የሲያትል የማመላለሻ እቅድ

አማርኛاَلْعَرَبِيَّةُ • 繁体字 • 简化字 • 日本語 • ភាសាខ្មែរ • 한국어 • ລາວ • Oromiffa • русский язык • af-Soomaali • Español • Tagalog • ภาษาไทย • ትግርኛ • Tiếng việt •  украї́нська мо́ва •  English

በሲያትል የመጓጓዣ የወደፊት ራዕይ

የሲያትል የማመላለሻ እቅድ (STP) ምንድን ነው እሱ?

የሲያትል የማመላለሻ እቅድ (STP) ሁሉንም ሰው ቦታዎችን እና እድሎችን በአስተማማኝነት መድረስ፣ ቀልጣፋ እና በዋጋ ተመጣጣኝ አማራጮችን የሚያቀርብ የማመላለሻ ስርዓት ለመገንባት ያለን ቁርጠኝነት ነው።

የማመላለሻ ስርዓታችን ከመንገድ እና ከእግረኛ መንገድ በላይ ነው። አውቶቡሶችን፣ ቀላል ባቡርን፣ የእግረኛ መንገዶችን፣ የሕዝብ ቦታዎችን እና ከዚህም በላይ ብዙ ሌሎችንም ያካትታል። ነገር ግን ኮቪድ-19፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ እና ፈጣን የህዝብ ቁጥር መጨመር ይህ ስርአት ያለችግር እንዲሄድ አስቸጋሪ ያደርጉታል። ለዚህም ነው አሁን እና ወደፊት የሚሰራ ዘላቂ ስርዓት መፍጠር የምንፈልገው።

የሲያትል የማመላለሻ እቅድ (STP) ለኔ እና ለማህበረሰቦቼ ጉዳይችን የሚሆነው ለምንድነው?

የትም ብትሄድ - ሥራም ሆነ ትምህርት ቤት፣ ጓደኞችን መጎብኘት፣ ገበያ መሄድ፣ ወደ አምልኮ ቦታዎ መሄድ ወይም እራት ለመብላት – ደህንነቱ በተጠበቀ፣ ውጤታማ እና በዋጋ ተመጣጣኝ በሆነ መንገድ ማድረግ መቻል ይኖርብዎታል። በቀላል አነጋገር፣ የማመላለሻ ፍላጎታችን የዕለት ተዕለት ህይወታችንን በብዙ መልኩ ይቀርፃል። በሲያትል የማመላለሻ እቅድ (STP) አሠራር ውስጥ በመሳተፍ፣ ለሁሉም ሰው በተሻለ ሁኔታ የሚሰራ ስርዓት እንድንገነባ ይረዱናል።

የሲያትል የማመላለሻ ሥርዓት ሁሉንም ሊጠቅም ይገባል። በጣም ብዙ ጊዜ፣ የመንግስት እቅዶች ሲዘጋጁ፣ ብዙ ሰዎችን ያገላሉ - በተለይም ጥቁሮችን፣ ተወላጆችን፣ ወይም የቀለም ማህበረሰብ አካል ክፍል የሆኑትን፤ (ሴት ከሴት፣ ግብረ-ሰዶማዊ፣ ሁለትዮሻዊ ጾታ፣ ጾታ ለዋጭ፣ ጾታው የተለየ፣ መታወቂያው መስቀለኛ የሆነ፣ መሃል-ገብ +) LGBTQIA+ የሆኑ ሰዎች፤ በድህነት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች፤ ስደተኛ ማህበረሰቦች እና በቤት ውስጥ እንግሊዝኛ የማይናገሩ ሰዎች፤ ወጣቶች፤ አረጋውያን፤ እና አካል ጉዳተኞች ሰዎች። ፍላጎታቸው እንዲሟላላቸው የሁሉም ሰው ድምጽ መሰማት አለበት ብለን እናምናለን።

አንድ ላይ፣ እስኪ ጥያቄውን እንመልስ: የማመላለሻ ስርዓታችን ምን እንዲመስል እና እንዴት እንዲሰማ ይፈልጋሉ?

