SBA Disaster Loan Technical Assistance

Update 4/29

The U.S. Small Business Administration will open the application portal for the $28.6 billion Restaurant Revitalization Fund (RRF) on Monday, May 3, 2021, at 9 a.m. PDT. Eligible applicants should register for an account in advance at restaurants.sba.gov starting this Friday, April 30, 2021, at 6 a.m. PDT. Once businesses register for an account  they will  be able to complete their application by uploading the required documents to the application portal on May 3. Eligible businesses are eligible for up to $5 million in funding  per location, not to exceed $10 million total for the applicant and affiliated businesses.

The Shuttered Venue Operators Grant (SVOG) is now open. The American Rescue Plan Act allocated an additional $1.25 billion to SVOG — bringing the program funding to a total of $16.25 billion. Additional changes include applicants can apply for the second round of PPP and SVOG. The SVOG grant will be reduced by the PPP loan amount. PPP applications have been updated to reflect this. 

Ready for Business Banner

Has your business experienced financial loss and hardship due to the COVID-19 pandemic? If so, the Ready for Business Fund is here to help your business bounce back.  

GSBA and Comcast Washington opened Ready for Business Fund – Round 2 to support small businesses impacted by COVID-19. The $2,500 cash grant will be awarded to selected small businesses. The application is open to any small business in Washington State established prior to March 2, 2020.

Priority will be given to small businesses within the communities most impacted by COVID-19, including LGBTQ-, BIPOC-, and women-owned businesses, as well as businesses located in rural areas.

Additionally, awardees will receive wrap-around support services including GSBA membership, technical support, marketing and consulting. This grant does not have to be repaid, and it can be used for any purpose to help the business recover from the economic crisis.

Applications close on April 9 at 4:00 p.m. PDT.

Apply for the Ready for Business Fund

የአነስተኛ ንግድ አስተዳደር (SBA) ብድር ማመልከቻ ለመሙላት እርዳታ ይፈልጋሉ?

ቅድምያ ክፍያ ከፈጸሙ የSBA  ብድርን እንደምያጸድቅልዎ ቃል በመግባት  ወይንም ለጥቃቅን ንግድ ብድር በከፍተኛ ወለድ የሚሰጥ የተገናኛችሁ ሰው ካለ ማጭበርበር  ሊሆን እንደምችል ይጠራጠሩ። ለSBA  ብድሮች ለማመልከት ምንም ክፍያ ያለም።

የኢኮኖሚ ልማት ቢሮ (OED) ለንግድ ድርጅቶች ለሚከተሉት ነጻ የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፡

  • ያሉትን የገንዘብ ድጋፍ ምንጮችን የተ ሻለ እንድትረዱ
  • መስፈርት ማሟላታችሁን ለማረጋግጥ
  • ለ SBA ብድሮች ለማመልከትና ማመልከቻውን ለመሙላት  

እባክዎን የሲያትል ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በ(206) 684-8090 ይደዉሉ። ለትርጉም አገልግሎት ጠይቆ በስልክ የቋንቋ እርደታ ማግኘት ይችላሉ።

ሲደውሉ እባክዎን ይንገሩን፡

  • ስሞን
  • ስልክ ቁጥር
  • የሚፈልጉትን ቋንቋ
  • ምን እርዳታ እንደሚፈልጉ  

የቋንቋ ድጋፍ ከፈለጉ ወይ ሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ሠራተኛ መልሶ ይደዉልሎታል ወይንም ለመነጋገር እንዲረዳዎት ሶስተኛ ወገን አስተርጓሚ በስልክ እንዲረዳዎት እንጠራሎታለን።

እባክዎን ብዙ ሰዎች ድጋፍ ለማግኘት ይደውሉልናል፤ ስለሆነም ብዙ ሊጠብቁ እንደሚችሉ ያስቡ። ከአስተርጓሚ ጋርም ለመገናኘት ሊጠብቁ ይችላሉ።

በCOVID-19 ወረርሽኝ ምክንያት የደረሰቦትን የኢኮኖሚ መስተጓጎል ለመወጣት እንዲረዳዎ ከSBA አራት የገንዘብ ድጋፍ አማራጮች እነዚህ ናቸዉ፡  

SBA የኢኮኖሚ ጉዳት አደጋ ብድሮችና (EIDL)

