የመደብር የፊት ለፊት ገጽታ ጥገና የገንዘብ ድጋፍ

የኢኮኖሚያዊ ልማት ጽህፈት ቤት (Office of Economic Development) በንብረት ላይ ጉዳት ለደረሰባቸው ትናንሽ የንግድ ተቋማት በኢኮኖሚ እንደገና ማገገም እንዲችሉ ለመርዳት ወደ 2 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የፌደራል የድጋፍ ገንዘብ መዋዕለ ንዋይ እያደረገ ነው። በመደብር የፊት ለፊት ገጽታ ጥገና የገንዘብ ድጋፍ በኩል፣ ትናንሽ የንግድ ተቋማት ከጥር 1 ቀን 2021 ጀምሮ ወይም ከዚያ በኋላ የመደብር የፊት ለፊት ገጽታ ንብረቶች ላይ ያጋጠሙትን ጉዳቶች ለመጠገን የሚያግዝ የ $2,000 ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ።

የማመልከቻ መቀበያዎች ጥቅምት 18 ቀን 2022 ጀምረው ክፍት ይሆናሉ። የእኛ ቢሮ የገንዘብ ድጋፍ ሁሉ ወጪ ተደርጎ እስኪያልቅ ድረስ ከአነስተኛ የንግድ ተቋማት የሚመጡ ማመልከቻዎችን በቀጣይነት ይቀበላል። እባክዎን ከማመልከትዎ በፊት ከታች ያለውን መረጃ ይከልሱ።

ማመልከቻው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተዘጋጅቶ በመስመር ላይ/ኦንላይን ገቢ መደረግ አለበት። ማመልከቻዎን እንዲያጠናቅቁ ለመርዳት የሁለት ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ሰራተኞች ይገኛሉ፣ በተጨማሪም ከዚህ በታች ያሉትን የማመልከቻ ጥያቄዎች አስቀድመው ማየት ይችላሉ። የትርጉም ወይም የአስተርጓሚ አገልግሎቶችን ለመጠየቅ፣ እባክዎን (206) 684-8090 ይደውሉ።

እዚህ ያመልክቱ

ምን ዓይነት የንብረት ጉዳት ነው መስፈርቱን የሚያሟላው?

የመደብር የፊት ለፊት ገጽታ ጥገና የገንዘብ ድጋፎች አሁን ላይ ላጋጠመ የንብረት ጉዳት ወይም ያለፉት የንብረት ጉዳቶች ለመጠገን ከኪስ ወጪ ተደርጎ የተከፈለውን ገንዘብ መልሶ ለመክፈል ብቻ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ።

መስፈርቱን የሚያሟሉ የንብረት ጉዳቶች የተሰበሩ መስኮቶች፣ የተሰበሩ በሮች፣ የተሰበሩ መቆለፊያዎች እና በመስኮቶች ዙሪያ ያጋጠሙ መጋጋጦችን ያካትታሉ።

ይህ የገንዘብ ድጋፍ የመከላከል እርምጃዎችን፣ ሕንጻ/ ቤቶች ላይ የተሳሉትን/ የተጻፉትን እና የተቀቡትን ማስወገጃ፣ ለደህንነት ካሜራዎች ወይም በስርቆት ለጠፉ እቃዎችን ግዢ የሚወጣ ወጪን አይሸፍንም

የብቃት መስፈርቶች

ለዚህ የገንዘብ ድጋፍ ብቁ ለመሆን የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለብዎት:

