Amharic / አማርኛ
በሲያትል ምርጫዎች ላይ ድምፅዎ እንዲሰማ ያድርጉ
የዲሞክራሲ ቫውቸሮች የሲያትል ነዋሪዎች በሲያትል ከተማ ምርጫ ለሚደግፏቸው እጩዎች የገንዘብ መዋጮ የሚያደርጉበት መንገድ ነው። ፕሮግራሙ በመራጭ በተፈቀደ የንብረት ታክስ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት ሲሆን ይህም አማካይ የንብረት ባለቤት በዓመት 8 ዶላር ያህል ያስወጣል።
የዴሞክራሲ ቫውቸር ምንድን ነው?
የሲያትል ከተማ ለነዋሪዎች የዴሞክራሲ ቫውቸሮችን ያቀርባል። የዲሞክራሲ ቫውቸር የሲያትል ነዋሪዎች ለአካባቢው የምርጫ ዘመቻዎች ለመለገስ የሚጠቀሙባቸው እያንዳንዳቸው ባለ 25 ዶላር የምስክር ወረቀቶች ናቸው።
ለምን የዲሞክራሲ ቫውቸሮችን ይጠቀማሉ?
የእርስዎ ተሳትፎ ተጽዕኖ ያሳድራል። የዲሞክራሲ ቫውቸር ፕሮግራም የሲያትል ነዋሪዎችን ለዘመቻዎች መለገስ እና ለምርጫ መወዳደር የሚችሉትን ቁጥር እና ብዝሃነትን ለመጨመር ረድቷል።
የዴሞክራሲ ቫውቸር መቀበል የሚችሉት የትኛዎቹ የምርጫ ተወዳደሪዎች ናቸው?
ለከተማ ምክር ቤት፣ ለከተማ ጠበቃ፣ ወይም ለሲያትል ከንቲባ የሚወዳደሩ ተሳታፊ እጩዎች ብቻ ናቸው ዘመቻዎቻቸውን ለመደገፍ ቫውቸርዎን መቀበል የሚችሉት።
ስለ እጩዎቹ እንዴት ማወቅ እችላለሁ?
ተሳታፊ እጩ ተወዳዳሪን በ ተሳታፊ እጩ ተወዳዳሪዎች ገፅ ላይ ያግኙ። ስለ እጩዎቹ የበለጠ ለማወቅ የእጩ መግቢያዎቻቸውን ያንብቡ።
ቀጣዩ የሲያትል ከተማ ምርጫ የሚካሄደው መቼ ነው?
ቀጣዩ የሲያትል ከተማ ምርጫ የሚካሄደው በ2025 ነው። የዲሞክራሲ ቫውቸሮችን ከተቀበሉበት ጊዜ አንስቶ እስከ ህዳር 29፣ 2025 ድረስ መጠቀም ይችላሉ።
የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ከሆነ የዴሞክራሲ ቫውቸርን መቀበል ይችላሉ:
- የሲያትል ነዋሪ፣
- ቢያንስ የ18 ዓመታት ዕድሜ፣ እና
- የዩ ኤስ አሜሪካ ዜጋ፣ አሜሪካዊ፣ ወይም ሕጋዊ ቋሚ ነዋሪ።
የዲሞክራሲ ቫውቸሮችን ለመቀበል የተመዘገበ መራጭ መሆን አያስፈልግም። ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ከሆነ ቫውቸሮችን ለመቀበል ማመልከት ይችላሉ።
ማንኛውም አይነት ጥያቄ ካለዎት እባክዎን (206) 727-8855 ይደውሉ። ነፃ የቋንቋ ትርጉም አገልግሎት አለ።
ከማህበረሰብህ ጋር ለመጋራት እነዚህን ቁሳቁሶች ማውረድ ወይም ማተም ትችላለህ።