በሲያትል ውስጥ ለወደፊት የማመላለሻ ራዕይ

የሲያትል የማመላለሻ እቅድ (STP)ን በመፍጠር ይማሩ እና ይቀላቀሉ! ከተሳትፎ እድሎች ጋር ለማገናኘት፣ የሥራ እቅድ ግብአቶችን ለማግኘት እና በእቅድ ሂደቱ ላይ እንደተዘመኑ ለመቆየት ይህንን ጣቢያ ይጠቀሙ።

አሁን ምን እየሆነ ነው ያለው?

የእቅድ ሂደታችን ገና አሁን እየተጀመረ ነው፣ እና የእርስዎን እገዛ እንፈልጋለን!

ለመጀመር እንዲረዳን፣ እቅዱን አብረን በምናቀናጅበት ጊዜ በሲያትል ዙሪያ እንዴት እንደሚመላለሱ ይንገሩን እና ከእርስዎ ጋር የምንገናኝበትን ምርጡን መንገድ ያሳውቁን።

ስለ ሲያትል የማመላለሻ እቅድ የበለጠ ይወቁ

ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች

ስለ የሲያትል የማመላለሻ እቅድ (STP) የበለጠ ሊነግሩኝ ይችላሉ?

የሲያትል የማመላለሻ እቅድ (STP) በሲያትል ውስጥ ለወደፊቱ የመጓጓዣ ራዕይ ነው። የህብረተሰቡ ተሳትፎ ለዕቅዱ ልማት ወሳኝ አካል ነው። የሲያትል የማመላለሻ እቅድ (STP) ለከተማችን አሁን እና ለወደፊት የሚሰራ የማመላለሻ ስርዓት ግቦችን፣ ስልቶችን እና ምክሮችን ያስቀምጣል። ዕቅዱ ከወደፊት የማመላለሻ ገንዘብ እስከ በሕዝብ ቦታ የምንደሰትበትን እና በከተማ ውስጥ የምንዘዋወርበትን መንገድ የሚያሻሽሉ ፕሮጀክቶች እና ፕሮግራሞች ድረስ ሁሉንም ነገር መልክ ያስይዛል።

ፍላጎቶችዎን የሚያሟላ የማመላለሻ ስርዓት ለመፍጠር ከእርስዎ እና ከጎረቤቶችዎ ጋር ለመስራት በጉጉት እንጠብቃለን።

ብዙ ጊዜ፣ የመንግስት እቅዶች ሲዘጋጁ ሰዎችን በተለይም ጥቁር፣ ተወላጅ ወይም የቀለም ማህበረሰብ አባላት የሆኑትን፤ LGBTQIA+ የሆኑ ሰዎች፤ በድህነት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች፤ ስደተኛ ማህበረሰቦች እና በቤት ውስጥ እንግሊዝኛ የማይናገሩ ሰዎችን፤ ወጣቶችን፤ አረጋውያን አዋቂዎችን፤ እና አካል ጉዳተኞችን ያገለላሉ። ፍላጎታቸው እንዲሟላ የሁሉም ሰው ድምጽ መሰማት አለበት ብለን እናምናለን። እቅዱ የሁሉንም ሰው እሴቶች እና ፍላጎቶች የሚያንፀባርቅ መሆኑን ለማረጋገጥ ከሚያገለግሏቸው ማህበረሰቦች ጋር ነባር ግንኙነት ካላቸው ማህበረሰብን መሠረት ካደረጉ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ላይ ነን።

ዋናው ነገር? የሲያትል የማመላለሻ እቅድ (STP) የማመላለሻ ስርዓትን ለመገንባት ያለን ቁርጠኝነት ነው:

  • የሁሉንም ሰው ፍላጎት ያሟላል፣
  • ሁላችንም በአስተማማኝ፣ በብቃት እና በተመጣጣኝ ዋጋ ከቦታዎች እና እድሎች ጋር ያገናኘናል፣ እና
  • ዘር፣ ደረጃ፣ ጾታ፣ የወሲባዊነት ዓይነት፣ ዜግነት፣ ዕድሜ፣ ወይም ችሎታ ሳይለይ – ሁሉንም ሰው – በክብር እና በእኩልነት ይንከባከባል።

የሲያትል የማመላለሻ እቅድ (STP) መቼ ነው የሚያበቃው?

