ከመሄድዎ በፊት ይወቁ (Know Before You Go)

English
አማርኛ
繁體中文
한국어
Soomaali
Español
Tiếng Việt

ይህንን በራሪ ወረቀት ማተም ይችላሉ።

የከተማው ኣስተዳደር ባዘጋጀው የሉመን ፊልድ የኮሚዩኒቲ የክትባት ጣብያ ለመከተብ ቀጠሮ በመያዝዎ እናመሰግናለን።

ጉብኝትዎ የተሳካና ደህንነቱን የጠበቀ እንዲሆን፡ ከጉብኝትዎ በፊት ምን ይዘው መምጣት፡ የት መሄድ፡ ምን መጠበቅ እንዳለብዎ ዘርዝሮ የሚገልጽ "ከመሄድዎ በፊት ይወቁ" የሚለውን ጽሑፍ በደምብ ይመልከቱ። ስለ ኩነቱ ጥያቄ ካለብዎት ወይም ለኣካለ ጉዳተኛ የሚያስፈልግ ኣቀባበል ለመጠየቅ ከፈለጉ የስያትል ከተማ የደምበኞች ኣገልግሎት ጽ/ቤት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ8 a.m. እስከ 5 p.m ባለ ግዜ (206) 684-2489 ወይም (206) 684-CITY ይደውሉ። የትርጉም ኣገልግሎት በስልክም ሆነ በክትባት ጣብያው ኣዘጋጅተናል።

ከቀጠሮዎ በፊት

የሚከተሉትን ክስተቶች ካጋጠምዎት፡ ለርስዎና ለሌሎች ጤንነትና ደህንነት ሲባል ወደ ጣብያው ኣይምጡ።

 • የኮቪድ-19 ሕመም የሚመስሉ ምልክቶች ካለብዎት፡ እንደ ትኩሳት፡ የጉሮሮ ሕመም ወይም ሳል የመሳሰሉ። ወይም
 • ኮቪድ-19 እናዳለበት ከተረጋገጠ ሰው የቅርብ ግንኙነት ካደረጉ

ወደ ቀጠሮ ጣብያ ምን ይዘው ይምጡ

 • ፎቶግራፍዎ ያለበት መታወቅያ ወረቀት
 • ማስክ ወይም የፊት ሽፋን
 • ክትባቱ በላይኛው የክንድዎ ኣካባቢ በቀላሉ ለመስጠት እንዲቻል፡ ጉርድ እጅጌ፡ ወይም እጅጌው ወደላይ በቀላሉ መሰብሰብ የሚችል ልብስ ይልበሱ።

  መታወቅያ ወረቀት ባይኖርዎትም ክትባቱ በነጻ ይሰጥዎታል።

ምን ይዘው መምጣው የለብዎትም

 • የቤት እንሰሳት (ፐት) (ዓይነስዉር መሪ ውሻ ካልሆነ)
 • ጓደኞችና ቤተሰብ። ልጆች የሚጠብቅልዎ ከሌለ ልጆችዎ፡ እርዳታ የሚያስፈልግዎ ከሆነም እርዳታ ሰጭ ይዘው መምጣት ይቻላል። ክትባቱ ቀጠሮ ላስያዙ ሰዎች ብቻ ነው የሚሰጠው።
 • ትልቅ ሻንጣ/ቦርሳ ወይም ባክ ባክ

በየትኛው ሰዓት ላይ መድረስ እንዳለብዎት

በተቻለ መጠን ያስያዙት ቀጠሮ ትንሽ ግዜ ሲቀረው ይድረሱ።

 

የት ፓርክ ማድረግ እንደሚኖርብዎት

330 S Royal Broughman Way በሚገኘው የሉመን ፊልድ ፓርኪን ማእከል ጋራጅ ነጻ ፓርኪን ይኖራል። ጋራጁ ከሮያል ብሮጋም ወይ ሳውዝ ጎን እንዲሁም ከቲ-ሞቢል ፓርክ ማዶ ይገኛል።

 

