የሲያትል መደብር መነቃቃት

ከጥቁር፣ የአገሬው ተወላጆች እና ሌሎች ስራ ፈጣሪዎች እና ባለቀለም አርቲስቶች ብቅ-ባይ ሱቆች እና የጥበብ መገጣጠሚያዎችን ከክፍት የሲያትል መሃል ከተማው የሱቅ ፊት ለፊት ጋር ለመግጠም የሲያትል ኢኮኖሚ ልማት ጽህፈት ቤት ከሲያትል ጉድ ብዝነስ ኔትወርክ (Seattle Good Business Network) እና ሹንፓይክ (Shunpike) ጋር እየተባበረ ነው። እነዚህ የሥራ እቅዶች ህዝቡ የሲያትል መሃል ከተማውን እንዲጎበኝ የሚያበረታታ፣ የአካባቢ ንግዶችን እና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን የሚደግፉ ንቁ እና አሳታፊ የመንገድ ገፅታዎችን በመፍጠር ሰፈሮችን፣ አነስተኛ ንግዶችን፣ አርቲስቶችን እና የንብረት ባለቤቶችን ይጠቅማሉ። ይህ ፕሮግራም በአሜሪካ የነፍስ አድን እቅድ (the American Rescue Plan) ሥር በተቋቋመ በኮሮናቫይረስ አካባቢያዊ ፊስካል ማገገሚያ ፈንድ (CLFR) የገንዘብ ድጋፍ እየተደረገለት ነው።

ከሁለት እስከ አራት ወራት የሚፈጅ ተለዋዋጭ የአጭር ጊዜ የማነቃቃት እንቅስቃሴዎችን በማቅረብ፣ የሲያትል መደብር መነቃቃት (Seattle Restored) የመደብር የፊት ለፊት ገፅታዎች ከታህሳስ 2021 እስከ ሚያዚያ 2022 ይከፈታሉ። ለመሳተፍ ምንም ወጪ የለም፣ እና ፕሮግራሙ ለእያንዳንዱ ተሳታፊ አነስተኛ ንግድ እና አርቲስት $2,500 ዶላር የስራ ካፒታል ይሰጣል።

የሲያትል መደብር መነቃቃት (Seattle Restored) ማመልከቻዎች ጥር 17፣ 2022 ይዘጋሉ።   

የአከራይ እና የንብረት አስተዳዳሪ ማመልከቻ

የአነስተኛ ንግድ እና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ማመልከቻ

አመልካቾች እስከ ፌብሩዋሪ 25፣ 2022 ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል። በሲያትል መደብር መነቃቃት (Seattle Restored) ላይ ለበለጠ መረጃ፣ ብቁነት እና መስፈርቶች፣ ወደ www.SeattleRestored.org ይሂዱ።

 

የሲያትል የኢኮኖሚ ልማት ጽሕፈት ቤት ለሁሉም የሲያትል የተለያዩ ማኅበረሰቦች የኢኮኖሚ ዕድሎችን ተደራሽነት በማስተዋወቅ ከተማዋን በሙሉ የሚጠቅም ፍትሐዊና ሁሉን አቀፍ ኢኮኖሚ ለመገንባት ቁርጠኛ ነው። የንግድ ተመጣጣኝነት እና የአጎራባች ንግድ ዲስትሪክት ቡድኖች ማህበረሰቦች እንዲበለፅጉ እና ከጎረቤት አጋሮች፣ ከአነስተኛ ንግዶች እና ፈጠራዎች ጋር በጋራ በመሆን የጋራ ሀብትን እና እድገትን የመቋቋም ችሎታን እንዲገነቡ ያግዛሉ። 

ለተጨማሪ ጥያቄዎች፣ ለትርጉም ወይም ለትርጓሜ፣ ለቴክኒክ ድጋፍ፣ ለአካል ጉዳተኝነት ማስተናገጃዎች፣ ተለዋጭ ፎርማት ላላቸው ቁሳቁሶች ወይም የተደራሽነት መረጃ ለማግኘት እባክዎ የሲያትል የኢኮኖሚ ልማት ጽሕፈት ቤትን በ (206) 684-8090 ወይም oed@seattle.gov ያግኙ።