English
አማርኛ
繁體中文
한국어
Soomaali
Español
Tiếng Việt

Photo credit: Wikimedia Commons

የመሃል ከተማ መንገድ መልሶ ግንባታ እቅድ

ከንቲባ Jenny A. Durkan እና የመሃል ከተማው የ Seattle ማህበረሰብ አመራሮች በቅርቡ Road to Downtown Recovery plan (የመሃል ከተማ መንገድ መልሶ ግንባታ እቅድ) ን አሳውቀዋል፤ ይህም ሰራተኞችን፣ አነስተኛ ንግዶችን፣ እና ጎብኝዎችን ወደነበሩበት ከተማ ለመመለስ የሚደረጉ አዳዲስ ጥረቶችን እና መዋእለ ንዋዮችን ያካትታል። ከተማዋ Seattle Rescue Plan (የ Seattle የማዳን እቅድ) መዋእለ ንዋዮች እና ሌሎች የፌዴራል ድጎማዎችን በመጠቀም፣ ከ 9 ሚሊዮን ዶላር በላይ በከተማው መልሶ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ መዋእለ ንዋይ ያፈሳል፤ ይህም ባዶ የመጋዘን መግቢያዎችን ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት፣ ለመሃል ከተማ አነስተኛ ንግዶች ቀጥተኛ የገንዘብ ድጋፍን፣ እና ስራ ለሌላቸው ወይም ከሥራ ቅጥር በታች ለሆኑ የከተማው መስተንግዶ ሠራተኞች የሠራተኛ ልማት ፕሮግራሞች ይጨምራል። ለዚህ የመልሶ ግንባታ ጥረት ሲባል፣ የከተማው የመሀል ከተማ ትርጉም ከ Seattle Center (የ Seattle ማዕከል) እስከ Stadium District (ስቴዲየም ዲስትሪክት) እና ከ I-5 እስከ Waterfront (ዋተርፍሮንት) ድረስ ይዘልቃል።

የመሃል ከተማ ጎብኝዎችን ለማሳደግ የ Seattle ከተማ እና የመሃል ከተማ አጋሮች በጁላይ እና ሴፕቴምበር "Welcome Back Weeks" ያዘጋጃሉ።

ከተማው ኩነቶችን እና ፕሮግራሞችን ለማሳደግ ከሚያደርገው ጥረት አንዱ፣ ከተማው እና DSA ከጁላይ 12 - 25 እና ከሴፕቴምበር 4 - 19"Welcome Back Weeks (የእንኳን ደህና ተመለሳችሁ ሳምንታት)" ን ለማስተናገድ በአጋርነት እየሰሩ ነው። Welcome Back Weeks ከትላልቅ ኮንሰርቶች እና ከችርቻሮ ማስተዋወቂያዎች እስከ ትናንሽ የመሃል ከተማ ምግብ ቤቶች እና ቡና ቤቶች ድጋፍን የሚያበረታቱ ልዩ ልዩ ኩነቶችን ያጠቃልላል።

welcome back to pioneer square

እንኳን በደህና መጡ ወደ፡ Pioneer Square!

በኦሲደንታል አደባባይ (Occidental Square) ላይ አንድ ኮንሰርት፣ ተለይቶ የቀረበ

  • የቀጥታ ሙዚቃ ከ Shaina Shepherd፣ Shenandoah Davis፣ እና Black Tones 
  • 'ፋውንድ ፋሽን' ዐውደ-ርዕይ ከፓዝ ዊዝ አርት (Path with Art) 
  • ከፓርቲ ሃት (Party Hat Gallery) ጋለሪ ነፃ የስክሪን ዕትመት
  • የቢራ ጋርደን (እንዲወሰን)
  • ጆንሰን እና ጆንሰን እና ፒፋይዘርን የክትባት መደብ ይቀርባል  

መቼ: - ቅዳሜ ሐምሌ 24፣ ቀን 10፡30 a.m. - 3 p.m.

የት፣ ኦሲደንታል አደባባይ (Occidental Square), 117 S Washington St, Seattle, WA 98104

 

welcome back to westlake እንኳን በደህና መጡ ወደ፡ Westlake!