ላስያዙት ቀጠሮ የት መሄድ እንዳለብዎ

ቀጠሮዎ በከተማው የኮሚዩኒቲ ክትባት ጣብያ፡ በሉመን ፊልድ ነው።

 • በመኪና ከመጡ፡ እባክዎ 330 S Royal Broughman Way ባለው የሉመን ፊልድ ፓርኪን ጋራጅ ፓርክ ኣርገው ወደ ጣብያው የሚወስድ የኣቅጣጫ ምልክቶችን ይከተሉ (ከታች ያለውን ምስል ይመልከቱ)።
 • በህዝባዊ መጓጓዣ ወይም በእግር ከመጡ፡ ሮያል ብሮጋም ወይ ሳውዝ እና ኦክሲደንታል ኣቨኑ ሳውዝ ከሚጋጠሙበት ኣጠገብ ያለው ዋናው የኮሚዩኒቱ የክትባት ጣብያ መግብያ ይጠቀሙ።
 • ሁሉም መግብያዎች ለኣካለ ጉዳተኞች (ADA) ኣመቺ ናቸው። ዋናው የኣካለ ጉዳተኞች መግብያ ወደ ሉመን ፓርኪን ጋራጅ የቀረበው መግብያ ነው።

Map displaying the location of the Lumen Field Event Center Mass Vaccination Site and parking lot

ጣብያው እንደደረሱ ምን መጠበቅ እንዳለብዎት

ክትባት የሚሰጡትንም ይሁን እንግዶች በሙሉ ጣብያው ጋ እንደደረሱ የሚከተሉትን ይጠየቃሉ፡

 1. ቀጠሮ ማስያዝዎን ማረጋገጥ።
  ቀጠሮ የሚያረጋግጡ እንግዳ ተቀባዮች በጣብያው ይኖራሉ። ክትባት ለመውሰድ ቀጠሮ ያስያዙ ብቻ ነው ክትባቱ የሚሰጣቸው። ትርፍ የክትባት ኣቅርቦት የለም። ኣለቀጥሮ ክትባት መውሰድም ኣይፈቀድም።

 2. የእጅዎ ንፅሕና ይጠብቁ (ሳኒታይዝ)፡ ማስክ ወይም የፊት መሸፈኛ ይልበሱ።
  ማስክ ከሌለዎት በጣብያው ይሰጥዎታል።

 3. የጤና ጥበቃ ማጣርያ ጥያቄዎችን ይመልሱ
  በየመግብያው ትኩረትዎ የሚጠይቅ የጤና ጥበቃ ማጣርያ ጥያቄዎች ተለጥፈዋል። የኮቪድ ምልክቶች እንደሌለብዎት ወይም ኮቪድ-19 ከያዘው ሰው እንዳልተገናኙ የቃል ምስክርነትዎ የሚቀበሉ እንግዳ ተቀባዮች በጣብያው ይኖራሉ። ይህ እርምጃ የታካሚዎችና እንግዶች እንዲሁም በጣብያው ያሉ በጎ ፈቃደኞች እና ሰራተኞች ጤናና ደህንነት ለመጠበቅ ነው።

  የኣስተርጓሚ ኣገልግሎት በጣብያው ኣዘጋጅተናል።

 4. በጸጥታ ኣስከባሪ መስመር ወይም የቦርሳ ፍተሻ ይለፉ
  መግባት እንዳይከለከሉ፡ በጣም ኣስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ብቻ ይዘው ይምጡ። ትልቅ ሻንጣ ወይም ባክፓክ ይዘው ከመምጣት ይቆጠቡ።

 

ጣብያው ውስጥ እንደገቡ ምን እንደሚጠብቁ

1ኛ እርምጃ፡ የመምጣትዎ ምዝገባ (ቸክ ኢን)

ታካሚዎች የምዝገባና የክትባት ወረፋ ወደሚይዙበት ኣቅጣጫ መመርያ ይሰጣል። ለመንቀሳቀስ ረዳት የሚፈልጉ ከሆነ Line A የሚለውን መስመር ይያዙ። የኣስተርጓሚ እርዳታ የሚፈልጉ ከሆነ Line B የሚለውን መስመር ይያዙ። ቀጠሮው ጀምሮ እስኪያልቅ ማስክ እንዲያረጉና ማህበራዊ ርቀት እንዲጠብቁ ያስፈልጋል።