በCOVID-19 ጉዳት የደረሰባቸዉ ንግድ ድርጅቶችና ለትርፍ የማይሰሩ ድርጅቶች አነስተኛ ወለድ ያለቸዉ የሥራ ማስኬጃ ብድሮችን በፌደራል የአነስተኛ ንግድ አስተዳደር  (SBA) የኢኮኖሚ ጉዳት አደጋ ብድሮች  (EIDL) ፕሮግራም በኩል ለማግኘት ለማመልከት ብቁ ናቸው። እነዚህ ብድሮች አነስተኛ ንግድ ድርጅቶችን ያለባቸውን ዕዳና ሥራ ማስኬጃ ወጪዎችን ለመሸፈን ሊረዱ ይችላሉ። ወለዱ ለአነስተኛ ንግድ ድርጅቶች  3.75% ና ለትርፍ የማይሰሩ ድርጅቶች  2.75% ነው።

EIDL ለማመልከት የጊዜ ገደቡ እሱ መስከረም  30, 2020 ነዉ። 

ከማመልከትዎ በፊት የሚከተሉትን መረጃ ያዘጋጁ፡

  • የቀጣሪ መለያ ቁጥር (EIN)
  • የማህበራዊ ዋስትና ቁጥር (SSN)
  • ፌብሯሪ 1 2019 - ጃንዋሪ 31 2020 ጠቅላላ ገቢ
  • ፌብሯሪ 1 2019 - ጃንዋሪ 31 2020 የተሸጡ ዕቃዎች ወጪ
  • የሠራተኞች ቁጥር
  • የባንክ አካዉንትና ራዉትኝ ቁጥሮች      

SBA የደመወዝ መከላከያ ፕሮግራም (PPP) ብድሮች  

PPP IconየSBA የደመወዝ መከላከያ ፕሮግራም (PPP) በCOVID-19 ችግር ወቅት ሠራተኞቻቸውን መክፈል መቀጠል እንዲችሉ ይቅር ሊባሉ የሚችሉ ብድሮችን ለአነስተኛ ንግድ ድርጅቶች ያቀርባል። ንግድ ድርጅቶች በአካባቢ ባንኮቻቸዉ በኩል ያመለክታሉ፤ የብድር መስፈርቱ ለሁሉም ተመሳሳይ ነው። አነስተኛ ንግድ ድርጅቶች፣ ለትርፍ የማይሰሩ ድርጅቶችና፣  ለራሳቸው የሚሰሩ ግለሰቦች ወይንም ገለልተኛ ኮንተራክተሮች 500 ወይንም ያነሰ ሠራተኞች ካላቸዉ ለማመልከት ብቁ ናቸው። ብድሮቹ ይቅር የሚባሉ ናቸው የሚከተሉት እስከሆኑ ድረስ፡ 

  • ብድሮቹ ከፌብሯሪ 16 እስከ ጁን 30 2020 ባሉት የስምንት ሳምንታት ግዜ የደመወዝ ወጪዎች፣ ለአብዛኛዉ የሞርጌጅ ወለድ፣ ኪራይና፣  የግልጋሎት ወጪዎችን ለመሸፈን ጥቅም ላይ ከዋሉ።
  • የሠራተኞና ክፍያ ደረጃዎች ከፌብሯሪ 16 በፊት የነበሩበት ደረጃዎችን የጠበቀ ከሆነ። 

ወርሃዊ የሠራተኞች ደመዋዝ ለማስላት የሚከተሉትን እርምጃዎች ይዉሰዱ፡

1. ከCOVID-19 በፊት የነበረዉን ዓመታዊ የሠራተኞች ደመዋዝ ያስሉ። የደመዋዝ ወጪዎች ለሁሉም ጊዜያዊና ቋሚ ሠራተኞች የሚከተሉትን ወጪዎች ይጨምራል፡

  • የወር ደመዋዝ፣ የሰዓት ክፍያ፣ ኮሚሺን፣ ጉርሻ ወይንም ተመሳሳይ ማካካሻ (ለያንዳንዱ ሠራተኛ በዓመት ጣሪያዉ $100,000 ድረስ)፣
  • የእረፍት ክፍያ፣ የወሊድ፣ የቤተሰብ፣ የህክምና ወይንም የህመም እረፍት፣
  • ለመለያያ ወይንም የመባረር ክፍያ ፣
  • የቡድን ህክምና ጥቅማ ጥቅሞች ለማቅረብ የሚያስፈልጉ ክፍያዎች ኢንሹራንስን ጨምሮ፣
  • ለጡረታ ጥቅማ ጥቅሞች ክፍያ፣
  • ከማካካሻ ላይ የሚታሰብ ሠራተኛ የሚከፍለዉ የስቴትና አካባቢ ቀረጦች ክፍያ፡
  • ያንድ ግለሰብ ድርጅትና ገለልተኛ ኮንትራክተር ደመዋዞች፣ ኮሚሺኖች፣ ገቢ፣ ወይንም የራስ ቀጣሪዎች የተጣራ ገቢ በሠራተኛ ቁጥር በዓመት ጣሪያዉ $100,000 ድረስ።  