  • ከጥር 1 ቀን 2021 በኋላ በመደብራቸው የፊት ለፊት ገጽታ ላይ አካላዊ ጉዳት ደርሶ ከሆነ።
  • በኮቪድ-19 ምክንያት ቀጥተኛ የኢኮኖሚያዊ ችግር ያጋጠማቸው።
  • አሁን ላይ ተቀባይነት ያለው የሲያትል የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው።
  • የከተማ ንግድ እና ሥራ (B&O) ግብር ሙሉ በሙሉ የከፈሉ።
  • በሲያትል ከተማ ወሰኖች ውስጥ ያሉ።
  • በግል ባለቤትነት የተያዘ፣ በሌላ ንግድ ስም ፌቃድ ያልሆነ (non-franchise) እና የተቀጢላ (non-chain) ንግድ የሆነ።
  • ለትርፍ የተቋቋመ ንግድ የሆነ።
  • ከሁለት (2) የማይበልጡ ቦታዎች/ አድራሻ ያላቸው።
  • በአሁኑ ጊዜ ክፍት እና ለንግድ ስራ ንቁ የሆኑ።

ተጨማሪ መመዘኛዎች:

  • በአንድ ንግድ፣ የንግድ ድርጅት ባለቤት፣ EIN፣ SSN፣ UBI ቁጥር፣ የአንድ ንግድ ፈቃድ ቁጥር፣ የቤት እና/ወይም የንግድ አድራሻ ከሁለት በላይ ማመልከቻዎች መቅረብ አይችሉም። እያንዳንዱ ማመልከቻ ለተለያዩ ክስተቶች እና የተለያዩ ቀናት ያላቸው መሆን አለባቸው።
  • ንግድ ቢያንስ ለ 24 ወራት በሥራ ላይ የቆየ መሆን አለበት (እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2022)
  • ንግዱ በአንድ አጠቃላይ ህዝቡን የሚያገለግል አካላዊ መገኛ ቦታ እና/ወይም ተንቀሳቃሽ የጭነት መኪናዎች ላይ ሆኖ የሚሰራ መሆን ይኖርበታል።

የንግድ መጠንን የተመለከቱ መመዘኛዎች:

  • ንግድ ላለፉት 24 ወራት ከ50 በላይ የሙሉ ጊዜ ተመጣጣኝ (FTE) ሰራተኞች ሊኖሩት አይችልም።
  • ለሲያትል ከተማ የፋይናንስ እና አስተዳደራዊ አገልግሎቶች መምሪያ በ2020 እና 2021 በንግድ እና ሥራ (B&O) ግብሮች ላይ ሪፖርት በተደረገው መሰረት ንግዱ ከ$1,000 ዶላር በላይ እና ከ $7,000,000 ዶላር የማይበልጥ ዓመታዊ የተጣራ ገቢ ያለው መሆን አለበት።

ለመደብር የፊት ለፊት ገጽታ ጥገና የድጋፍ ገንዘብ (Storefront Repair Fund) ለማመልከት ብቁ ያልሆኑ ንግዶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:

  • ከ ኪንግ ካውንቲ ጋር ባልታካለለ አካባቢ ውስጥ የሚገኝ የንግድ ተቋማ።
  • በሲያትል ማዘጋጃ ቤት ህግ አንቀጽ 6.270 ስር የሚተዳደሩ "የአዋቂዎች መዝናኛ" ንግዶች። 
  • የሀሺሽ/ካናቢስ ሱቆች፣ አብቃዮች እና ማከፋፈያዎች ብቁ አይሆኑም። 
  • 501(c)(3), 501(c)(6) ወይም 501(c)(19) ለትርፍ ያልተቋቋሙ አካላት።

አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች

ማመልከቻዎትን ለማስገባት የሚከተሉት ሰነዶች ያስፈልግዎታል:

  • የተዋሃደ የንግድ መታወቂያ (UBI) ቁጥር (ዘጠኝ አሃዞች)
  • የከተማ ንግድ ፈቃድ ቁጥር (ስድስት አሃዞች)
  • የንግድ እና ሙያ (B&O) ግብሮች። የግብሮችዎን ቅጂዎች ማስገባት አያስፈልግዎትም።

ለገንዘብ ድጋፍ ከተመረጡ፣ እርስዎ የሚከተሉትን ማስገባት ይኖርብዎታል:

