የመገልገያ ፍጆታ ክፍያዎችን ለመክፈል እገዛ ይፈልጋሉ?

በሲያትል የከተማ መብራት ወይም በሲያትል የህዝብ መገልገያ ሂሳብ ክፍያ ወደኋላ ነዎት? 

እኛ ለመርዳት እዚህ አለን! የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለአንዳንድ ደንበኞቻችን አስፈላጊ የሆኑ የመገልገያ ፍጆታ አገልግሎቶችን መግዛት አስቸጋሪ እንዳደረገው እናውቃለን።  አስፈላጊ የመገልገያ ፍጆታ አገልግሎቶችን መቀበልዎን ለመቀጠል እንዲረዳዎ፣ እና የመክፈያ አማራጮችን እና ያለዎትን ቀሪ ሂሳቦች ለመክፈል እንዲረዳዎ የሂሳብ ድጋፍ ፕሮግራሞችን እናቀርባለን።  

የክፍያ ዕቅዶች

የሲያትል ከተማ ብርሃን እና የሲያትል የህዝብ መገልገያ ክፍያ ዕቅዶች

በሲያትል ከተማ መብራት (ኤሌክትሪክ) እና በሲያትል የህዝብ መገልገያዎች (ውሃ፣ ፍሳሽ እና ቆሻሻ) የመገልገያ ፍጆታ ሂሳቦችዎ አልፎብዎት ከሆነ፣ ለሁሉም የነዋሪዎች እና የንግድ ደንበኞች የአጭር እና የረጅም ጊዜ የክፍያ እቅዶችን ያቀርባሉ። በክፍያ እቅድ፣ በጊዜ ሂደት ቀሪ ሂሳብዎን ትንሽ በትንሽ ክፍል መክፈል ይችላሉ። አዲሶቹን የመገልገያ ፍጆታ ሂሳቦችን እና የክፍያ እቅድ ክፍያዎችን በሰዓቱ በመክፈል፣ ባለመክፈል አገልግሎቶችን ማቋረጥ እንደገና ስንጀምር የርስዎ የመገልገያ ፍጆታ አገልግሎቶችን ያቆያሉ።

የክፍያ ሂሳብ እርዳታ ፕሮግራሞች

የመኖሪያ ቤት ደንበኛ ከሆኑ እና የገቢ ብቁነት መስፈርቶችን ካሟሉ ለቀጣይ እና ለአደጋ ጊዜ የክፍያ መጠየቂያ እርዳታ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።

የመገልገያ ፍጆታ ቅናሽ ፕሮግራም 

ለወደፊቱ የሲያትል ከተማ ብርሃን ሂሳቦችን 60% ቅናሽ እና ለወደፊቱ የሲያትል የህዝብ መገልገያ ክፍያዎችን 50% ቅናሽ የሚያሰጥ፣ በገቢ ብቁ የሆኑ ደንበኞች በሲያትል ከተማ የመገልገያ ፍጆታ ቅናሽ ፕሮግራም መመዝገብ ይችላሉ።

የአደጋ ጊዜ የክፍያ ሂሳብ እርዳታ ፕሮግራሞች

የሲያትል ከተማ መብራት

ከ$250 ዶላር ወይም ከዚያ በላይ የኤሌክትሪክ ቀሪ ሂሳብ ክፍያዎ አልፎብዎት ከሆነ ወይም የመዘጋት አደጋ ካጋጠመዎት፣ የሲያትል ከተማ መብራት የአደጋ ጊዜ ቢል እርዳታ ፕሮግራም ሊረዳዎ ይችላል። ያለፉትን ቀሪ ሂሳባቸውን ለመቀነስ (በሁለት $710 ዶላር ክሬዲት ይከፋፈላል)፣ ለገቢ ብቁ የሆኑ ደንበኞች በአመት እስከ $1,420 በአፋጣኝ፣ የአደጋ ጊዜ ዕርዳታ ሊያገኙ ይችላሉ።

የሲያትል የሕዝብ መገልገያዎች (SPU)