ረቂቁ STP በ2023 አጋማሽ ላይ ለህዝብ ግምገማ ይገኛል።

አሁኑኑ መሳተፍ እችላለሁ?

አዎ! የእርስዎን እሴቶች፣ ፍላጎቶች እና ልምዶች/ ገጠመኞችን የሚያንፀባርቅ አንድ እቅድ ማዳበር እንፈልጋለን። ሃሳቦችዎን ለማጋራት የእኛን የሲያትል የማመላለሻ እቅድ የመስመር ላይ የተሳትፎ ማእከልን ይጎብኙ!

የጊዜ ሰሌዳ

መጋቢት 2022፡ የሥራ እቅድ ጅምር!

      • በዚህ ወር ውስጥ ግቦቻችንን፣ አላማዎቻችንን፣ መርሃ ግብሮቻችንን እና የተሳትፎ እድሎችን ከአጋሮቻችን እና ማህበረሰቦች ጋር እያጋራን ነው።

ከግንቦት - ነሐሴ 2022

      • የህዝብ ተሳትፎ ዙር 1። በዚህ ዙር ወቅት፣ በሲያትል ዙሪያ ስትንቀሳቀሱ ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ነገሮች፣ ተግዳሮቶችዎን እና ፍላጎቶችዎን ለመረዳት ከማህበረሰቡ ጋር ሰርተናል።

        በመጀመሪያው የተሳትፎ ዙር ወቅት እያንዳንዳችሁ ግብአቶቻችሁን እና ሃሳቦቻችሁን ያካፈላችሁትን ሁሉ እናመሰግናለን! በሲያትል ዙሪያ ስትንቀሳቀሱ ቅድሚያ የምትሰጧቸውን ነገሮች፣ ተግዳሮቶቻችሁን እና ፍላጎቶቻችሁን እንድታካፍሉ ጠይቀናችኋል።

        እስካሁን የሰማናቸውን እና እቅዱ እንዴት ቅርጽ እየያዘ እንዳለ በአጭሩ የሚገልጸውን የዙር 1 የተሳትፎ ማጠቃለያውን በኋላ በዚህ በልግ እናካፍላለን። እስከዚያው ድረስ፣ በዙር 1 ወቅት ሰዎች በእኛ የመጀመሪያ በይነተገናኝ የካርታ ስራ ላይ ያስቀመጧቸውን የወረቀት መርፌዎችን መገምገም ይችላሉ።

ከመስከረም-ታህሳስ 2022

      • የህዝብ ተሳትፎ ዙር 2። በሁለተኛው ዙር የተሳትፎ ወቅት፣ በዙር 1 ወቅት ከእናንተ የሰማነውን እናካፍላለን እና የእናንተ ግብአቶች እንዴት ዕቅዱን እንደሚመራ እየረዳ ያለበትን እናሳያለን። እንዲሁም ወደፊት እርስዎ እንዴት መዘዋወር እንደሚፈልጉ፣ እኛ ምን እርምጃዎችን እንድንወስድ እንደሚፈልጉ፣ እና እነዚህ እርምጃዎች የማመላለሻ ስርዓታችን አካል እንዲሆኑ እንዴት ማየት እንደሚፈልጉ ለመረዳት እንሰራለን።

ከጥር - ሰኔ 2023

      • የህዝብ ተሳትፎ ዙር 3። በህዝባዊ ተሳትፎ ደረጃ 3፣ ለአስተያየትዎ የ STP ረቂቅን ከእርስዎ ጋር እያጋራን ነው።

በ2024 መጀመሪያ

  • STPው ተጠናቅቋል!