በዌስትሌክ ፓርክ (Westlake Park) እና በፓስፊክ ፕሌስ (Pacific Place) ለቤተሰብ ተስማሚ የሆነ በዓል:

  • የ 'ሃሎዊን በሐምሌ ወር' ዝግጅት በዌስትሌክ ፓርክ እና በፓስፊክ ፕሌስ ውስጥ ያሉ ልጆች እና ቤተሰቦች  በአከባቢው ባሉ ሻጮች እና መደብሮች እየተዘዋወሩ ባህላዊ ልብስ በመልበስ trick-or-treat እያሉ የሚያቀርቡት
  • የእግረኛ መንገድ ሽያጮች እና የምግብ መኪናዎች ከአከባቢው አነስተኛ ንግድ ባለቤቶች ጋር መደብሮቻቸውን ይዘው ወደ ህዝባዊ ቦታ በመምጣት እዉጭ ሽያጭ ያካሄዳሉ 
  • ነፃ የፊት ቅብ፣ የልብስ ውድድር፣ THRILLER የዳንስ ክፍሎች፣ ወርክሾፖች እና ለቤተሰቡ በሙሉ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች
  • ቀኑን ሙሉ የቀጥታ ትርዒቶች El Vez፣ Teatro Zinzanni፣ SANCA's Cirrus Circus Lelavision፣  Up Up Circus እና ሌሎችንም ያካተቱ
  • ጆንሰን እና ጆንሰን እና ፒፋይዘርን የክትባት መደብ ይቀርባል

መቼ: እሑድ ሐምሌ 25፣ 12 - 8 p.m. (ጊዜያዊ)

የት: Westlake Center, 400 Pine St, Seattle, WA 98101

በ Welcome Back Weeks ወቅት ፕሮግራምን ማቅረብ የሚፈልጉ ንግዶች ወይም ድርጅቶች ተግባራታቸውን ለ DSA ለማስተዋወቅ ይህንን ቅጽ ማጠናቀቅ አለባቸው።ከተማው ተጨማሪ የክረምት ፕሮግራሞችን ለመደገፍ በከተማው ሁሉም የመሀል ከተማ ሰፈር የንግድ ዲስትሪክቶች ላይ መዋእለ ንዋይ እያፈሰሰ ነው።ከተማው ከጁላይ ወር ጀምሮ፣ City Hall፣ Central Library፣ እና የመኖሪያ ጥበቦች ድርጅቶችን ጨምሮ የ Seattle Center ካምፓስ እንዲሁም በኦክቶበር የ Climate Pledge Arena ን ጨምሮ የመሃል ከተማ ተቋማትን ቀስ በቀስ ይከፍታል።

የ Seattle Rescue Plan መዋእለ ንዋዮችን በመጠቀም፣ የ Seattle ከተማ ከ 9 ሚሊዮን ዶላር በላይ የመሃል ከተማ መልሶ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ መዋእለ ንዋይ ሊያፈስ ነው።

በተጨማሪም፣ ለመሃል ከተማ ሰራተኞች፣ ጎብኝዎች እና ነዋሪዎች ደህንነቱ የተጠበቀ፣ እንግዳ ተቀባይ የሆነ ተሞክሮን ለማረጋገጥ፣ በ DSA የሚተዳደረው፣ Metropolitan Improvement District (የሜትሮፖሊታን ማሻሻያ ዲስትሪክት) ለተጨማሪ መሳሪያዎች፣ ጽዳት፣ ኩነቶች እና የቀጥታ ስርጭት ሙዚቃ እና ሌሎች መገልገያዎችን ጨምሮ $3.2 ሚሊዮን መዋእለ ንዋይ እያፈሰሰ ነው።

የከተማዋ መልሶ ግንባታ ጥረት አካል በመሆን፣ ከተማው ለመሀል ከተማው አነስተኛ የንግድ ተቋማት እና ለኪነ-ጥበባት እንዲሁም ለባህላዊ ድርጅቶች ቀጥተኛ የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል፤ እንዲሁም ጊዜያዊ የኪነ-ጥበባት ጭነቶች፣ ሥራ ወይም pop-up የችርቻሮ ቦታዎች ያላቸውን ባዶ መደብሮች ለማንቃት በፕሮግራሙ ላይ መዋእለ ንዋይ ያፈሳሉ።የከተማው የንግድ ተቋማትን ለመደገፍ ጎዳናዎችን እና የእግረኛ መንገዶችን ለማንቃት የበለጠ ነፃ ፈቃዶችን ለማቅረብ ከተማው ወደ  Seattle Department of Transportation (SDOT፣ የሲያትል የትራንስፖርት መምሪያ) ፣ በሴፕቴምበር መጨረሻ ነጻ ፈቃዶችን ወደ 120 በእጥፍ ከማሳደግ አላማ ጋር፣ ሀብቶችን እየጨመረ ነው።