  • የንብረት ጉዳት ማረጋገጫ። ከሚከተሉት ሰነዶች ከሶስቱ ውስጥ ሁለቱን ማስገባት ይኖርብዎታል:
    • የተጠናቀቁ ጥገናዎች ደረሰኞች እና/ወይም አሁኑ ላለ ጉዳት ግምቶች።
    • የፖሊስ የክስተት ሪፖርት ቁጥር።
    • የመደብር የፊት ለፊት ገጽታ ላይ የደረሰ ጉዳት የሚያሳዩ ፎቶዎች።
  • ልዩ የሆነ አካል መታወቂያ (UEI) ቁጥር።
    • ከሚያዚያ 2022 ጀምሮ፣ በፌዴራል ከሚወጡ የገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራሞች የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት አንድ ልዩ የሆነ አካል መታወቂያ (UEI) ቁጥር ያስፈልጋል። ለዚህ ቁጥር እንዴት ማመልከት እንደሚቻል በተመለከተ የዋሽንግተን ስቴት የንግድ መምሪያ ይህንን የUEI በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች ዝርዝር አዘጋጅቷል።
  • የአሰሪ የመለያ ቁጥር (EIN) ወይም የማህበራዊ ዋስትና ቁጥር (SSN)
    • የሲያትል ከተማ እንግዳ ተቀባይ ከተማ ነች። ለ አቃፊነት እና እኩልነት ዋጋ እንሰጣለን። የከተማው ሰራተኞች ስለ ዜግነት ሁኔታ የተመለከቱ ጥያቄዎችን የማይጠይቁ እና የስደተኝነት ሁኔታቸው ምንም ይሁን ምን ነዋሪዎችን ሁሉ የሚያገለግሉ ናቸው፡፡
  • W-9 ቅጽ ያጠናቅቁ።

የማመልከቻ ሂደት

ከጥቅምት 18 ቀን 2022 ጀምሮ ማመልከቻዎን በመስመር ላይ/ኦንላይን ማስገባት አለቦት።

የእኛ ቢሮ ማመልከቻው እንደደረሰው አንድ ማመልከቻ ለገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ብቁ መሆኑን ለመወሰን ግምገማ ያካሂዳል።

ሰራተኞች አመልካቾችን በ 206 የአከባቢ ቁጥር/ ኮድ በሚጀምር ስልክ ወይም በ@seattle.gov ከሚያልቅ ኢሜይል በኩል ያገኟቸዋል። የንግድ ተቋማት የ አንድን ሰራተኛ ማንነት በ(206) 684-8090 ወደ ቢሮአችን በመደወል ወይም በድህረ-ገፃችን ላይ ያለውን የሰራተኞች የስም ማውጫ ገፃችንን በመጎብኘት ማረጋገጥ ይችላሉ።

ለመደብር የፊት ለፊት ገጽታ ጥገና የገንዘብ ድጋፍ እዚህ ላይ ያመልክቱ

የትርጉም ወይም የቃል ትርጉም ድጋፍ

ጥያቄዎችን ለመመለስ እና አመልካቾችን ማመልከቻዎቻቸውን እንዲያጠናቅቁ ለመርዳት የሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ሰራተኞች ቀጥሎ ባሉት ቋንቋዎች ይገኛሉ: አማርኛ፣ ቻይንኛ፣ ኮሪይኛ፣ ሶማሊኛ፣ ስፓኒሽ፣ የታይ ቋንቋ እና ቬትናምኛ። በተጨማሪ ቋንቋዎች የሚቀርብ ድጋፍ በእኛ የቋንቋ መስመር በ (206) 684-8090 ላይ ይገኛል።

እንዲሁም ይህን ሰነድ ከማመልከትዎ በፊት ከማመልከቻው ጥያቄዎች ጋር መከለስ ይችላሉ: የመደብር የፊት ለፊት ጥገና የገንዘብ ድጋፍ ማመልከቻ ጥያቄዎች

ለብዙ አጋጣሚዎች ማመልከት ይችላሉ?