ሲያትል ይህን እቅድ ለምን አሁን አስፈለጋት?

አስቸኳይ እና አዳዲስ ተግዳሮቶች: በጋራ፣ የማመላለሻ ስርዓታችንን የሚነኩ የመጓጓዣ ችግሮች እያጋጠሙን ነው። ይህ የሚያካትተው:

      • የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በማህበረሰብ ኑሮዎች እና በምንጓዝበት መንገድ ላይ እያስከተለ ያለው ተጽእኖ፣
      • በመንገዶቻችን ላይ ድንገተኛ የአየር ንብረቱ ጽንፈኛ የአየር ሁኔታ እያሳደረ ያለው አሉታዊ ተጽዕኖ፣
      • ትራፊክን የሚያስጨምር የህዝብ ቁጥር ከፍ የሚያደርግ እና በህዝብ ማመላለሻ አቅራቢያ በተመጣጣኝ ዋጋ የመኖሪያ ቤት አስፈላጊነትን ሲያጐላ፣
      • እና ተጨማሪ ብዙ።

እነዚህ አስቸኳይ እርምጃ ይጠይቃሉ። ለእነዚህ ተግዳሮቶች ምላሽ የሚሰጥ እና ሁሉም ሰው በሲያትል ዙሪያ በደህና፣ በብቃት እና በተመጣጣኝ ዋጋ መዘዋወርን እንዲረዳ አዲስ የመጓጓዣ ዘዴን መተለም እና መፍጠር አለብን።

የአዲሱ የማመላለሻ ልማት የገንዘብ ድጋፍ ጥቅል: የእኛ የአሁኑ የገንዘብ ድጋፍ ጥቅላችን፣ የሲያትል ማንቀሳቀስ ቀረጥ (Levy to Move Seattle)፣ በ2024 ያበቃል። ሲያትልን ለማንቀሳቀስ ቀረጥ (Levy to Move Seattle) በዘጠኝ አመታት ውስጥ (2016-2024) $930 ሚሊዮን ዶላር ያቀርባል እና 30% የሚሆነውን የማመላለሻ በጀታችንን ያቀርባል። በግብረመልስዎ ላይ የተመሰረተ አዲስ የገንዘብ ድጋፍ ጥቅል ማዘጋጀት አለብን። በርስዎ እገዛ የሲያትል የማመላለሻ እቅድ (STP)ን በመፍጠር፣ ፍላጎቶችዎን የሚያሟላ የሚቀጥለውን የገንዘብ ድጋፍ ጥቅል ማዘጋጀት እንችላለን።

ከሲያትል አጠቃላይ የእቅድ ማሻሻያ ጋር መጣጣም: የሲያትል አጠቃላይ የእቅድ ማሻሻያ (አጠቃላዩ እቅድ) በሚቀጥሉት ሃያ አመታት ውስጥ እንዴት ሲያትል እንደሚያድግ እና እንደሚሻሻል የትልቅ-ምስል ውሳኔዎች ሲያደርጉ የከተማው መምሪያዎች የሚጠቀሙበት መሳሪያ ነው። ከሌላ ብዙ ነገሮች ውስጥ፣ የማመላለሻ አካልን አጠቃላይ እቅድ ያካትታል። የሲያትል የማመላለሻ እቅዱን (STP) እያዘጋጀን ሳለ አጠቃላይ እቅዱም እየተዘመነ ነው። ይህ አስፈላጊ ነው ምክንያቱም የሲያትል የማመላለሻ እቅድ (STP) ከአጠቃላይ የእቅድ ግቦቹ እና ፖሊሲዎች በማመላለሻ ስርዓታችን ውስጥ እንዴት ሕይወት እንደሚዘሩ ለህብረተሰቡ የበለጠ ዝርዝር ግልጽነት ስለሚሰጥ ነው።

ይህንን እቅድ የሚያንቀሳቅሱት የትኞቹ እሴቶች ናቸው?

