እና ፌዴራል

የንግድ መውጫ ስልቶች

  • ንግድዎን ለመልቀቅ የተለያዩ መንገዶች አሉ። እንደ ሁኔታዎ፣ የሚያዘጋጁት ስልት የሚከተሉትን ነጥቦች በውስጡ ሊያካትት ይችላል፦
    • ንግዱን በቤተሰብ ውስጥ ማቆየት
    • በሰራተኞች ባለቤትነት የሚተዳደር ህብረት ስራ ማህበር ወይም የሰራተኞች የአክሲዮን ባለቤትነት እቅድ መፍጠር
    • ንግዱን በግልጽ ገበያ መሸጥ
    • ንግዱን ለሌላ ንግድ መሸጥ (ግዢ)
    • ውህደት
    • ንብረትን ወደ ገንዘብ መቀየር (Liquidation)
    • ለኪሳራ ማመልከት
  • የሚመርጡት ስልት ንግድዎን ለማቆም/ለማስተላለፍ መከተል ያለብዎትን እርምጃዎች ይወስናል።

ንግድን ለመዝጋት የሚያስፈልጉ የቼክሊስት ዝርዝሮች

  • የህግ ምክር ይጠይቁ፦ ንግድዎን እንዴት መዝጋት እንደሚችሉ መረዳትዎን ያረጋግጡ። ይህ እዳዎችን፣ ውሎችን፣ ማሳወቂያዎችን እና መከተል ያለብዎትን ማንኛውንም ህጎች መቋቋምን ያካትታል። እነዚህን መስፈርቶች ማወቅ ቀጣይ እርምጃዎችዎን ለማቀድ ይረዳዎታል።
  • የቁጥጥር ኤጀንሲዎችን ያሳውቁ፦ መለያዎችዎ በትክክል መዘጋታቸውን ወይም መተላለፋቸውን ለማረጋገጥ ፈቃድ እና ፍቃድ የሰጡዎትን ሁሉንም የመንግስት ኤጀንሲዎች ያነጋግሩ
    • ፌዴራል
    • ግዛት/ስቴት
    • ካውንቲ (ወይም ካውንቲዎች፣ በተለያዩ ካውንቲዎች ውስጥ ብዙ ፈቃዶች ካሉዎት)
    • ከተማ (ወይም ከተሞች፣ በተለያዩ ከተሞች ውስጥ ብዙ የንግድ ፈቃዶች ካለዎት)
  • ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት ያሳውቁ፦ ክፍያ መፈጸሙን በማረጋገጥ ወይም የሚጠበቅብዎትን ገንዘብ እንዴት እና መቼ እንደሚከፍሉ በመግለጽ ለሚመለከታቸው ሰዎች እና አጋሮች ያሳውቁ
    • ደንበኞች
    • ሰራተኞች
    • ኢንሹራንስ ሰጪዎች
    • አከራዮች
    • አበዳሪዎች
    • የአገልግሎት አቅራቢዎች
    • ሻጮች
  • በሞት ምክንያት የንግድ ስራ መዘጋት፦ እነዚህ የስቴት ኤጀንሲዎች በሞት ምክንያት ሲዘጉ ንግድ ስራ መከተል ያለበት ልዩ ሂደት አላቸው፦
    • የሰራተኛ እና ኢንዱስትሪዎች መምሪያ
    • የፈቃድ አሰጣጥ መምሪያ
    • የገቢዎች መምሪያ፡ የንግድ ፈቃድ አገልግሎቶች ታክስ
    • የቅጥር ደህንነት መምሪያ
    • የአልኮል እና ማሪዋና ቦርድ
    • የስቴት/የግዛት ጸሐፊ