የሰራተኞችን እና አነስተኛ ንግዶችን መመለስ ለማመቻቸት በመኸር ወቅት ከተማው በዝቅተኛ ሁኔታ ለሚሰሩ የከተማው መስተንግዶ ሰራተኞች አዲስ የሥራ ኃይል ልማት እና የሥራ ምደባ ድጋፎችን ይጀምራል፤ እንዲሁም ከክልል አጋሮች ጋር በመሆን በቴክኖሎጂው ዘርፍ የዘር እኩልነትን ለማስፋፋት የቴክኖሎጂ አስተባባሪ በመሆን ህብረተሰቡን መሠረት ያደረጉ መፍትሄዎችን ያዘጋጃል።ሠራተኞቹን ወደ መሃል ከተማ ተመልሰው የትራንዚት አጠቃቀምን ለማበረታታት፣ SDOT] በቅርቡ 2,000 ነፃ ORCA ካርዶችን ለቻይናታውን ዓለም አቀፍ ዲስትሪክት እና ለፓዮኒር አደባባይ ሬስቶራንት እና ግሮሰሪ ለማቅረብ ፕሮግራም ጀምሯል። የመሀል ከተማ ሰራተኞች እና ትናንሽ ንግዶችን ጤና እና ደህንነት የሚታዩ መሐላዎችን እና የማህበረሰብ አገልግሎት መኮንኖች ን በመጨመር - በ Seattle Police Department (የሲያትል ፖሊስ መምሪያ)አሁን ባለው የሰራተኛ እጥረት ውስጥ እስከሚቻለው መጠን ድረስ-  የወንጀል መበራከት ባሉባቸው አካባቢዎች እንደ Health One መስፋፋትን ከመሰሉ ጥረቶች ጎን ለጎን፣ በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ የሆኑ ግለሰቦችን ያለ መሐላ የገባ መኮንን ምላሽ በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል ከተማው ቅድሚያ ይሰጣል።

ከተማው እና ካውንቲው በ Seattle ከተማ ውስጥ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ያለመኖሪያ ቤት የሚኖሩ ተጋላጭ ሰዎችን ችግር ለመፍታት አዳዲስ ሀብቶችን ተግባራዊ እያደረጉ ነው።Seattle Rescue Plan 450 ግለሰቦችን ወደ ደህና ቦታዎች ለማንቀሳቀስ እና 300 አዳዲስ ቤቶችን ለመስራት ማገዝን ጨምሮ የቤት እጦት ያጋጠማቸውን 750 ግለሰቦችን ይረዳል።በቤት-አልባነት ላይ የ King County አዲስ መዋእለ ንዋዮች ተጨማሪ 500 ግለሰቦችን ወደ መሃል ከተማ እና ያልተዋሃደ የ King County ን ወደ ደህንነታቸው የተጠበቁ ቦታዎች ያዛውራሉ።

እንደ ከተማ የማስዋብ ጥረቱ አካል፣ የታቀዱ ኩነቶች ያሉባቸው አካባቢዎች ቅድሚያ እንደተሰጣቸው ለማረጋገጥ ከተማው ከመሀል ከተማ አካላት እና ከከተማው መምሪያዎች ጋር በመሆን የቆሻሻ መጣያ ጽዳቶችን ያስተባብራል።እነዚህ ጥረቶች የ Clean City program (የከተማ እናጽዳ ፕሮግራም) እና የመንገዳ ዳር ስእሎች ማቃለያን እንዲሁም የእጽዋት ሳጥኖችን የማደስ እና የግድግዳ ስዕሎችን፣ የጥበብ ግንባታዎችን እና የመብራት መትከልን ለመጨመር አዳዲስ ጥረቶችን የመቀጠል ጥረቶችን ያካትታሉ።የ Washington ግዛት Department of Transportation (የትራንስፖርት መምሪያ) የመሃል ከተማውን I-5 ኮሪደር በቆሻሻ መጣያ ማስወገጃ እና የመንገድ ዳር ስእሎችን በማቃለል ችግሮችን ይፈታል።