የሲያትል የማመላለሻ እቅድ (STP) እሴቶቻችንን ያንፀባርቃል። እቅዱ ከባድ ተግዳሮቶቻችንን ለመፍታት በእኛ የአየር ንብረት፣ ፍትሃዊነት፣ መጋቢነት እና የደህንነት ፍላጎቶች ላይ የሚያተኩር ሆኖ ይረዳል።

የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ እሴቶች እና ግቦች:

ፍትሃዊነት: ማመላለሻ የቀለም ማህበረሰቦችን እና በገቢዎች ሁሉም ላሉ፣ ችሎታዎች እና የእድሜ ፍላጎቶች ማሟላት አለበት ብለን እናምናለን። ግባችን የዘር አኩልነት የሰፈነበት እና ማህበራዊ ፍትህ የነገሰበት የማመላለሻ ሥርዐት ለመገንባት ከማህበረሰቦች ጋር አጋርነት መመስረት ነው።

ደህንነት: ሁሉም ሰው በከተማው ውስጥ በደህና መንቀሳቀስ መቻል አለበት ብለን እናምናለን። ግባችን ደህንነቱ የተጠበቀ የማመላለሻ አከባቢዎችን መፍጠር እና በሲያትል ውስጥ ከባድ እና ገዳይ አደጋዎችን ማስወገድ ነው።

ተንቀሳቃሽነት: የመጓጓዣ ምርጫዎች እድሎችን ለማግኘት ወሳኝ እንደሆኑ እናምናለን። ግባችን ሰዎችን፣ ቦታዎችን እና እቃዎችን በአስተማማኝ ሁኔታ የሚያገናኝ ተደራሽ የማመላለሻ ስርዓት መገንባት፣ መስራት እና ማቆየት ነው።

ዘላቂነት: በዘላቂ መጓጓዣ በኩል የአካባቢ ጤና ለወደፊት ትውልድ መሻሻል አለበት ብለን እናምናለን። ግባችን የአየር ንብረት ቀውሱን ዘላቂነት ባለው፣ መቋቋም በሚችል የማመላለሻ ሥርዓት መፍታት ነው።

መኖር: የዕለት ተዕለት ኑሮን ለመደገፍ ማመላለሻ አስፈላጊ ነው ብለን እናምናለን። ግባችን የህዝብን ህይወት በሚያበለጽግ እና የማህበረሰብ ጤናን በሚያሻሽል መንገድ መንገዶቻችንን እና የእግረኛ መንገዶቻችንን ማስተዳደር ነው።

በጣም ጥሩ መሆን: የምናገለግላችው ማህበረሰቦች ከሚጠበቁት በላይ እንደሆነ እናምናለን። አላማችን ዛሬ እና ነገ የሚያጋጥሙትን ፈተናዎች ለመቋቋም በላቀ እና በክህሎት የታጠቀ ቡድን መገንባት ነው።

ሲያትል ከበፊቱ ብዙ እቅዶች አሉት። አዲስ እቅድ ለምን ያስፈልገናል? ከዚህ የተለየ ምን ያደርጋል?

ሁለንተናዊ እቅድ: STP የመንቀሳቀስ፣ የመዳረሻ፣ እና የህዝብ ቦታ ፍላጎቶችን በአንድ ሰነድ ውስጥ እንደ አንድ የተዋሃደ ስርዓት ይመለከታል። እቅዱ የአሁን እና የወደፊት ፍላጎቶቻችንን ለማሟላት ያሉትን የእግረኛ፣ የብስክሌት፣ የመጓጓዣ እና የጭነት የአሰራር እቅዶቻችንን ያሻሽላል። STP እንደ የሲያትል ራዕይ ዜሮ፣ የዘር እና የማህበራዊ ፍትህ ተነሳሽነት፣ የአየር ንብረት የድርጊት መርሃ ግብራችን፣ የማመላለሻ በኤሌክትሪክ ሀይል የመስራት ንድፍ እና ሌሎችን የመሳሰሉ በርካታ የከተማ ውጥኖችን ያካትታል። በተጨማሪም፣ የትኞቹ ስልቶች ሲያትልን በተሻለ ሁኔታ እንደሚያገለግሉ ለማየት እንድንችል በሌሎች የክልል የማመላለሻ ወኪሎች የተፈጠሩ እቅዶችን ያጣቅሳል።