የውሃ/የፍሳሽ/ቆሻሻ የክፍያ ሒሳብዎን ወደ ኋላ ቀርተው ከሆነ እና የመዘጋት ስጋት ካጋጠመዎት የሲያትል የህዝብ መገልገያ አስቸኳይ እርዳታ ፕሮግራም ሊረዳዎ ይችላል። በገቢ ብቁ የሆኑ ደንበኞች በአመት እስከ $1074 ዶላር በአፋጣኝ ሊያገኙ ይችላሉ፣ የአደጋ ጊዜ ርዳታ ያለፈውን ቀሪ ሂሳባቸውን ለመቀነስ (በሁለት $537 ዶላር ክሬዲት ይከፋፈላል)።

አሁኑኑ ያመልክቱ

አግኙን

በመገልገያ ፍጆታ የክፍያ ሂሳቦች ወደ ኋላ ከቀሩ ወይም በየወሩ ክፍያዎችን ለመፈጸም እየታገሉ ከሆነ፣ የመገልገያ አገልግሎቶችዎን ለማቆየት፣ የክፍያ እቅድ ለማዘጋጀት እና ለክፍያ መጠየቂያ እርዳታ ለማመልከት ከእርስዎ ጋር ልንሰራ እንችላለን።

ለደንበኛ አገልግሎት ቡድናችን ይደውሉ

ክፍያ ለመፈጸም፣ የክፍያ እቅድ ስለማዘጋጀት ተወካይ ለማነጋገር፣ ወይም ለክፍያ መጠየቂያ ፕሮግራሞች ለማመልከት (ከሰኞ እስከ አርብ፤ ከጠዋቱ 7፡30 - 6፡00 ምሽት) በ (206) 684-3000 ይደውሉልን። ከእንግሊዝኛ ውጭ በሌላ ቋንቋ እርዳታ ከፈለጉ የደንበኛ እንክብካቤ ቡድናችን በመረጡት ቋንቋ ያለምንም ወጪ ይረዳዎታል።

የደንበኛ አገልግሎት ማዕከሎቻችንን ይጎብኙ 

የክፍያ ሂሳቦችዎን በአካል፣ በጥሬ ገንዘብ፣ በቼክ ወይም በክሬዲት ካርድ ለመክፈል የደንበኛ አገልግሎት ማዕከልን ይጎብኙ።

  • የሲያትል ከተማ መብራት የሰሜን አገልግሎት ማዕከል
    1300 N 97th Street, Seattle, WA 98103 | ሰኞ – አርብ፤ ከጧት 8:30 – 4:30 ከሰዓት | (206) 615-0600
  • የሲያትል ከተማ መብራት የደቡብ አገልግሎት ማዕከል
    3613 4th Avenue S, Seattle, WA 98134 | ሰኞ – አርብ፤ ከጧት 8:30 – 4:30 ከሰዓት | (206) 386-4200
  • ባላርድ የአገልግሎት ማዕከል
    5604 22nd Ave NW, Seattle, WA 98107 | ማክሰኞ – አርብ፤ ከጧት 9:00 – 5:00 ከሰዓት | (206) 684-4060
  • የማዕከላዊ ወረዳ አገልግሎት ማዕከል
    464 12th Avenue, First Fl, Seattle, WA 98122 | ማክሰኞ – አርብ፤ ከጧት 9:00 – 5:00 ከሰዓት | (206) 684-4767
  • የመሃል ከተማ የአገልግሎት ማዕከል
    700 Fifth Avenue, Seattle, WA 98104 | ሰኞ – አርብ፤ ከጧት 8:30 – 4:00 ከሰዓት | (206) 684-3000
  • የሌክ ሲቲ አገልግሎት ማዕከል
    12525 28th Ave NE, 2nd Fl, Seattle, WA 98125 | ማክሰኞ – ቅዳሜ፤ ከጧት 9:00 – 5:00 ከሰዓት | (206) 684-7526
  • የደቡብ ምስራቅ አገልግሎት ማዕከል
    3815 S Othello St, Suite 105, Seattle, WA 98118 | ሰኞ – ቅዳሜ፤ ከጧት 9:00 – 5:00 ከሰዓት | (206) 386-1931
  • የደቡብ ምዕራብ አገልግሎት ማዕከል
    2801 SW Thistle St, Seattle, WA 98126 | ሰኞ – አርብ፤ ከጧት 9፡00 – 5:00 ከሰዓት | (206) 684-7417
  • የዩኒቨርሲቲ አገልግሎት ማዕከል
    4534 University Way NE, Seattle, WA 98105 | ማክሰኞ – ቅዳሜ፤ ከጧት 9:00 – 5:00 ከሰዓት | (206) 684-7542