ንግድዎን ለመልቀቅ የሚያግዙ የህዝብ ሀብቶች

  • የተተኪነት አሰራር ማቀጃ መሳሪያ (Succession Planning Toolkit)፦ ከንግድ ስራዎ ለመውጣት የሚያደርጉትን እቅድ ሲያዘጋጁ ግምት ውስጥ ሊያስገቧቸው የሚገቡ ዋና ዋና ጥያቄዎችን እና መረጃዎችን፣ ስለ ንግድ ድርጅቶች ዓይነቶች እና የውርስ እቅድ (Estate Planning) አጭር ማጠቃለያ፣ እንዲሁም የመዝጋት ሂደቱን ለማደራጀት የሚረዳዎትን የተግባር ቅጽ (Worksheet) ያካተተ የተተኪነት አሰራር ማቀጃ መሳሪያ (Succession Planning Toolkit) ፈጥረናል።
  • የዋሽንግተን ስቴት ንግድዎን ይዝጉ (Close Your Business) መመሪያ፦ የስቴቱ ንግድዎን ይዝጉ መመሪያ ንግድዎን እንዴት እንደሚዘጉ መረጃ እና ሀብቶችን ጨምሮ በርካታ የንግድ ልማት ሀብቶችን ያቀርባል።
  • የሀገር ውስጥ ገቢዎች አገልግሎት (IRS)፦ የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ገቢዎች አገልግሎት (IRS) የንግድ ድርጅትዎ ዓይነት ምንም ይሁን ምን፣ ከፌደራል ታክስ አንጻር ንግድዎን የመዝጋት ሂደቱን በስኬት እንዲወጡ የሚረዱ የመረጃ ምንጮች ዝርዝር እና ሰራተኞችዎን በተገቢው መንገድ ለማሰናበት የሚረዱ መረጃዎችን አዘጋጅቷል።
  • የአሜሪካ አነስተኛ ንግድ አስተዳደር (SBA)፦ SBA የመውጫ ስልትዎን ለማቀድ የሚያስችል የአካባቢው የሙያ ድጋፍ የሚያገናኝዎ ከመሆኑም በላይ፣ ንግድዎን (ድርጅትዎን) በህጋዊ መንገድ ለመዝጋት ወይም ለመሸጥ የሚከተሏቸውን ዝርዝር እርምጃዎች ያቀርባል።