የአሰራር ውህደት እና ቅልጥፍና: STP እድሎችን፣ ሰዎችን እና ቦታዎችን ለማግኘት በጋራ እንዲሰሩ የመንቀሳቀስ አማራጮችን (እንደ ብስክሌት መንዳት፣ መራመድ፣ ትራንዚት መውሰድ እና ሌሎችም) እርስዎን ያግዛል።

የማህበረሰብ ተሳትፎ: ለሲያትል ማመላለሻ እቅድ (STP) ግልፅ የሆነ፣ ሁሉን የሚያሳትፍ ቅድሚያ እንሰጣለን። ለእርስዎ እና ለጎረቤቶችዎ ለመሳተፍ በተሻለ ቀላል ለማድረግ አዳዲስ አቀራረቦችን እንጠቀማለን።

በእቅድ ሂደቱ ውስጥ ማኅበረሰቡ እንዴት ይሳተፋል?

በእርስዎ ተመርቶ: STP በእናንተ – በማህበረሰቦቻችን ይመራል። ድምጾቻችሁ ለእቅዱ ቅርጽ በመስጠት ይረዳሉ። ከሁሉ የላቀ የማመላለሻ ችግሮቻችንን ለከተማችን በአዲስ እይታ ለመቅረፍ በምንሰራበት ወቅት የእናንተን ሃሳቦች እንሰማለን እና ምላሽ እንሰጣለን።

በተለምዶ ከዕቅድ ሂደት ውጪ በሆኑ ሰዎች ላይ ትኩረት: የወደፊት የማመላለሻ ስርዓታችንን ለመቅረጽ በመላ ሲያትል ካሉ ሰዎች ጋር እናገናኛለን፣ ይህም አብዛኛውን ጊዜ ከዕቅድ ሂደቱ ውጪ በሆኑ ሰዎች ላይ በማተኮር ነው። ይህም ጥቁር፣ ተወላጅ ወይም ጥቁር የቀለም ማህበረሰብ አካል የሆኑትን፤ LGBTQIA+ የሆኑ ሰዎች፤ በድህነት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች፤ ስደተኛ ማህበረሰቦች እና በቤት ውስጥ እንግሊዝኛ የማይናገሩ ሰዎች፤ ወጣቶች/ ጐልማሶች፤ አረጋውያን አዋቂዎች፤ እና አካል ጉዳተኞችን ያጠቃልላል።

ከማህበረሰቡ ጋር ቅርበት ያላቸውን አቅም መገንባት: ማህበረሰብን መሠረት ካደረጉ ድርጅቶች እና ከሲያትል የጎረቤት መምሪያ ማህበረሰብ ትስስር ጋር በመተባበር ከማህበረሰባችን ጋር ሽርክና የሚፈጥር፣ ለሁሉም ሰው መሳተፍ ቀላል የሚያደርግ እና የዘር እኩልነት መሰረት ላይ የሚገነባ የተሳትፎ ሂደት ለማዳበር እየሰራን ነው።

አዲስ የተሳትፎ ስልቶች: በሲያትል የማመላለሻ እቅድ (STP) የተሳትፎ ሂደት፣ ሰዎች በዘር ፍትሃዊ እና እኩልነት ባለው መንገድ እንዲሳተፉ ቀላል ለማድረግ እየጣርን ነው። ከተጨማሪ ድምጾች እንሰማለን፣ ብዙ ጊዜ የተገለሉ ማህበረሰቦች ተሳታፊ መሆናቸውን እናረጋግጣለን እና ሰዎች የእነሱ ተሳትፎ አስፈላጊ እንደሆነ እንዲሰማቸው እንረዳለን። ይህን የምናደርገው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ለህብረተሰብ ጤና ቅድሚያ የሚሰጡ ከባህል ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን፣ ተደራሽ እና አካታች ስልቶችን በመጠቀም ነው።

