የስያትል ኮቪድ-19 (COVID-19) ስደተኞች ኣስቸኻይ እርዳታ ፈንድ (2021 ዳግም ማረጋገጫ ቅጽ)

English
አማርኛ
简体中文
한국어
Soomaali
Español
Tagalog
Tiếng Việt

ከሲያትል የአደጋ እርዳታ ፈንድ ቡድን የቴክስት መልዕክት ወይም ኢሜይል ደርሶዎት ይሆናል።


እባክዎን በመልዕክቱ ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች ይከተሉ። ለመጀመሪያው የሲያትል የአደጋ ጊዜ እርዳታ ፈንድ አመልክተውና ብቁ ለሆኑትና፣ ብቁ ሆነው ለሚቀጥሉ ግለሰቦች የሲያትል ከተማ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል። የስኮላርሺፕ ጃንኪስ ድርጅት (Scholarship Junkies) ለኦክቶበር 2020 የሲያትል የአደጋ ድጋፍ ፈንድ ብቁ የሆኑን አመልካቾች እያገኛቸው ነው።

የአመልካች ሁኔታዎች ተለውጠዉ ሊሆን ስለሚችል ለዚህ ተጨማሪ ዙር የገንዘብ ድጋፍ ብቃታቸውን እያረጋገጡ ነው።


መረጃዎን ለማረጋገጥ ደህንነቱ የተጠበቀ መታወቂያዎን (Secure ID) ይጠቀማሉ። ይህ ደህንነቱ የተጠበቀ መታወቂያ (Secure ID) ለእርስዎ ብቻ ልዩ የሆነ ነው፣ እባክዎን አያጋሩ።

የሚከተለውን መረጃ ማረጋገጥ ያስፈልግዎታል፡

  • የእርስዎን ስም፣ የትውልድ ቀን እና አድራሻ
  • የቤተሰብዎ መጠን (ራስዎን ሳይጨምር የአዋቂዎች ብዛት፣ እና በቤተሰብዎ ውስጥ ከ 18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ብዛት)፤
  • የቤተሰብዎን ወርሐዊ ገቢ፤
  • ተመራጭ የመክፈያ ዘዴ።

ጥያቄ ካለዎት፣ እባክዎን ወደ (206) 312-1630 ይደውሉ ወይም ቴክስት ያድርጉ ወይም ወደupdate@seattlecovidfund.org ኢሜይል ያድርጉ።