ማሳወቅ ያለባቸው የቁጥጥር ኤጀንሲዎች፡- የሲያትል ከተማ

  • የሲያትል ከተማ መብራት (SCL)፦ ስለ መለያዎ (አካውንትዎ) ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት የሲያትል ከተማ መብራት (SCL) ያሳውቁ። የSCL መለያዎን በኦንላይን ቅጽ ወይም በስልክ ቁጥር (206) 684-3000 መጀመር፣ ማቆም ወይም ማስተላለፍ ይችላሉ።
  • የሲያትል የትራንስፖርት መምሪያ (SDOT)፦ ለሕዝብ ቦታ ካፌ፣ ለሕዝብ መገልገያዎች ወይም ተመሳሳይ መዋቅሮች ማንኛቸውም ፈቃዶች ካለዎት፣ የሚጠበቀውን የመዝጊያ ቀናት፣ የንግድዎ አድራሻ እና የፈቃድ ቁጥሮችዎን በመጥቀስ ለSDOT በpublicspace@seattle.gov ኢሜይል ይላኩ። ነባሩ የፈቃድ ክፍያ መጠየቂያዎ (ቢል) መቋረጡን ለማረጋገጥ ከእርስዎ ጋር ክትትል ያደርጋሉ።
  • የሲያትል የእሳት አደጋ መከላከያ መምሪያ (SFD)፦ ከSFD ዓመታዊ ፈቃዶች ካለዎት እና ንግድዎን ለመዝጋት ወይም ሥራዎችን ለማቆም ካቀዱ፣ ማንኛውንም የስረዛ ጥያቄ በኢሜይል በpermits@seattle.gov ይላኩ።
    • በኢሜይሉ ውስጥ የሚከተለውን መረጃ ያካትቱ፦
      • የንግድ ስም
      • የፈቃድ ቁጥር ወይም የፈቃድ ዓይነት
      • የስረዛው ምክንያት
    • እንዲሁም SFD ፈቃዱ ከማለቁ አንድ ወር ገደማ በፊት በሚልከው የፈቃድ እድሳት ማሳወቂያ ላይ ምላሽ በመስጠት መሰረዝ ይችላሉ። በቅጹ ላይ ያለውን “ሰርዝ” (Cancel) ሳጥን ምልክት ያድርጉበት። የእድሳት ማሳወቂያውን ለSFD በኢሜይል ወይም በመደበኛ ደብዳቤ መልሰው መላክ ይችላሉ።
  • የሲያትል የፈቃድ እና የታክስ አስተዳደር፦ በሲያትል ውስጥ የንግድ ሥራዎን የማይቀጥሉ ከሆነ እና የንግድ ፈቃድ የታክስ ሰርቲፊኬትዎን መሰረዝ ከፈለጉ፣ ለፈቃድ እና የታክስ አስተዳደር በ ኦንላይን ቅጻቸው በኩል ያሳውቁ። እንዲሁም በኢሜይል (tax@seattle.gov) መላክ ወይም የሚከተለውን መረጃ የያዘ ደብዳቤ መላክ ይችላሉ፦ ስም፣ ስልክ ቁጥር፣ የደንበኛ ቁጥር፣ የንግዱ ህጋዊ ስም እና ንግዱ የተዘጋበት ቀን። መለያዎን (አካውንትዎን) ከዘጉ በ10 ቀናት ውስጥ የመጨረሻውን የታክስ ሪፖርት (ታክስ ሪተርን) ማቅረብ እና ያሉብዎትን ያልተከፈሉ ታክሶች በሙሉ መክፈል አለብዎት።
  • የሲያትል የሰራተኛ ደረጃዎች ጽሕፈት ቤት (OLS)
    • ሙሉ የደንቦች ዝርዝር።
    • የካናቢስ ሰራተኞች የስራ ማቆያ ደንብ የካናቢስ ንግድ ባለቤቱን ከቀየረ፣ ሰራተኞች ስራቸውን እንዲይዙ የሚረዱ ጥበቃዎች አሏቸው።
    • የሚከፈልበት የህመም እና የደህንነት ፈቃድ ደንብ(SMC 14.16)አንድ ንግድ በሌላ አዲስ አሰሪ ሲወሰድ/ሲተካ፣ ሰራተኞች ቀደም ሲል ያከማቹትን የሚከፈልበት የሕመም እና የደህንነት ፈቃድ በሙሉ ይኖራቸዋል፡፡ አዲሱ ባለቤት የሚከፈልበት የህመም እና የደህንነት ፈቃድ ደንቦችን ወዲያውኑ መከተል አለበት። በዚህ ህግ መሰረት እንደ “አዲስ አሰሪ” አይቆጠሩም።
    • የሆቴል ሰራተኞች የስራ ማቆያ ደንብ (SMC 14.29)
      • ህጉ የሚከተለውን ይጠይቃል፦
        • አሁን ያለው (ወጪው) ባለቤት ንግዱ አዲስ ባለቤት እንደሚኖረው የሚገልጽ የጽሁፍ ማስታወቂያ መስጠት አለበት።
        • የባለቤትነት ማስተላለፊያ ሰነዶች ከተፈረሙ በኋላ በአምስት የስራ ቀናት ውስጥ፣ ነባሩ (ወጪው) ባለቤት ማሳወቂያውን ሰራተኞች እና የስራ አመልካቾች በቀላሉ ሊያዩት በሚችሉበት ቦታ መለጠፍ አለበት።
        • ነባሩ ባለቤት ለአዲሱ (ተረካቢ) ባለቤት በቅድሚያ የስራ እድል ሊሰጣቸው የሚገቡ ሰራተኞችን ዝርዝር መስጠት አለበት።
        • በአዲሱ ባለቤት ስር ለህዝብ ክፍት ከተደረገ በኋላ ባሉት የመጀመሪያዎቹ 180 ቀናት ውስጥ፣ አዲሱ ባለቤት ሌላ ሰው ከመቅጠሩ በፊት በዚያ ዝርዝር ውስጥ ላሉ ሰዎች የስራ እድል መስጠት አለበት።
  • የሲያትል የህዝብ መገልገያ (SPU)፦ ስለ ውሃ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ እና የቆሻሻ ውሃ፣ እና የደረቅ ቆሻሻ አገልግሎቶችዎ ማንኛቸውም ጥያቄዎች ካሉዎት ለSPU ያሳውቁ። የSPU መለያዎችዎን በኦንላይን ቅጻቸው ወይም በስልክ ቁጥር (206) 684-3000 መክፈት፣ መዝጋት ወይም ማዛወር ይችላሉ።

ማሳወቅ ያለባቸው የቁጥጥር ኤጀንሲዎች፡- ካውንቲ፣ ስቴት እና ፌዴራል

Economic Development

Beto Yarce, Director
Address: 700 5th Ave, Suite 5752, Seattle, WA, 98104
Mailing Address: PO Box 94708, Seattle, WA, 98124-4708
Phone: (206) 684-8090
Fax: (206) 684-0379
oed@seattle.gov

Sign Up for Latest Updates

Subscribe

Our core purpose is leading projects and making investments that open up access to economic opportunities, reduce the racial wealth gap, and encourage innovation and growth.