የቀጠሮ ማረጋገጫዎ ዝግጁ ያርጉ። ፎቶግራፍ ያለው ማስታወቅያ ወረቀት ከያዙም፡ ለማሳየት ዝግጁ ያርጉ። በጣብያው የምትሰጡት ስምና ቀጠሮ ስታስይዙ ያስገባችሁትን ስም መለያየት የለበትም።

2ኛ እርምጃ፡ ክትባት መውሰድ

የጤና ኣጋሮቻችን ከሆኑት ኣንዱ ክትባት ይሰጥዎታል። ክትባት መሰጠት በምትፈልጉት ክንድ ያልው እጅጌ ወደላይ ይሰብስቡ። መሸፈኛ ፋሻ ይሰጥዎታል። ከጠየቁም፡ ስለወሰዱት ክትባት ተጨማሪ መረጃ ይሰጥዎታል። ተመሳሳይ መረጃ በቀጠሮ ማረጋገጫ ኢመይልዎ ይላክልዎታል።

3ኛ እርምጃ፡ በማቆያ/መከታተያ ቦታ ኣረፍ ብሎ መጠበቅ

ሰዓት ቆጣሪዎ ለ15 ደቂቃ በማዘጋጀት በመከታተያ ቦታ ኣረፍ ብለው ይቀመጡ። ከበድ ያለ የሕመም ስሜት ከተሰማዎት እባክዎን ለ30 ደቂቃ ይጠብቁ።

4ኛ እርምጃ፡ ሁለተኛውን ክትባት የሚወስዱበትን ቀን በቀን መቁጠርያዎ ያስገቡ

መውሰድ ካለብዎት ሁለት ክትባቶች ይህ የመጀመርያው ከሆነ፡ ሁለተኛውን ዶዝ እንዳይረሱ፡ የሚወስዱበትን ቀን በቀን መቁጠርያዎ ያስገቡ። ራስዎን ከኮቪድ-19 ለመከላከል በጣሙን ውጤታማ የሆነው መንገድ የሚፈለጉትን የክትባት ዶዞች በሙሉ ወስዶ መፈጸም ነው።

Community Vaccination Hubs

The City of Seattle helps operate a COVID-19 Community Vaccination Hub at North Seattle College in partnership with the Seattle Visiting Nurse Association.

The Community Vaccination Hub at North Seattle College is primarily a drive-through site, but it can also accommodate people biking and walking. Patients can enter the campus using the 95th Street entrance immediately off of College Way. The vaccination hub will initially operate three days per week, Wednesday through Friday, from 9 a.m. to 4 p.m. As supply increases, the days and hours of operation will increase.

You can find a "What to Expect" flyer here.

Community-based organizations that serve BIPOC communities, older adults, and immigrants and refugees have advance registration access to the site. Appointments also become available to eligible residents who have signed up through the City of Seattle vaccine notification list.

If you have any additional questions, please contact the Customer Service Bureau for additional questions:
(206) 684-2489

The Seattle Fire Department operates a Community Vaccination Hub in the Rainier Beach neighborhood. The Community Vaccination Hub in Rainier Beach is a walk-up vaccination site that operates Monday – Saturday, from 9 a.m. to 4 p.m.

You can find a “What to Expect” flyer here.

Community-based organizations that serve BIPOC communities, older adults, and immigrants and refugees have advance registration access to the site. Appointments also become available to eligible residents who have signed up through the City of Seattle vaccine notification list.

If you have any additional questions, please contact the Customer Service Bureau for additional questions:
(206) 684-2489

The Seattle Fire Department operates a Community Vaccination Hub in the West Seattle neighborhood. The Community Vaccination Hub in West Seattle is a walk-up vaccination site that operates Monday – Saturday, from 9 a.m. to 4 p.m.

Community-based organizations that serve BIPOC communities, older adults, and immigrants and refugees have advance registration access to the site. Appointments also become available to eligible residents who have signed up through the City of Seattle vaccine notification list.

If you have any additional questions, please contact the Customer Service Bureau for additional questions:
(206) 684-2489