ቢሮአችን የገንዘብ ድጋፍ መዋጮ ውጪ ሆኖ እስከሚያልቅ ድረስ ብዙ ሆን ተብሎ የመደብር ፊት ለፊት ገጽታ የማበላሸት ጉዳት ያጋጠማቸውን የንግድ ተቋማት እስከ ሁለት ጊዜ ድረስ እንዲያመለክቱ ይፈቅዳል። ለሁለተኛ ድጎማ ብቁ ለመሆን አጋጣሚዎቹ በተለያዩ ቀናት ውስጥ የተከሰቱ መሆን አለባቸው።

ለዚህ የገንዘብ ድጋፍ ስጦታ የፖሊስ ሪፖርት ማቅረብ ያስፈልጋል?

የፖሊስ ሪፖርት ማቅረብ አስፈላጊ አይደለም። የንብረት ጉዳት ማረጋገጫን ለማሳየት ከሚከተሉት ሰነዶች ከሶስቱ ውስጥ ሁለቱን ማስገባት ይኖርብዎታል: ደረሰኞች፣ የፖሊስ የክስተት ሪፖርት ቁጥር ወይም ፎቶዎች።

የንግድ ተቋማት 911 ላይ በመደወል ወይም በመስመር ላይ ወንጀል ሪፖርት ማድረጊያ ድህረ-ገጽ በኩል የፖሊስ ሪፖርት ማስመዝገብ ይችላሉ።

እርዳታ ይፈልጋሉ ወይም ጥያቄዎች አሉዎት?

እባክዎን ለእርዳታ (206) 684-8090 ይደውሉ እና በድምጽ መልእክትዎ ውስጥ የሚከተሉትን መረጃዎች ያስተውሉ: ስም፣ የስልክ ቁጥር፣ ተመራጭ ቋንቋ፣ እና የተፈለገው የድጋፍ አይነት።

በቀጣይነት የሚኖሩ ፕሮግራሞች ወይም እርዳታ

ሌሎች ፕሮግራሞችን የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎች ከኢኮኖሚያዊ ልማት ጽህፈት ቤት (OED) ለማግኘት፣ እባክዎን ለጋዜጣችን አባልነት ይመዝገቡ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይከተሉን: @SeattleEconomy ብለው በ ትዊተር፣ በ እንስታግራም፣ እንደዚሁም በ ፌስቡክ ላይ።

የሲያትል የኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት (OED) ለሁሉም የሲያትል የተለያዩ ብዝሃነትን የተላበሱ ማህበረሰቦች የኢኮኖሚያዊ ዕድሎች ተደራሽነትን በማስፋፋት መላውን ከተማ የሚጠቅም ፍትሃዊ እኩልነትን እና አካታች ኢኮኖሚን ለመገንባት ቁርጠኛ ነው።

የሲያትል ከተማ ሁሉ ሰው በፕሮግራሞቹ እና በዝግጅቶቹ እንዲሳተፍ ያበረታታል። ለተጨማሪ ጥያቄዎች፣ ለትርጉም ወይም ለቃል ትርጉም፣ ለቴክኒካዊ ዕርዳታ፣ ለአካል ጉዳተኝነት መስተናገጃዎች፣ ለተለዋጭ የመረጃ/ ማስረጃ ይዞታዎች ላላቸው ወይም የተደራሽነት መረጃን ለማግኘት፣ እባክዎ የሲያትል የኢኮኖሚ ልማት ጽሕፈት ቤት (OED)ን በ (206) 684-8090 ወይም oed@seattle.gov ላይ ያግኙ

Economic Development

Markham McIntyre, Director
Address: 700 5th Ave, Suite 5752, Seattle, WA, 98104
Mailing Address: PO Box 94708, Seattle, WA, 98124-4708
Phone: (206) 684-8090
Phone Alt: (206) 684-0379
Fax: (206) 684-0379
oed@seattle.gov

Newsletter Updates

Subscribe

Sign up for the latest updates from Economic Development

The mission of the Office of Economic Development (OED) is to help create healthy businesses, thriving neighborhoods, and community organizations to contribute to a robust economy that will benefit all Seattle residents and future generations.