This content has been professionally translated in other languages.
Este contenido ha sido traducido profesionalmente a otros idiomas.
此內容已被專業翻譯成其他語言。
Nội dung này đã được dịch chuyên nghiệp sang các ngôn ngữ khác.
Qoraalkan waxaa si xirfad leh loogu turjumay luqado kale.
Ang nilalamang ito ay propesyonal na isinalin sa ibang mga wika.
이 콘텐츠는 전문적으로 다른 언어로 번역되었습니다.
ይህ ይዘት በሙያዊ በሌሎች ቋንቋዎች ተተርጉሟል።
ለንግድ ቦታዎ የኮንስትራክሽን ፈቃድ የማማከር/የስልጠና አገልግሎት ይፈልጋሉ?
- ከየሲያትል የግንባታ እና ቁጥጥር መምሪያ (SDCI) ጋር በመተባበር፣ ብቁ ለሆኑ አነስተኛ ንግዶች የንግድ ቦታ ፈቃዶችን እና ፈጣን አገልግሎቶችንእንዲያገኙ እገዛ እናደርጋለን። የግንባታ ፍላጎቶች ጥናትን፣ የቀደመ የፈቃድ አሰጣጥ መመሪያን እንዲሁም ፈጣን የፈቃድ አሰጣጥን በተመለከተ ድጋፍ እናቀርባለን።
የግንባታ፣ የንግድ፣ የመሬት አጠቃቀም እና በቦታው ላይ ምርመራ የሚደረግባቸው ፈቃዶች
- በሲያትል ውስጥ ብዙ ፕሮጀክቶች ፈቃድ ይፈልጋሉ። የፕሮጀክቶች አይነቶች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ ነገር ግን በእነዚህ ብቻ አይወሰኑም፡ የንግድ ቦታን መገንባት ወይም ማደስ፣ የHVAC ስርዓቶችን እና የወጥ ቤት መከለያዎችን መትከል፣ የኤሌክትሪክ ስርዓቶችን መትከል እና ሌሎችም።
- የህንጻ አጠቃቀም ፈቃዶች
- የግንባታ ፈቃዶች
- በቦታው ላይ ምርመራ የሚደረግባቸው ፈቃዶች
- የንግድ ፈቃዶች
የሲያትል እሳት አደጋ መከላከል መምሪያ ፈቃዶች
- የሲያትል የእሳት አደጋ ህግ ፈቃድ የሚጠይቁ ስራዎችን፣ እንቅስቃሴዎችን እና ቁሳቁሶችን ይለያል። የእሳት አደጋ መከላከያ መምሪያ ፈቃዶች ለልዩ ዝግጅቶች፣ ሰዎች ለሚሰበሰቡባቸው ትላልቅ የህንጻ ቦታዎች፣ አደገኛ ቁሳቁሶችን ለማከማቸት ወይም ለመጠቀም፣ እንደ ትኩስ ስራ (hot work) እና የሚረጭ ማጠናቀቂያ (spray finishing) ላሉ አደገኛ ስራዎች፣ ከፍተኛ ክምር ያላቸው ተቀጣጣይ ቁሳቁሶችን ለማከማቸት እና የእሳት ወይም የደህንነት ስጋት ሊፈጥሩ ለሚችሉ ሌሎች እንቅስቃሴዎች መገኘት አለባቸው።
- የሲያትል እሳት አደጋ መከላከል መምሪያ አብዛኛውን ጊዜ በዓመት አንድ ጊዜ የብዙ ቤተሰብ መኖሪያዎች፣ የንግድ እና የኢንዱስትሪ ህንፃዎችን ነፃ ኢንስፔክሽን (ምርመራ) ያካሂዳል። የምርመራው ግብ የእሳት አደጋዎችን ቁጥር እና ክብደት መቀነስ ነው። ስለ ምርመራ ፕሮግራሙ እና ምርመራውን ለማለፍ እና ህንጻዎን ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ ሊወስዷቸው ስለሚችሉ እርምጃዎች የበለጠ ለማወቅ፣ እባክዎ በበርካታ ቋንቋዎች የሚገኘውን የደንበኞች ድጋፍ ማስታወሻ (Client Assistance Memorandum) 5969 ይመልከቱ።