2. እነዚህን ወጪዎች የዓመቱን ጠቅላላ ደመዋዝ ለማስላት ይደምሩ።

3. አማካይ ወርሃዊ ደመዋዝ ለማግኘት በ12 ያካፍሉ።

ይህን ቁጥር ከአገር ዉስጥ ገቢ አገልግሎት (IRS)  941 የሠራተኞች የሩብ ዓመት የፌደራል ቀረጥ ተመላሽ ቅጽ መስመር 5E ላይም ማግኘት ይችላሉ። ከወቅታዊው ችግር በፊት ካሉት አራት ሩብ ዓመቶች መስመር 5E ጠቅላላ ይደምሩና አማካይ ወርሃዊ ደመዋዝ ለማግኘት በ12 ያካፍሉ።

ኣመልካቾች የሚከተሉትን ሰነዶችም ማቅረብ አለባቸዉ፡

  • ከጃንዋሪ 31 2020 ወዲህ የSBA EIDL ካለዎት, የብድርዎን ቀሪ ይያዙ
  • 2018 ወይንም 2019 ዓመታዊ ቀረጥ ተመላሽ
  • 2018 or 2019 የሩብ ዓመት ቀረጥ ተመላሾች
  • በድርጅቱ ማቋቋሚያ ሰርተፊኬት ላይ የድርጅቱ ባለቤትነት ማረጋገጫ
  • የሠራተኞች ደመዋዝ ሰነድ
  • የድርጅት ማቋቋሚያ አንቀጾች
  • የአፈጻጸም ስምምነት (ለኃላፊነቱ የተወሰነ ድርጅቶች (LLCs)፤ ከሌላ አስፈላጊ አይደለም)
  • መተዳደሪያ ደንብ (ለኮርፖሬሽኖች፤ ከሌላ አስፈላጊ አይደለም)
  • የሰሜን አሜሪካ ኢንዱስትሪ ምደባ ዘዴ (NAICS) ደንብ (https://www.census.gov/eos/www/naics/

የSBA የፈጣን ድልድይ ብድሮች 

Express Bridge Loan Iconፈጣን ድልድይ ብድር የሙከራ ፕሮግራም   ከSBA ፈጣን አበዳሪ ጋር የሥራ ግንኙነት ላላቸው አነስተኛ ንግድ ድርጅቶች በፍጥነት እስከ $25,000 ማግኘት እንድችሉ ይፈቅድላቸዋል። እነዚህ ብድሮች ለቀጥታ የSBA የኢኮኖሚ ጉዳት አደጋ ብድሮች  (EIDL) እያመለከቱ ባሉበት ግዜ ያለውን ክፍተት ሊሞለ ይችላል።  የአነስተኛ ንግድ ድርጅት ውሳኔ ወይንም የኢኮኖሚ ጉዳት አደጋ ብድር ክፍያ እየተጠባበቀ እያለ በአስቸኳይ ገንዘብ ከፈለገ ለSBA ፈጣን ድልድይ ብድር ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።

የነበሩ የSBA ብድሮችን ማስተላለፍ 

Debt Relief IconበSBA በኩል የነበረ የድርጅት ብድር ካለዎት፣ የSBA ዕዳ እፎይታ ፕሮግራም በCOVID-19 ምክንያት የተፈጠረባቸውን ተግዳሮቶች እያተወጡ ባሉበት ወቅት ለአነስተኛ ንግድ ድርጅቶች ብድሩን ያስተላልፋል።   ከSBA ጋር የነበረ ብድር ካለዎት በSBA ዕዳ እፎይታ ፕሮግራም በኩል SBA የነዚህን ብድሮች ዋናውንና ወለዱን ሊከፍል ይችላል።    

Economic Development

Markham McIntyre, Director
Address: 700 5th Ave, Suite 5752, Seattle, WA, 98104
Mailing Address: PO Box 94708, Seattle, WA, 98124-4708
Phone: (206) 684-8090
Phone Alt: (206) 684-0379
Fax: (206) 684-0379
oed@seattle.gov

Newsletter Updates

Subscribe

Sign up for the latest updates from Economic Development

The mission of the Office of Economic Development (OED) is to help create healthy businesses, thriving neighborhoods, and community organizations to contribute to a robust economy that will benefit all Seattle residents and future generations.