በዚህ ሂደት ውስጥ የእናንተ ድምጾች በጣም አስፈላጊ አካል ይሆናል፣ እና ከእናንተ እና ከጎረቤቶቻችሁ ጋር ለመላው ሲያትል የሚሰራ አንድ እቅድ ለማዘጋጀት በጉጉት እንጠባበቃለን።

የሲያትል ማመላለሻ እቅድ (STP) ከሲያትል አጠቃላይ እቅድ ዝመና ጋር እንዴት ተገናኘ?

የሲያትል አጠቃላይ የእቅድ ማሻሻያ - አንድ የሲያትል ፕላን - በሚቀጥሉት ሃያ አመታት ሲያትል እንዴት እንደሚያድግ እና እንደሚለማ ጠቃሚ ውሳኔዎችን ይመራል።

ሁለቱንም እቅዶች በአንድ ጊዜ ለማዘጋጀት ከእቅድ እና ማህበረሰብ ልማት ቢሮ (OPCD) ጋር በቅርበት እንሰራለን። በጋራ፣ የ STP እና አንድ የሲያትል እቅድ የወደፊት መኖሪያ ቤቶችን፣ ስራዎችን እና የማህበረሰብ መዋዕለ ንዋዮችን አብረን እንቃኘዋለን።

የበለጠ ለማወቅ እና የሲያትል ትልቁን ምስል የወደፊት ሁኔታን ለመጋራት የ OPCDን አንድ የሲያትል እቅድ ድህረ ገጽን ይጎብኙ።

ለሲያትል የማመላለሻ እቅድ የአካባቢ የአየር ንብረት ግምገማ ሂደት ምንድ ነው?

የሲያትል የማመላለሻ እቅድ (STP) በስቴት የአካባቢ የአየር ንብረት የአቋም መመሪያ ሕግ (SEPA) ግምገማ ሂደት ውስጥ ያልፋል። SEPA ዕቅድ በማውጣት እና በውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች የአካባቢ ንብረት እሴቶችን በሚገባ ግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑን ያረጋግጣል።

የተፈጥሮ የአካባቢ ተጽዕኖ መግለጫ (EIS) ግኝቶች ለግልጽነት ያለንን ቁርጠኝነት ያጠናክራሉ እና በመረጃ የተደገፈ ውሳኔ የማድረግ አስተዋፅዖ ያበረክታል። በተፈጥሮ የአካባቢ ተጽዕኖ መግለጫ (EIS) ላይ እርስዎ የሰጡት አስተያየቶች በትልቁ የማህበረሰብ ተሳትፎ በኩል ለSTP በአንድ ላይ ተዳምሮ ከተጋራው ግብአት ጋር እየተካተተ ነው።

አስተያየት የማሳያ/ የማካለል ወቅት: ሰኔ 16 - ሐምሌ 29 ቀን 2022

በአስተያየት መስጫ ወቅት እያንዳንዳችሁ አስተያየቶችን ከኛ ጋር የተካፈላችሁትን ሁሉ እናመሰግናለን። የእርስዎ ግብአት በተፈጥሮ የአካባቢ ተጽዕኖ መግለጫ (EIS) ውስጥ ምን እንደሚካተት እያሳወቀ ነው።

Transportation

Greg Spotts, Director
Address: 700 5th Ave, Suite 3800, Seattle, WA, 98104
Mailing Address: PO Box 34996, Seattle, WA, 98124-4996
Phone: (206) 684-7623
684-Road@seattle.gov

Newsletter Updates

Subscribe

Sign up for the latest updates from Transportation

The Seattle Department of Transportation (SDOT) is on a mission to deliver a transportation system that provides safe and affordable access to places and opportunities for everyone as we work to achieve our vision of Seattle as a thriving, equitable community powered by dependable transportation.