የህዝብ ማለፊያ መስመር/መንገድ፡ የመንገድ አጠቃቀም ፈቃዶች ፦
- የሲያትል ከተማ መንገዶች፣ የእግረኛ መንገድ መተላለፊያዎች፣ አደባባዮችና የጓሮ መንገዶች (alleys) የከተማዋ የህዝብ ማለፊያ መስመር (Public Right-of-Way) አካል ናቸው። ከእነዚህ ቦታዎች አንዱን ጥቅም ላይ በማዋል ማነቃቃትና ማልማት ይፈልጋሉ? በሕዝብ መተላለፊያ መንገድ ውስጥ ከመሥራትዎ ወይም ከመጠቀምዎ በፊት ፈቃድ ያስፈልግዎታል። ፈቃዶች እነዚህን ቦታዎች ለሁሉም ሰው ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ተደራሽ እና በጥሩ ሁኔታ እንዲቆዩ ያደርጋሉ።
- የመንገድ አጠቃቀም ፈቃዶች ሰፈርዎን የተሻለ ለማድረግ ይህንን ቦታ እንዲጠቀሙ ያስችልዎታል። ዝግጅቶችን ማስተናገድ፣ የእግረኛ መንገድ ካፌ መክፈት ወይም ሰዎችን እንዲሰበሰቡ የሚጋብዙ ተጨማሪ ነገሮችን ማከል ይችላሉ።
- እነዚህ ተግባራት ማህበረሰብዎን በተጨባጭ መንገድ ያጠናክራሉ። ማህበራዊ ግንኙነትን ያነሳሳሉ፣ የአካባቢው ንግዶች እንዲያድጉ ይረዳሉ፣ እንዲሁም መንገዶቻችንን የበለጠ ደህንነታችው የተጠበቀ እና እንግዳ ተቀባይ ያደርጋሉ።
- የመንገድ ላይ የምግብ ሽያጭ
- የውጪ መቀመጫዎች፡
- የማህበረሰብ ማነቃቂያ ለማህበረሰብ ወይም ለንግድ ስብሰባዎች እና ለሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች፡
- የተለመዱ የማህበረሰብ እንቅስቃሴዎች፦ የሰፈር ነዋሪዎች ዝግጅቶችን (የብሎክ ፓርቲዎች) እና የመጫወቻ መንገዶች፣ የጎረቤታሞች ስብሰባዎች ወይም በዓላት፣ እንዲሁም እንደ ጎዳና ላይ ባዛሮች ያሉ የመንገድ እና የእግረኛ መንገድ ዝግጅቶችን ያካትታሉ
- በሕዝብ መተላለፊያ መንገድ ውስጥ ያሉ የግል መዋቅሮች (አጥሮች፣ የድንጋይ ክምሮች፣ በረንዳዎች፣ ግድግዳዎች፣ ወዘተ.)
- የሸቀጣሸቀጥ ማሳያ
- የሕዝብ መገልገያዎች (የአበባ ማስቀመጫዎች፣ ጥበብ፣ የሕዝብ መቀመጫዎች፣ ወዘተ.)
በታሪካዊ ወረዳዎች ውስጥ ልዩ የግምገማ እና የማጽደቅ ሂደቶች
- ሲያትል ስምንት ታሪካዊ ወረዳዎች አሏት። በእነዚህ ወረዳዎች ውስጥ ያሉ ሕንፃዎች እና የሕዝብ ቦታዎች ታሪካዊ ገጽታቸውን እና ባህሪያቸውን ለመጠበቅ ልዩ ደንቦችን መከተል አለባቸው። የዜጎች ቦርድ ወይም የቅርስ ጥበቃ ቦርድ በእነዚህ ወረዳዎች ውስጥ የሚደረጉ ለውጦችን በከተማው ህግ የተቀመጡትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ይገመግማሉ። አንዳንድ ታሪካዊ ወረዳዎች በሌሎች ልዩ የግምገማ እና የማጽደቅ ሂደቶች ስርም ያልፋሉ።